Time in Ethiopia:

Mar 26, 2014

የደቡብ ሱዳንና የግብፅ ወታደራዊ ስምምነት

Geez Bet | Wednesday, March 26, 2014
ደቡብ ሱዳን ከግብፅ ጋ የሁለትዮሽ ወታደራዊ ትብብር ስምምነት መፈራረሟን ዘገባዎች ያመለክታሉ። ጁባ ተመሳሳይ መግባባት ላይ ከሁለት ዓመታት በፊት ከተነጠለቻት ሰሜን ሱዳን ጋም መድረሷ ተገልጿል። 
ሱዳን ትሪቢዩን እንደሚለዉ የደቡብ ሱዳን እና ግብፅ ወታደራዊ ትብብር መፈራረም ይፋ የተደረገዉ በጁባ መንግስት ሥር በሚተዳደረዉ የደቡብ ሱዳን ቴሌቪዥን ነዉ። በመከላከያ ሚኒስትር ኩሎ ማንያንጋ ጁኩ የሚመራ የደቡብ ሱዳን የልዑካን ቡድን ካይሮን በጎበኘበት ወቅት ነዉ ካይሮና ጁባ የሁለትዮሽ ወታደራዊ ትብብር ስምምነቱን የተፈራረሙት። ዝርዝር ስምምነቱ ይፋ ባይሆንም የዜና አዉታሩ ወታደራዊ ምንጮቹን ጠቅሶ እንደዘገበዉ የወታደራዊ ኃይሎች የልምድ ልዉዉጥ፣ ልዩ ኃይሎችን የማሰልጠን እና በጋራ ልምምዶችን ማድረግን ያካትታል። ግብፅም ሆነች ደቡብ ሱዳን አሁን በሚገኙበት ያልተረጋጋ ሁኔታ ሊፈራረሙ የሚችሉት ወታደራዊ ስምምነት
ሙሉውን አንብብ-Read More

የሙሥሊም ወንድማማቾች የሞት ብይን

Geez Bet | Wednesday, March 26, 2014
በትናንትናዉ ዕለት የግብፅ ፍርድ ቤት በ529 የሙስሊም ወንድማማቾች ማኅበር አባላት ላይ የሞት ቅጣት በይኗል። ዉሳኔዉ በተሰጠበት በዚሁ ችሎት 147ቱ ብቻ ናቸዉ በስፍራዉ ተገኝተዉ ፍርዱን ያደመጡ ሲሆን ቀሪዎቹ ከሚጠብቃቸዉ ፍርድ ለማምለጥ በሽሽት ላይ መሆናቸዉ ተገልጿል። 
የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የካይሮ መንግስት የሞት ፍርድ ዓለም ዓቀፍ ሕግን እንደ ሚፃረር በማሳሰብ፤ ሌሎች ተመሳሳይ እጣ ይጠብቃቸዋል ያላቸዉ በሺዎች የሚገመቱ ዜጎች ሁኔታ እንደሚያሳሰበዉ ዛሬ አስታዉቋል።
ትናንት ግብፅ ዉስጥ የተላለፈዉ የሞት ቅጣት ብይን በሀገሪቱ ዘመናዊ ታሪክ የመጀመሪያዉ መሆኑ ነዉ የተገለጸዉ። ብይኑ ሲሰጥ ፍርድ ቤት በአካል የቀረቡት 147ቱ ሲሆኑ ቀሪ 398ቱ በሌሉበት ነዉ የተበየነባቸዉ። የእያንዳንዱ የክስ ሁኔታ ባለመነበቡም ማን በምን ምክንያት የሞት ብይን እንደተላለፈበት ለማወቅ ግልፅ እንዳልሆነ ነዉ የተገለፀዉ። የተከሳሽ ጠበቆች ደንበኞቻቸዉን
ሙሉውን አንብብ-Read More

Mar 24, 2014

የብሔራዊ ፈተናዎች ኩረጃ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ በጥናት ተመለከተ

Geez Bet | Monday, March 24, 2014
የአገሪቱ ብሔራዊ ፈተናዎች ላይ የሚታየው ኩረጃ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን በፌዴራል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ጥናት ተጠቆመ፡፡ መጋቢት 11 ቀን 2006 ዓ.ም.
‹‹በብሔራዊ ፈተናዎች ዙሪያ የሚስተዋሉ የሥነ ምግባር ችግሮች፣ ተግዳሮቶችና መፍትሔዎቻቸው›› በሚል ርዕስ ኮሚሽኑ ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ የቀረበው የመነሻ ጥናት ችግሩ አሳሳቢ ነው ተብሏል፡፡ 

የአገሪቱን የነገ ዕጣ የሚወስኑና ችግር ፈቺ ይሆናሉ የሚባሉ ተማሪዎች በተደራጀ ሁኔታ ኩረጃ ላይ መትጋታቸው ከሥነ ምግባር ችግርነት አልፎ በሙስና የሚፈረጅበት ደረጃ ላይ መድረሱን፣ በኮሚሽኑ የሥነ ምግባር ትምህርት ባለሙያ በመሆን ለአሥር ዓመታት ያገለገሉትና የጥናቱ አቅራቢ የሆኑት አቶ ከበደ ሲማ ገልጸዋል፡፡ ችግሩ አሳሳቢ ደረጃ ላይ በመድረሱ እንደ አገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና የፈተናዎች ኤጀንሲ ላሉ ተቋማት ብቻ የሚተው አለመሆኑንም አቶ ከበደ ጠቁመዋል፡፡ 
ሙሉውን አንብብ-Read More

የግብፅ ኩባንያ በኢትዮጵያ ትልቁን የወርቅ ክምችት አገኘ

Geez Bet | Monday, March 24, 2014
አስኮም ማይንኒግ የተባለው የግብፅ ኩባንያ በኢትዮጵያ ታሪክ እስከዛሬ ከተገኘው የላቀ የወርቅ ክምችት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አገኘ፡፡
የተገኘው የፅንስ ወርቅ ክምችት በኢትዮጵያ የወርቅ ፍለጋ ታሪክ ከተገኙ የወርቅ ክምችቶች በሙሉ ይበልጣል ተብሏል፡፡ 
በቅርቡ ከተደረሰባቸው የወርቅ ክምችቶች መካከል በቱሉ ካፒ ወለጋ ኒዮታ ሚኒራልስ የተሰኘ የእንግሊዝ ኩባንያ፣ በመተከል ሳካሮ በሚድሮክ ጐልድ በኦሮሚያና ትግራይ ክልሎች በናሽናል ማይኒንግ በአፋርና በትግራይ ክልሎች ስትራቴክስ በተባለው የእንግሊዙ ኩባንያ፣ በትግራይ ክልል በኢዛና ማይንኒግ የተገኙት ተጠቃሾች ናቸው፡፡ የግብፅ ኩባንያ አስኮም በቤኒሻንጉል
ጉሙዝ ክልል ያገኘው የወርቅ ክምችት በእነዚህ ኩባንያዎች ከተገኙት ክምችቶች ሁሉ እንደሚበልጥ ተገልጿል፡፡
    የማዕድን ሚኒስትሩ አቶ ቶሎሳ ሻጊ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ አስኮም ያገኘው የወርቅ ክምችት እስከዛሬ ከተገኙ ክምችቶች ሁሉ የላቀ ነው፡፡ የኩባንያው ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ለማዕድን ሚኒስቴር ኃላፊዎች ስላገኙት ግኝት ከሁለት ሳምንት በፊት ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን፣ ኩባንያው ባካሄደው
ሙሉውን አንብብ-Read More

Mar 22, 2014

Group: Ethiopia Regularly Records Phone Calls

Geez Bet | Saturday, March 22, 2014

NAIROBI, Kenya (AP) — A rights group says that Ethiopia's government regularly listens to and records the phone calls of opposition activists and journalists using equipment provided by foreign technology companies.
Human Rights Watch said in a report Friday that the foreign equipment aids the Ethiopian government's surveillance of perceived political opponents inside and outside the country.
The group's Arvind Ganesan said Ethiopia is using its government-controlled telecom system to silence dissenters. The group says that recorded phone calls with family and friends are often played during abusive interrogations.
Human Rights Watch said most of the monitoring technology is provided by the Chinese firm ZTE. Several European companies have also provided equipment, the group said, including from the U.K., Germany and Italy.
Source: Associated Press
ሙሉውን አንብብ-Read More

Mar 18, 2014

የክሪሚያ ሕዝበ ዉሳኔና አፀፋዉ

Geez Bet | Tuesday, March 18, 2014
ጊዚያዊ ጥቅላይ ሚንስትሩ እንዳሉት የሩሲያ ጦር በሳቸዉ አገላለጥ ለክሪሚያ «ገንጣይና ከፋፋዮች» ከለላ መስጠቱ እዉነት ነዉ።የዚያኑ ያክል ያዜንዩክና ጓዶቻቸዉ በዩናይትድ ስቴስና በተባባሪዎችዋ እቅፍ ዉስጥ መሆናቸዉም ሐቅ። 
የኪየቭ-አዲስ መሪዎች የትንሽ ግዛታቸዉን ትንሽ ጠላቶቻቸዉን ትተዉ የትልቅ ጎረቤታቸዉን ትልቅ ጠላታቸዉን እያወገዙ ደግሞ በተቃራኒዉ እንደራደር ይላሉ።የበርሊን-ለንደን-ፓሪስ መሪዎችና ተከታዮቻቸዉ ኪየቮችን ለፍጥጫ እያጃገኑ፤ ሞስኮዎችን ለመቅጣት እየዛቱ ከኪየቮች ጋር ተወያዩ ይላሉ።ኪየቭ-ብራስልሶችን የሚመሩት የዋሽግተን መሪዎች ሞስኮዎችን የሚያስፈራራ ጦር እያዘመቱ፤ ሞስኮዎችን እየቀጡ፤ ለተጨማሪ ቅጣት እየዛቱ ከሞስኮዎች ጋር ይደራደራሉ።የሞስኮ ጠላቶች የሌሉ ያክል የዘነጓቸዉ  የክሪሚያ የሞስኮ ታማኞች ትንሺቱን፤ ጥንታዊቱን ሥልታዊ ግዛታቸዉን ለሞስኮዎች ለማስረከብ ወሰኑ።ሩሲያዎች አስወሰኑ።የጦር ዘመቻ፤ የቅጣት እርምጃ ፉከራዉ ገቢር ይሆን-ይሆን? ላፍታ አብረን እንጠይቅ።

    በሩሲያ የሚደገፉት የዩክሬንዋ ትንሽ-ልሳነ ምድር ግዛት የክሪሚያ ራስ-ገዝ መስተዳድር ጠቅላይ ሚንስትር ስርጌይ አክሲየኖቭ፤ የምክር ቤቱ አፈ-ጉባኤ ቭላድሚር ኮንስታንቲኖቭ ከየካቲት ማብቂያ ጀምሮ-ካቢኔ ምክር ቤታቸዉን እንዳስወሰኑ፤ እንደዛቱ፤ እንደፎከሩት በርግጥም አደረጉት።
የትንሺቱ ሥልታዊ ምድር ሕዝብ ግዛቲቱ ከሩሲያ ጋር ዳግም እንድትዋሐድ በድምፁ ወሰነ።ሲምፌሮፖል-ትናንት።«ወደ ሩሲያ እንኳን ደሕና መጣሽ።»እስከ ትናንት ከክሪሚያ ትናንሽ ጠላቶቻቸዉ ይልቅ-የሞስኮ ጠንካሮችን ሲያወግዙ ሲወነጅሉ የከረሙት የኪየቭ አዲስ መሪዎች ትናንት እኒያን የትንሽ ግዛታቸዉን መሪዎች አስታወሱ፤ ወነጀሉ፤ ሊቀጡ- ሊያስቀጡ ዛቱም።ጊዚያዊ ጠቅላይ ሚንስትር አርሴኒ ያዜንዩክ።
«የዩክሬን መንግሥት እኒያን በሩሲያ ወታደሮች የተከለሉትን የዩክሬንን ነፃነት ለማጥፋት የሚንቀሳቀሱ የመገንጠልና የመከፋፈል ቀለበት መሪዎችን እንደሚይዛቸዉ ምንም ጥርጥር የለዉም።ዓ,መት፤ ሁለት ዓመት ይወስድ
ሙሉውን አንብብ-Read More

Mar 17, 2014

ግብረሶዶማዊነትን ለምን እንቃወማለን?

Geez Bet | Monday, March 17, 2014
(ካሣሁን ዓለሙ):-
አንዳንድ ጊዜ የግብረ ሰዶማዊነት የዚህን ያህል አሟጋች መሆኑን ሳይና በአለማቀፍ ተቋማት ድጋፍ አግኝቶ እንዲስፋፋ ሲደረግ ስመለከትና ስሰማ ይገርመኛል፤ ግርምቴ ዝም ብሎ የመጣ አይደለም፤ ይልቁንም ግብረሰዶም ከሰው ልጆች ተፈጥሮ ውጭ የሆነ ተግባር መስሎ ስለሚታየኝና የሚሰጠው ጥቅም አልገለጽልህ ቢለኝ ነው፡፡ ስለዚህ የራሴን መሟገቻ ነጥቦች ላቅርብ ፈለግሁ ይህ ጽሑፍም በዚህ ዕይታ የተቃኘ ነው፡፡ መልካም ንባብ!
ለመሟገትም ‹ግብረሰዶማዊነት ተፈጥሮ የሚደግፈው ድርጊት ነው ወይ?› በሚል ጥያቄ መነሣት የግድ ይላል፤ መልሱም ‹ግብረሰዶማዊነት ተፈጥሯዊ ነው› የሚል ከሆነ
ሙሉውን አንብብ-Read More

‹‹ለእኔ የአካዳሚክ ነፃነት ችግር ሆኖ አያውቅም›› ፕሮፌሰር ተከስተ ነጋሽ

Geez Bet | Monday, March 17, 2014
ፕሮፌሰር ተከስተ ነጋሽ፣ የኢትዮጵያ የትምህርት ጥራትና ተገቢነት ተመራማሪ
ፕሮፌሰር ተከስተ ነጋሽ የተወለዱት አስመራ ነው፡፡ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን አስመራ፣ የሁለተኛ ደረጃን ደግሞ በጅማ ነው የተከታተሉት፡፡

የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ከአስመራ ዩኒቨርሲቲ በሕግ አግኝተዋል፡፡ ለሁለት ዓመታት ከሠሩ በኋላ ስኮላርሺፕ አግኝተው እንግሊዝ ከሄዱ በኋላ ለረዥም ዓመታት ቆይተዋል፡፡ ያጠኑት ታሪክ ነበር፡፡ የኢትዮጵያ የትምህርት ጥራትና ተገቢነትን በተለያዩ ጥናቶቻቸው ለሃያ ሦስት ዓመታት ተመልክተዋል፡፡ “Crisis of Ethiopian Education፡ Implications for nation Building, Rethinking Ethiopian Education, Ethiopian Education from Crisis to Collapse” በሚሉ ርዕሶች መጻሕፍትም አሳትመዋል፡፡ የመጀመሪያውና እ.ኤ.አ. በ1990 በሲዳ ስዊድን ድጋፍ የታተመው መጽሐፋቸው ጥሩ ተቀባይነትን
ሙሉውን አንብብ-Read More

Mar 15, 2014

“ቅዱስ ኤልያስ ይዞት የመጣውን መፅሐፍ” ቤተ ክርስትያን እንድትቀበል ተጠየቀ

Geez Bet | Saturday, March 15, 2014
መጽሐፉ ለአቡነ ማትያስና ለጠ/ሚ ኃይለማርያም እንዲደርሳቸው ተደርጓል
ደብዳቤው ለእስራኤሉ ጠ/ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታናሁ እና ለተመድ ተልኳል

       ከተፃፈ ከ2 ሺህ ዓመታት በላይ አስቆጥሯል የተባለውንና ስለ ቅዱስ ኤልያስ መምጣት ምስጢር የሚተነትነውን መጽሐፍ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ተቀብላ ወደተለያዩ ቋንቋዎች በማስተርጎም ምዕመናኖችን እንድታስተምር፣ “ማህበረ ሥላሴ ዘደቂቀ ኤልያስ” ለቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ በጻፈው ደብዳቤ ጠየቀ፡፡
ሙሉውን አንብብ-Read More

Mar 13, 2014

የአ.አ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ የትምህርት ዘርፍና ፈተናው

Geez Bet | Thursday, March 13, 2014
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ የትምህርት ክፍል በተማሪዎች ብዙም የማይመረጥበት ሁኔታ የትምህርት ዘርፉን ሕልዉና ሳይፈታተን እንደሚይቀር እየተገነገረ ነዉ። 
     ወደዩኒቨርሲቲ የመግባት እድል ከሚያገኙ ተማሪዎች አብዛኞቹ ከምረቃ በኋላ ሥራ ከማግኘት እድል ጋ በተያያዘ የትምህርት ዘርፉን ከመምረጥ ሲቆጠቡ፤ 70/30 የተሰኘዉ የትምህርት ፖሊሲም የበኩሉን አስተዋፅኦ ማድረጉን ታዛቢዎች ያመለክታሉ። እንዲያም ሆኖ ከዘርፉ ምሁራን አንዳንዶች በቀጣይ በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ሕልዉናዉ ተጠናክሮ ይቀጥላል የሚል ተስፋ አላቸዉ።
በቅርቡ ነዉ የታሪክ የትምህርት ክፍል በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተከፈተበትን 50ኛ ዓመት ያከበረዉ። በወቅቱም በያዝነዉ የትምህርት ዓመት በትምህርት ክፍሉ ለመማር የተመዘገበ ተማሪ አለመኖሩ ተገልጿል። ለዚህ እንደምክንያት ከተጠቀሱት መካከል 70/30 በተባለዉ መርኀግብር መሠረት በማኅበራዊ ሳይንስ የትምሕርት ዘርፍ ባጠቃላይ የሚመደቡ በመቶዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች ወደበርካታ የትምህርት ዘርፎች መከፋፈላቸዉ አንዱ ነዉ። በዚህም ተማሪዎች የተሻለ የሥራ ዕድል ያስገኝልናል ብለዉ ወደሚያምኑት የትምህርት ክፍል ማዘንበላቸዉ የታሪክ ትምህርት ዘርፍን
ሙሉውን አንብብ-Read More

Mar 10, 2014

ፓትርያርኩ ‹‹ቤተ ክርስቲያን በዩኒቨርስቲ ምሩቃን አትመራም” ማለታቸው ቅሬታ ፈጠረ

Geez Bet | Monday, March 10, 2014
ስለማኅበራት የሰጡትን አስተያየት መልሰው እንዲያጤኑት ተጠየቀ
‹‹ማኅበራት በትኩረት ሊመሩና ጉዟቸውም እየተፈተሸ ሊስተካከል ይገባል›› - መንግሥት
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ‹‹ከዩኒቨርስቲ ተመርቀው ቤተ ክርስቲያንን እንምራ እያሉ ነው፤ ቤተ ክርስቲያኒቱ ትውፊትና ሥርዓት አላት፤እንዲህ ማለት አይችሉም›› በማለት የሰጡትን አስተያየት መልሰው እንዲያጤኑት በንግግራቸው ቅር የተሰኙ የመንፈሳውያን ማኅበራት አገልጋዮች ጠየቁ፡፡
አገልጋዮቹ ለአዲስ አድማስ እንደተናገሩት፣ አቡነ ማትያስ ይሄን አስተያየት የሰነዘሩት በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያ ከኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር ጋር በመተባበር የካቲት 21 እና 22 ያዘጋጁት ሀገር አቀፍ የስብከተ ወንጌል የምክክር ጉባኤ በተካሔደበት ወቅት ነው፡፡
ሙሉውን አንብብ-Read More

ተራማጁ ደራሲ ለምን ተገለለ?

Geez Bet | Monday, March 10, 2014
የፈጠራ ስራዎች ፀረ-ፊውዳል ድርሰቶች አይደሉም የሚል ምሁር ከመካከላችን ይኖራል? ታዲያ ፀረ-ፊውዳል ታጋዩና የመሬት ላራሹ መፈክር አንጋቢው ተራማጁ የተማሪዎች ማህበር ይህን ህዝባዊ ደራሲ ሳያጎላው ያለፈው ሆን ብሎ ይሆን ወይስ ረስቶት?

ይህን ጽሑፍ ያዘጋጀሁት ስለ አንጋፋው ደራሲ አቤ ጉበኛ አንዳንድ ሃሳቦችን ለመሰንዘር ነው። ጽሑፉ ከምርምርም በሉት ከጥናት ሥራ ጋር የሚመደብ አይደለም፡፡ ወፍ በረር ወይም ወፍ ዘለል ምልከታ አይባልም፡፡ በአጭሩ እኔ ስለአቤ የተሰማኝን የገለጽሁበት መላምታዊ ስሜት ነው፡፡
አቤን እኔ በሚገባ ወይም በቅርበት አላውቀውም፡፡ የአቸፈር ሰው መሆኑን፣ ዳንግላ መማሩን የተረዳሁት በቅርቡ ነው፡፡ የእኛ ዘመን
ሙሉውን አንብብ-Read More

አንድነት ሁለተኛውን ዙር “የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት”ንቅናቄ ጀመረ

Geez Bet | Monday, March 10, 2014
የመሬት ፖሊስን ለማስለወጥ እታገላለሁ ብሏል
አንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ የመሬት ጥያቄን አጀንዳው በማድረግ ለሶስት ወራት የሚዘልቅ ሁለተኛ ዙር “የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት” ንቅናቄ መጀመሩን ጠቁሞ መሬት በመንግስት ቁጥጥር ስር መሆኑን በመቃወም እንደሚንቀሳቀስ ገልጿል፡፡
ፓርቲው በትናንትናው እለት በሠጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፤መሬት በመንግስት ቁጥጥር ስር መዋሉን በመቃወም የፖሊሲ ለውጥ እንዲደረግ ጫና ለመፍጠር፣ አዲስ አበባን ጨምሮ በተመረጡ 14 የክልል ከተሞች ህዝባዊ ስብሠባ የሚያካሂድ ሲሆን ስብሠባዎቹ በደሴ እና በድጋሚ በአዲስ አበባ የሚደረግ ሲሆን በየ15 ቀን ልዩነት በሃዋሣ፣ አዳማ፣ ለገጣፎ፣ መቀሌ፣ ደብረታቦር፣ ደብረ ማርቆስ፣ ድሬዳዋ፣ ጂንካ፣ ቁጫ፣ አሶሣ፣ ነቀምት እና ጋምቤላ ከተካሄደ በኋላ አዲስ አበባ ላይ በሚደረግ
ሙሉውን አንብብ-Read More

The art of ancient writing

Geez Bet | Monday, March 10, 2014
The Nephilim were offspring of the “sons of God” and the “daughters of men”. According to records, with the fall of the Watchers, the angels who fathered the Nephilim, a phenomenon was created in the world.  
“They became pregnant, and they bore great giants, whose height was 35 meters and who consumed all the acquisitions of men. And when men could no longer sustain them, the giants turned against them and devoured humankind”. This text was taken from the book of Enoch (Metshafe Henock), an ancient scripture believed to be translated into the local language during the Axumite period, part of Ethiopia's ancient treasures.

The book was a contribution by ancient brana (parchment) writers who wanted Ethiopians to know the mystery behind the fallen angles. It is not only this but books which talk about the cosmos and various planets such as Atard (mercury), Zohal (Venus), Mers (Mars), a design of rocket, the stars, the existence of the immortal people, the mis-creatures of the world, the
ሙሉውን አንብብ-Read More

Mar 5, 2014

የዩክሬን ቀውስ፣ የአውሮፓ ህብረትና የሩስያ ግንኙነት

Geez Bet | Wednesday, March 05, 2014
ትናንት ብራሰልስ ቤልጅየም የተሰበሰቡት የአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ሩስያ ጦሯን ከዩክሬን ካላስወጣች ከሩስያ ጋር የተጀመረው ንግግር እንደሚቋረጥ እንዲሁም ማዕቀቦች እንደሚጣሉባት አስጠንቅቀዋል ። 
«አውሮፓ የበርሊኑ ግንብ ከፈረሰ ወዲህ ያለ አንዳች ጥርጥር እጅግ ከባድ ቀውስ ውስጥ ትገኛለች ። ቀዝቃዛው ጦርነት ካበቃ ከ25 ዓመት በኋላ የአውሮፓ አዲስ የመከፋፈል አደጋ እውን ሆኗል » የጀርመን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፍራንክ ቫልተር ሽታይንማየር ትናንት በዩክሬን ቀውስ ላይ የተነጋገረው የአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አስቸኳይ ስብሰባ ከመጀመሩ አስቀድሞ የሰጡት አስተያየት ነበር ። በርግጥም ሽታይናማየር እንዳሉት አውሮፓ ከባድ ችግር ውስጥ ነው ያለችው ። በአንድ በኩል በእጇ
ሙሉውን አንብብ-Read More