Time in Ethiopia:

Dec 28, 2013

የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የደብር ሃላፊዎችና ሠራተኞች አዲሱን መዋቅር ተቃወሙ

Geez Bet | Saturday, December 28, 2013
“ዲግሪ ያላቸው በየአስተዳደሩ እንዲገቡ መደረጉ አግባብ አይደለም” በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የአዲስ አበባ ሃገረ ስብከት፣ ካለፈው ህዳር ወር ጀምሮ እያካሄደ ያለውን አዲስ
የመተዳደሪያ ደንብ የማፅደቅ ሂደት እና መዋቅራዊ ለውጥ አጥብቀው እንደሚቃወሙ የሃገረ ስብከቱ የአድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎችና ሠራተኞች ለቅዱስ ፓትሪያርኩና ለጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት አስታወቁ፡፡ ቅሬታ አቅራቢዎቹ ለፅ/ቤቶቹ ባስገቡት ደብዳቤ፤ የሃገረ ስብከቱ አዲስ መተዳደሪያ ደንብ ሁሉም የቤተክርስቲያኒቱ ሊቃውንት ሳይሳተፉበት በጥቂት አመራሮች
ሙሉውን አንብብ-Read More

ካልተሳፈርኩ” ብሎ የታክሲ ሹፌሩን በሽጉጥ ገደለ

Geez Bet | Saturday, December 28, 2013
  መገናኛ አካባቢ ወደ ጉርድ ሾላ በሚወስደው መስመር፣ አንድ መንገደኛ ትናንት ከምሽቱ 12 ሰዓት ላይ ሚኒባስ ታክሲ ውስጥ ካልተሳፈርኩ ብሎ ሾፌሩን ወንደሰን ደምሴን በሽጉጥ ገደለ፡፡ “ታክሲው
ውስጥ ካልተሳፈርኩ፣ አትሳፈርም” በሚል በተነሳው ጭቅጭቅ፣ ሾፌሩን ገድሏል የተባለውን ደጀኔ ገመቹ በቁጥጥር ስር እንደዋለ የገለፀው ፖሊስ፤ የአይን ምስክሮችን ቃል በመቀበል ምርመራ እያካሄደ ነው፡፡ ታክሲ እየጠበቁ የነበሩ የአይን ምስክሮች በወቅቱ አቶ ደጀኔ እጁን በማወዛወዝ ሚኒባስ ታክሲውን እንዳስቆመ ተናግረው፣ ከሾፌሩ ጋር ጭቅጭቅ እንደተፈጠረ
ሙሉውን አንብብ-Read More

Dec 26, 2013

ኢትዮጵያ ከግብፅ ጋር የተስማማችባቸውና ያልተስማማችባቸው ነጥቦች ይፋ ተደረጉ

Geez Bet | Thursday, December 26, 2013
ግብፅ የቅኝ ግዛት የውኃ ኮታዋ እንዲከበር አሁንም ጠይቃለች
•ለመስማማት የገባችውን ቃል አፍርሳለች
የውኃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር የህዳሴውን ግድብ ግንባታ በተመለከተ ከግብፅና ከሱዳን መንግሥታት ጋር እያደረገ የሚገኘውን ድርድር ውጤት አስታወቀ፡፡ የግብፅ መንግሥት ያቀረባቸው የግዴታ ሐሳቦች በኢትዮጵያ በኩል ተቀባይነት አላገኙም፡፡ 

የውኃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከግብፅና ከሱዳን አቻ ሚኒስቴሮች ጋር በህዳሴው ግድብ ላይ እያደረጋቸው የሚገኙ ድርድሮችን ማክሰኞ ዕለት ለባለድርሻ አካላትና ለመገናኛ ብዙኃን ሲያሳውቅ፣ ኢትዮጵያ ከግብፅ ጋር የተስማማችባቸውንና ያልተስማማችባቸውን ነጥቦች ይፋ አድርጓል፡፡ 
በሚኒስቴሩ የድንበር ተሻጋሪ ወንዞች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ፈቅ አህመድ ባቀረቡት ጽሑፍ፣ ሚኒስቴሩና ብሔራዊ የባለሙያዎች ቡድን ሥልታዊና የተጠና እንቅስቃሴ ሱዳን ከኢትዮጵያ ጐን እንድትቆም ማስቻሉን ገልጸዋል፡፡
ዓለም አቀፍ የባለሙያዎች ቡድን ባለፈው ዓመት መጨረሻ
ሙሉውን አንብብ-Read More

Dec 25, 2013

አነጋጋሪው የማንዴላ ወታደራዊ ስልጠና

Geez Bet | Wednesday, December 25, 2013
    ከ 4 ዓመት ገደማ በፊት፤ ወደ ኢትዮጵያ የተጓዙ አንድ የኔልሰን ማንዴላ ድርጅት ዋና ተመራማሪ፤ ማንዴላን በማሠልጠን ያገዙ በሕይወት የሚገኙ ሰዎችን ሁሉ ጠይቀው ያሰባሰቡት መረጃ ፣ ማንዴላ ከእሥራኤላውያን ጋር ግንኑነት እንደነበራቸው የሚያረጋግጥ አንዳችም እውነታ አልተገኘበትም። 
     ማንዴላን የጨበጣ ውጊያ ፣ የጦር መሣሪያ፣ አፈታትና አገጣጠም ፤ የቦንብ አጠቃቀምና የመሳሰለውን ያሰለጠኗቸው ኢትዮጵያ ውስጥ የነበሩ የእሥራኤል የስለላ ድርጅት(ሞሳድ) ሠራተኞች ናቸው ሲል «ሐዓሬትዝ» የተሰኘ በእስራኤል የሚታተም ጋዜጣ አስነብቧል። ይሁን እንጂ የኔልሰን ማንዴላ ድርጅት፤ በሰጠው መግለጫ፤ ከማንዴላ የግል ማኅደርም ሆነ ከሌላ ይህን ዜና የሚያረጋጋጥ አንዳች ፍንጭ እንደሌለ
ሙሉውን አንብብ-Read More

Dec 24, 2013

ደቡብ ሱዳን፤ ከጦርነት ወደ ጦርነት

Geez Bet | Tuesday, December 24, 2013
ከፖለቲካ ዲፕሎማሲዉ ይልቅ፥ ጠመንጃ ጦርነትን ያደጉ የኖሩበት ሳልቫ ኪር የዲንካን፥ እንደ ፖለቲከኛ-ሻጥርን፥ እንደ ዲፕሎማት ግድምድሞሽ ዘይቤን፥ እንደ ታጋይ የጫካ ዉጊያ አጣምረዉ የያዙት ዶክተር ሪክ ማቼር የኑዌር ጎሳን፥ ከየጎናቸዉ አሰልፈዉ ተፋጠዋል። 
 ዛሬ-ስምት ዓመት በዚሕ ወቅት ግድም የረጅም ጊዜዉ ጦርነት፥ የሚሊዮኖች እልቂት ፍጅት ስደት አበቃለት ተባለ።የዛሬ-ሰወስት ዓመት በዚሕ ወቅት ግድም ሕዝቧ በነፃ ዉሳኔዉ ነፃነትዋን ማስፀደቁ ተነገረ። የዓለም ፖለቲከኞች መሠከሩለትም።ደቡብ ሱዳን።ሐምሌ-ሁለት ሺሕ አስራ-አንድ (ዘመኑ በሙሉ እንደ ጎርጎሮሳዉያኑ አቆጣጠር ነዉ) ነፃነቷ ታወጀ።ፌስታ።

ወዲያዉ ግን ግጭት። ደግሞ ጦርነት።ዛሬም ጦርነት ላይ ናት።አዲስ ሐገር፥ ግራ አጋቢ ምድር።እንዴት ለምን? ላፍታ አብረን እንጠይቅ።
አምና ነዉ።መስከረም።አዲሲቱን አፍሪቃዊት ሐገር ካሮጌ እልቂት ፎጅቷ ለመድፈቅ፧ አዳዲስ ጄኔራሎቿ የጀመሩት አመፅ፣ የአሮጌ ፖለቲከኞችዋን ነባር ሸኩቻ፤ የነባር ጎሶችዋን አሮጌ ግጭት ባዲስ መልክ አንሮታል።እንደ የበላይ የበታቾቻዉ ሁሉ በዉጊያ፣ አመፅ፣ ሽኩቻ፣ የኖሩት የያኔዉ የሐገሪቱ ምክትል ፕሬዝዳንት ሪክ ማቼር ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ኒዮርክ የገቡት አዲሱ አመፅ፣ ሽኩቻ ግጭት ከኖሩበትና ከዘወሩት ብዙ ብጤዉ እንደማይከፋ እያሰላሰሉ ነበር።
ማቼር ከጉባኤዉ አዳራሽ ሲደርሱ ካገጠሟቸዉ ጋዜጠኞች ቢያንስ አንዱ የአዲሲቱ ሐገራቸዉን አዲስ ቀዉስ ምናልባትም የራሳቸዉንም ቅሬታ በቅጡ የሚያዉቅ ሳይሆን አይቅርም። «መንግሥትዎን መፈንቅለ መንግሥት ያሰጋዋል ይባላል» ብሎ ጠየቃቸዉ።ጥያቄዉ ያሰቡትን-ወይም ያለሰቡትን የሚያሳስብ ሊሆን፥ ላይሆንም ይችላል።መልሳቸዉ ግን «በፍፁም» የሚል ነበር።
እንዲሕ አይነት እርምጃ «ጅልነት» አሉ-አሉ አንጋፋዉ የነፃነት ታጋይ፥ «አዲሱን መንግሥት በአመፅ መጀመር አንፈልግም።» አከሉ፥-የአዲሲቱ ሐገር የያኔ ትልቅ ሹም።አሁንም አምና ነዉ።ግን ሐምሌ። ኪር እና ማቸር በየልባቸዉ የሚያስቡ፥ የሚያሰላስሉትን ከነሱ በስተቀር በግልፅ የሚያዉቅ-ከነበረ ቢያንስ አስካሁን በግልፅ አይታወቅም።

ሁለቱም ሁለት ዓመት እንደኖሩበት የመጀመሪያዉ እንደ ፕሬዝዳት፥ ሁለተኛዉ እንደ ምክትል ፕሬዝዳት በዓሉን አከበሩ።የነፃነት በዓል-ሁለተኛ ዓመት። ወዲያዉ ግን የመጀመሪያዉ ከሥልጣን አባራሪ፥ ሁለተኛዉ ተባባራሪ ሆኑ።

«አሁን የአንድ ሰዉ አገዛዝ ነዉ ያለን።ያንድ አገዛዝ ምን ማለት ነዉ።አምገነንነት።»
የቀድሞዉ ምክትል ፕሬዝዳት ሪክ ማቸር።ከሥልጣን በተባረሩ ማግሥት።ሐምሌ።ደቡብ ሱዳን፥ የሚነገር አይሆንባትም፥ የታቀደ አይፈፀምባትም፥የተነገረ-አይታመንባትም።ወይም የሚነገር፥ የሚባል፥ የሚታቀደዉ ከነባር እዉነቷ፥ከአቅም ማንነቷ ጋር ይጣረሱባታል።ማቼርም አምና መስከረም እንደ ምክትል ፕሬዝዳት ኒዮርክ ላይ የተቃወሙትን፥ባለፈዉ ሳምንት ለዕሁድ አጥቢያ ጁባ ላይ አደረጉት።መፈንቅለ መንግሥት።ከሸፈ።መዘዙ ግን ዛሬም አላባራም።
ፕሬዝዳት ሳልቫ ኪር የመላዉ ሱዳንን የምክትል ፕሬዝዳትነት ሥልጣን ከጆን ጋራግ ከወረሱበት ጊዜ ጀምሮ አደባባይ ሲወጡ አሜሪካኖች «የእረኛ» የሚሉት ሠፊ-ክብ ባርኔጣ ካናታቸዉ ተለይቶ አያዉቅም።ይወዱታል።ባርኔጣዉ በሚዘወተርበት ቴክስሳ ግዛት ያደጉ-የሚኖሩት የቀድሞዉ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳት ጆርጅ ደብሊዉ ቡሽ ለሳልቫ ኪር የሸለሟቸዉም ይሕኑ ባርኔጣ ነበር።
ዕሁድ ግን ባርኔጣቸዉን አዉልቀዉ፥ ሱፍ ከረባትታቸዉን በጄኔራል ማዕረግ በተንቆጠቆጠ የዉጊያ ልብስ ቀይረዉ ከጦር ሜዳ እንደተመለሰ ጄኔራል እያጉረጠረጡ ከቴሌቪዥን ካሜራ ፊት ብቅ አሉ።
እርግጥ ነዉ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራዉ ከሽፏል።የአዲሲቱ ሐገር እዉነታ ግን ፕሬዝዳንቷ ካሉት ተቃራኒዉ ነዉ።ራሷ ጁባ፥ ቦር፥ ጃንጌሌይ፥ ዩኒቱ ከተሞች እና ግዛቶች ዛሬም በሳምንቱ በዉጊያ ይርዳሉ።የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ ፓን ጊሙን ይሕን መሠከሩ።
«እያሽቆለቆለ የመጣዉ የደቡብ ሱዳን የፀጥታ ሁኔታ በጣም አሳስቦኛል።ሁሉም የፖለቲካ፥ የጦር እና የሚሊሺያ ሐይላት መሪዎች ሰላማዊ ሰዎችን የሚጎዳዉን ጠብ፥ ግጭታቸዉን እንዲያቆሙ እጠይቃለሁ።»የሰማቸዉ እንጂ ቢያንስ እስካሁን የተቀበላቸዉ የለም።ጥንት በዚያ ግዛት እንዲያ ነበር።ድሮም።የዛሬ ስምንት ዓመትም እንዲሁ።ጥር ዘጠኝ።ሁለት ሺሕ አምስት።ናይሮቢ።
«ወገኖቼ፥ የሐገሬ ወንዶችና ሴቶች ሆይ! እንኳን ደስ አላችሁ።ደስታም በናንተ ላይ ይሁን። ንቅናቄያችሁ SPLM/SPLA እና የብሔራዊ ምክር ቤት መንግሥት አጠቃላይ የሠላም ስምምነት ተፈራርመዉላችኋል።ዛሬ የፈረምነዉና እናንተ ያችሁትን ፍትሐዊ እና የተከበረ የሠላም ዉል አቅርበንላችኋል።በዚሕ የሠላም ዉል መሠረት ከአፍሪቃ ረጅሙን ጦርነት አቁመናል።»
የቀድሞዉ የደቡብ ሱዳን ነፃ አዉጪ ጦርና ንቅናቄ መሪ ዶክተር ጆን ጋራንግ።ጋራንግ እንዳሉት ትልቂቱ አፍሪቃዊት ሐገር በ1956 ነፃ ከወጣችበት ጊዜ ጀምሮ ከጥቂት ዓመታት ፋታ በስተቀር ጦርነት ተለይቷት አያዉቅም።ስምንቱ ሚሊዮኖችን የፈጀዉ፥ ከአራት ሚሊዮን በላይ ያሰደደዉን፥ ሰላሳ-ዘጠኝ ዓመታት ያስቆጠረዉን ጦርነት ማስቆሙ እርግጥ ነዉ።ከወጣትነት ዘመናቸዉ ጀምሮ ለአርባ ዓመታት ያኽል ያን ጦርነት ባንድ ወይም በሌላ መልኩ ሲዘዉሩ የነበሩት ጆንጋራንግ ያን ስምምነት ሲያበስሩ ዘግናኙ ጦርነት መቆሙን ብቻ ሳይሆን ሌላ ብጤዉ እንደማይከሰትም እርግጠኛ ነበሩ።ወይም ላዳመጣቸዉ መስለዉ ነበር።
«በዚሕ ሥምምነት መሠረት ከእንግዲሕ በየዋሕ ሕፃናትና እናቶች ላይ ከሠማይ የሚወርድ ቦምብ አይኖርም።ከእንግዲሕ ሕፃናት በደስታ የሚቦርቁበት፥ ባንድ ወይም በሌላ መልኩ ደስታቸዉን የተቀሙ እናቶች በእልልታ የሚደሰቱበት ሠላም ይሠፍናል።»«የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በርግጥ ከአቅሙ በላይ ተወጥሯል።እዚሕ ያለ ማንም ቢሆን የተለመደዉን ሠብአዊ ርዳታ ለማቀበል ነበር የተዘጋጀዉ።ጁባ ዉስጥም ሆነ በክፍለ ግዛቶች አሁን የተፈጠረዉ ቀዉስ ይፈጠራል ብሎ ማንም ሰዉ አልጠበቀም።»ከኑዌር የሚወለዱት ሪክ ማቼር እንደመሩት በሚታመነዉ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራና ሙከራዉን ባከሸፈዉ በፕሬዝዳት ሲልቫ ኪር ታማኞች መካካል ጁባ ዉስጥ ብቻ በተደረገዉ ዉጊያ ስድስት መቶ ሰዎች ተገድለዋል።በሌሎች ከተሞችና ክፍለ ግዛቶች በተደረገና በሚደረገዉ ዉጊያ የሞተ-የተሰደደ፥ የተፈናቀለዉን በትክክል የቆጠረዉ የለም።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እንዳስታወቀዉ ጁባ እና ቦር በሚገኙ ሰወስት ቅጥር ግቢዎቹ ብቻ ከሠላሳ-አምስት ሺሕ በላይ ሕዝብ ተጠልሏል።ምዕራባዉያን ሐገራት ዜጎቻቸዉን ከምስቅልቅሊቱ ሐገር ማሸሹን ነዉ-ያስቀደሙት።ከዋና ፀሐፊ ፓን ጊ ሙን እስከ ፕሬዝዳት ባራክ ኦባማ ያሉ መሪዎች ተፋላሚ ሐይላት ከተጨማሪ ጦርነት ታቅበዉ ልዩነታቸዉን በሰላም እንዲፈቱ መጠየቅ-፥ ማሰሰባቸዉ አልቀረም።«የደቡብ ሱዳን መንግሥት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ለመደራደር ዝግጁ ነዉ።የምሥራቅ አፍሪቃ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትሮች ለድርድር የሚያስፈልጋቸዉን መረጃ ብቻ ሳይሆን ለጀመሩት ጥረት የደቡብ ሱዳን መንግሥትን ሙሉ ዉክልናም አግኝተዋል።»
ከኑዌር የሚወለዱት እዉቅ ጄኔራል ፔተር ጋዴት፥በቅርቡ ከዩኒቲ ግዛት አስተዳዳሪነት የተሻሩት ታባን ዴንግ ጋይ፥ ከባሪ የሚወለዱት የቀድሞዉ ሚንስትርና ጄኔራል አልፍሬድ ላዱ ጎር፥የአናሳዉ የመርል ጎሳ አባል የሆኑት ዴቪድ ያዩ፥ እና በርስበርሱ ጦርነት ወቅት «ነጩ ጦር» በመባል የሚታወቀዉ ሚሊሺያ ሐይል ሁሉም እንደ ጋራ ጠላት በሚያዩት በሳልቫ ኪር መንግሥት ላይ ጠመንጃቸዉን አነጣጥረዋል።ይተኩሳሉም።
«ከቀድሞዉ ምክትል ፕሬዝዳት ከዶክተር ሪክ ማቼር እና ከቡድናቸዉ ጋር የሚተባበሩ ወታደሮች ጁባ ዩኒቨርስቲ አጠገብ በሚገኘዉ በSPLA ዋና ፅሕፈት ቤት ላይ ጥቃት ፈፅመዋል።ጥቃቱ እስከ ዛሬ ጠዋት ድረስ ቀጥሎ ነበር።ይሁንና ለዜጎቼ በሙሉ፥ መንግሥታችሁ ጁባ ያለዉን የፀጥታ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሩን ማሳወቅ እፈልጋለሁ።»

ተናገሩ።አልበሽር (የሰሜን ሱዳን ፕሬዝዳንት) ቦምብ የሚባለዉን ቃል ሲሰሙ ፈገግ አሉ። ጆንግ ጋራንግ የሠላም ስምምነቱን ዉጤት ለማየት፥ የሐራቸዉን ነፃነት ለመመልከት አልታደሉም።ከአርባ ዘመን ጦርነት አምልጠዉ በቅፅበት የሔሊኮብተር አደጋ-ሞቱ።ጋራንግ እንዳሉት እኒያ የሰሜን ሱዳን አዉሮፕላኖች የሚያወርዱት ቦምብ ከሁለት ሺሕ አምስት በኋላ ቆሟል።ደቡብ ሱዳን ግን ሠላም ሆና አለማወቋ እንጂ ቁጭቱ።
የጁባ ነዋሪዎች
በነፃነትዋ ዋዜማ ኮርዶፋን ግዛት ለተደረገዉ ጦርነት ሰሜን ሱዳኖችን መዉቀስ፥ መወነጅሉ፥ ለዛሬዎቹ የጁባ ገዚዎችም፥ ለምዕራባዉያን ደጋፊዎቻቸዉም ቀላል ነበር።አምና መጋቢት ሒጂሊጅ እና አካባቢዉን ያጋየዉን ዉጊያ የቆሰቆሱት ሳል ቫኪር መሆናቸዉ አለጠያየቅም፥ ጦርነቱ የቆመዉ ግን ሐያሉ ዓለም አልበሽርን አዉግዞ አስጠንቅቆ፥ ኪርን ካባበለ በኋላ ነበር።


ደቡብ ሱዳን እስከ ዛሬም ከአስሩ ግዛቶችዋ ዘጠኙ በእርስ በርስ ጦርነት፥በጎሳ ግጭትና ቁርቁስ እንደተመሠቃቀሉ ነዉ።እና ሰሜን ሱዳኖች የሚያወርዱት ቦምብ በርግጥ የለም።የደቡብ ሱዳን ሕዝብ ግን ዛሬም እንደተገደለ፥ እንደ ቆሰለ፥ እንደተሰደደ፥ እንደተራበ ነዉ።የሳልቫ ኪርን አገዛዝ እና የሳልቫ ኪር ጎሳ የዲንካን የበላይነት በመቃወም በየሥፍራዉ ያመፁት ሰባት የተለያዩ ቡድናት ከመንግሥት ጦር እና እርስር በርስ በሚያደርጉት ዉጊያ በብዙ ሺሕ የሚቆጠር ሕዝብ ተገድሏል።በብዙ ሺሕ የሚቆጠር ተፈናቅሏል።ወይም ተሰዷል።
አሁን ደግሞ መፈንቅለ መንግሥትና መዘዙ ያንመከረኛ ሕዝብ ከዳግም እልቂት፥ ስደት፥ ዶሎታል። አምና መስከረም ጋዜጠኛዉ ማቸርን ሥለመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ የጠየቀዉ፥ የሐገሪቱን የፖለቲካ ዉጥንቅጥ፥ የጎሳ ጠብ፥ ቁርቁስን ሥላወቀ፥ ወይም ሥለገመተ እንጂ-ነብይነት ቃጥቶት አልነበረም።
በጁባ የዩናይትድ ስቴትስዋ አምባሳደር ሱዛን ፔጅ በቀደም እንዳሉት ግን የሆነዉ እንደሚሆን ማወቅ አይደለም የጋዜጠኛዉን ያሕል እንኳን አልገመቱም ነበር።ማንም አልጠበቀም ይላሉ በጁባ የልዕለ ሐያሊቱ ሐገር ዲፕሎማት።ደቡብ ሱዳን፥ የሚባል አይደረግባትም።ከፖለቲካ ዲፕሎማሲዉ ይልቅ፥ ጠመንጃ ጦርነትን ያደጉ የኖሩበት ሳልቫ ኪር የዲንካን፥ እንደ ፖለቲከኛ-ሻጥርን፥ እንደ ዲፕሎማት ግድምድሞሽ ዘይቤን፥ እንደ ታጋይ የጫካ ዉጊያ አጣምረዉ የያዙት ዶክተር ሪክ ማቼር የኑዌር ጎሳን፥ ከየጎናቸዉ አሰልፈዉ ተፋጠዋል።የዚያች ሐገር አበሳ-በሁለቱ ታዋቂ ፖለቲከኞችዋ ጠብ፥ ግጭት አለማብቃቱ ነዉ ክፋቱ።

የኢትዮጵያን ጨምሮ የአካባቢዉ ሐገራት ዉጪ ጉዳይ ሚንስትሮች ጠብ፥ ግጭት፥ ጦርነቱን በሰላም ለመፍታት ባለፈዉ ሳምንት የጀመሩት የድርድር ጥረት ፍሬማ ዉጤት ማሳየቱን ጠቁመዋል።የደቡብ ሱዳኑ ማስታወቂያ ሚንስትር ሚካኤል ማኩይ በፋንታቸዉ መንግሥታቸዉ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ለመደራደር ዝግጁ መሆኑን አስታዉቀዋል።

ከምሥራቅ አፍሪቃ ሐገራት መካካል ዩጋንዳ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትሯን ብቻ ሳይሆን ጦሯንም ነዉ-ጁባ ያዘመተችዉ።የሠላም፥ ዲፕሎማሲና የዉጊያ ዘመቻ!! «የደቡብ ሱዳን ማስታወቂያ ሚንስትር መንግሥታቸዉ «ያለ ቅድመ ሁኔታ ለመደራደር መዘጋጀቱን ሲገልፁ፥የሐገሪቱ የጦር አዛዦች ባንፃሩ አማፂያኑ የሚቆጣጠሩትን ቦርን መልሶ የሚይዝ ጦር እያዘመቱ መሆናቸዉን አስታዉቀዋል።

አል በሽር አሁንስ ይፈግጉ ይሆን? ደቡብ ሱዳንስ ወዴት፥ እንዴት ትጓዝ ይሆን? ሥለ ማሕደረ ዜና ያላችሁን አስተያየት፥ ማሕደረ ዜና ቢቃኘዉ ጥሩ ነዉ የምትሉትን ጥቆማ በደብዳቤ፥ በስልክ፥ በፌስ ቡክ፥ በኢሜይል፥ በኤስ ኤም ኤስ ላኩልን።እስካሁን አስተያየት ጥቆማ የሰጣችሁኝን አመሰግናለሁ። ነጋሽ መሐመድ ነኝ ቸር ያሰማን።
ነጋሽ መሐመድ
ኂሩት መለሰ
Source: www.dw.de 

ሙሉውን አንብብ-Read More

Dec 23, 2013

የ2013 የአፍሪቃ ዓበይት ክንውኖች

Geez Bet | Monday, December 23, 2013
ሊያበቃ ጥቂት ቀናት የቀረው 2013 ዓም በአፍሪቃ በፖለቲካው እና በማህበራዊው ዘርፎች ከታዩት ዓበይት ክንውኖች ጥቂቱ ባጭሩ ይቃኛል። 
እአአ መጋቢት አምስት፣ 2013 ዓም ኬንያ ውስጥ የአጠቃላዩ ምርጫ ቀን ነበር። ብዙ ሕዝብ ነበር ድምፁን ለመስጠት የወጣው። በተፎካካሪዎቹ ኡሁሩ ኬንያታ እና በቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር ራይላ ኦዲንጋ ደጋፊዎቹ ጎራ ውስጥ ከፍተኛ ውጥረት ነበር የታየው። በምርጫው ኡሁሩ ኬንያታ አሸናፊ ቢሆኑም፣ ድላቸው አካራካሪ ነበር፣ ምክንያቱም፣ ከአምስት ዓመት በፊት እኢአ በ2007 ዓም የተካሄደው ምርጫ ውጤት ይፋ ከሆነ በኋላ በተከተሉት ወራት በሀገሪቱ የ 1,200 ሰዎች ሕይወት የጠፋበትን ግጭት ቀስቅሰዋል በሚል ብዙዎች የሚወቅሱዋቸው ኬንያታ እና በምርጫው ዘመቻ ወቅት
ሙሉውን አንብብ-Read More

Dec 21, 2013

ዶክተር አምሳሉ አክሊሉ ዐረፉ

Geez Bet | Saturday, December 21, 2013
አብዛኞቻችን የመዝገበ ቃላትን አጠቃቀም የተማርንበትንእንግሊዝኛ -አማርኛ መዝገበ ቃላት››
ያዘጋጁት ዶክተር አምሳሉ አክሊሉ 83 ዓመታቸው ታኅሣሥ 11 ቀን 2006 ዓም ዛሬ ዐረፉ፡፡ ዶክተር አምሳሉ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ከሚባልበት ዘመን ጀምሮ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ያስተማሩ መምህር ነበሩ፡፡
Source: http://www.danielkibret.com/
ሙሉውን አንብብ-Read More

የደቡብ ሱዳን የሥልጣን ሽኩቻ መዘዝ፣

Geez Bet | Saturday, December 21, 2013
የሰሜን ሱዳን የፖለቲካ ተጽእኖና ፤ የዐረብ ባህል ጫና አንገሽግሾት 22 ዓመታት መሪር ትግል ያካሄደው የደቡብ ሱዳን ህዝብ፤ ነጻነት ባወጀ በ 2 ዓመት ከመንፈቅ ገደማ ወደ አስከፊ የእርስ በርስ ውጊያ እንዳያመራ አሥግቷል። ባለፈው እሁድ በመዲናይቱ 
በጁባ ያገረሸው ውጊያ ፣ የ 500 ያህል ሰዎችን ሕይወት ቀጥፎ ፤ 34,000 ሰዎች፤ በተባበሩት መንግሥታት ጣቢያዎች መጠለያ እንዲሻ አስገድዷል ። የሥልጣን መቀናቀን ነው የተባለለት ውዝግብ ፣ በጎሣ ልዩነት ተካሮ ባፋጣኝ ወደሌሎች አካባቢዎች መዛመቱ የሚታወስ ነው። ጉዳዩ ያሳሰባቸው የምሥራቅ አፍሪቃ በይነ መንግሥታት ሚንስትሮች ፤ የአፍሪቃ ኅብረትና የተባበሩት መንግሥታት ተወካዮች ጁባ ውስጥ ከሀገሪቱ ፕሬዚዳንት
ሙሉውን አንብብ-Read More

Dec 20, 2013

ደቡብ ሱዳን ዉጊያና የሠላም ጥረት

Geez Bet | Friday, December 20, 2013
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እንደሚለዉ ፕሬዝዳት ኪየር የሚወለዱበት የዲንካ እና ማቼር የሚወለዱበት የኑዌር ጎሳዎች መልክ እና ባሕሪ የያዘዉ ዉጊያ ፈጣን መፍትሔ ካላገኘ አደገኛ ነዉ።ደቡብ ሱዳን፥ ነፃነት ያወጀችበትን ሁለተኛ ዓመት-ከመንፈቅ፥ ከረጅም ጦርነት የተላቀቀችበትን ሥምንተኛ ዓመት፥ እነሆ በጦርነት ልታከብር ዉጊያ ጀምራለች።
የደቡብ ሱዳን መንግሥት ጦር እና በመንግሥት ላይ ያመፁት ሐይላት ወታደሮች ባለፈዉ ዕሁድ ርዕሠ-ከተማ ጁባ ዉስጥ የጀመሩት ዉጊያ ወደ ሌሎች የሐገሪቱ አካባቢዎች እየተዛመተ ነዉ።የቀድሞዉ ምክትል ፕሬዝዳት የሪክ ማቼር ታማኞች የተባሉት ሐይላት ዛሬ ቦር የተባለችዉን ከተማ ተቆጣጥረዋል።በሌሎች አካባቢዎችም ዉጊያዉ መቀስቀሱ ተዘግቧል።የዉጪ መንግሥታት ዜጎቻቸዉን ከአዲሲቱ ሐገር እያሰወጡ ነዉ።ለግጭቱ ሠላማዊ መፍትሔ ለማፈላለግ ኢትዮጵያን ጨምሮ አራት የአካባቢዉ ሐገራት ዉጪ ጉዳይ ሚንስትሮቻቸዉን ወደ ጁባ ልከዋል።ነጋሽ መሐመድ አጭር ዘገባ አለዉ።
ሙሉውን አንብብ-Read More

Dec 19, 2013

ዓመታዊው የጋዜጠኞችን ፍዳ የዳሰሰው መግለጫ

Geez Bet | Thursday, December 19, 2013
በፓሪስና በኒው ዮርክ የሚገኙት ፣ ድንበር አያግዴው የጋዜጠኞች ድርጅት (RSF) እና ለጋዜጠኞች ህልውናና መብት ተሟጋቹ ፤ (CPJ)፣ በዓለም ዙሪያ የጋዜጠኞችን ፍዳ የሚዘረዝረውን ዓመታዊ መግለጫቸውን ይፋ አደረጉ። ለመገባደድ 2 ሳምንት ገደማ በቀረው 2013 ጎርጎሪዮሳዊው ዓመት
ውስጥ 71 ጋዜጠኞች መገደላቸውናና 178 በእሥራት በመማቀቅ ላይ እንደሚገኙ የወጣው ዘገባ ያስረዳል። ጋዜጠኞችን አሥሮ በማሠቃየት ከተወቁት 10 ሃገራት መካከል፤ ኤርትራ ፣ ኢትዮጵያ፤ግብፅ ፣ ቪየትናም፤ ሶሪያ ፤ አዘርባጃንና ዑዝቤኪስታን ይገኙበታል። በአፍሪቃው ቀንድ የጋዜጠኞችን ይዞታ የሚከታተሉትን ፤ በምሥራቅ አፍሪቃ የ CPJ ን ተጠሪ በማነጋገር ፤ ተከታዩን ዘገባ አቅርበናል።
በሥራ ላይ እንዳሉ ጋዜጠኞች ሕይወታቸውን ያጡባቸው አካባቢዎች ፤ እስያ፤ (24 ናቸው የተገደሉት፤)መካከለኛው ምሥራቅና ሰሜን አፍሪቃ (23) ከሰሐራ ምድረ በዳ በስተደቡብ በሚገኙ የአፍሪቃ ሃገራት አምና 21 እንደተገደሉ ሲታወቅ ዘንድሮ ከሞላ ጎደል በግማሽ ቀንሶ (10) ጋዜጠኞች
ሙሉውን አንብብ-Read More

ደቡብ ሱዳንና የተሰናከለው የዴሞክራሲ ተስፋ

Geez Bet | Thursday, December 19, 2013
የሱዳን ዋና ከተማ ጁባ ከእሁዱ መፈንቅለ መንግሥት ሙከራ በኋላ ዛሬ መረጋጋትዋ ተዘግቧል ። ነዋሪዎች ዛሬ ከቤታቸው መውጣት ጀምረዋል ። አልፎ አልፎ ተኩስ መሰማቱ ግን አልቆመም ። መንግሥት እንዳስታወቀው ከመፈንቅለ መንግሥት ሙከራው ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩ 10 ሰዎችን አስሯል ። 
ተዘግቶ የቆየው የጁባ አውሮፕላን ማረፊያ እንዲከፈት መንግሥት ትዕዛዝ ቢያስተላልፍም አንዳንድ አየር መንገዶች ወደ ጁባ ከመብረራቸው በፊት የፀጥታ ዋስትና ጠይቀዋል ። ዩናይትድ ስቴትስ ዜጎቿን ማስወጣት እንደምትጀምር አስታውቃለች ። በደቡብ ሱዳን የኃይል እርምጃ ማገርሸቱ የሃገሪቱን የዴሞክራሲ ተስፋ እንዳያሰናክል አስግቷል ። በጎሳ የተከፋፈሉ የደቡብ በሱዳን ጦር ሠራዊት አባላት ባለፈው እሁድ ለሊት ጁባ አቅራቢያ ከተታኮሱ በኋላ የተፈጠረውን መንግሥት የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ብሎታል ።
ሙሉውን አንብብ-Read More

Dec 17, 2013

እልፍ አንድ ሺህ ወይስ ዐሥር ሺህ?

Geez Bet | Tuesday, December 17, 2013
:
፩. ምክንያተ ጽሕፈት
ይስማዕከ ወርቁ በቅርብ ጊዜ ባሳተመው ‹ተከርቸም› በሚለው 6ኛ መጽሐፉ ‹እልፍ(፼) ዐሥር ሺህን ሳይኾን አንድ ሺህን ይወክላል› የሚል መከራከሪያ አቅርቧል፡፡ እኔም በመጽሐፉ ያቀረበውን የእልፍ(፼) ቁጥር አስተያየት ከተመለከትኩ በኋላ መስተካከል ያለበት ጉዳይ መስሎ ስለተሰማኝ ይህንን ጽሑፍ በተወሰነ ደረጃ ሞነጫጭሬ አስቀምጨው ነበር፤ በዕንቁ መጽሔት ተጠይቆ የሰጠውን መልስ ከተመለከትኩ በኋላ ግን መከራከሪያ ነጥቦችን ማቅረብ አስፈላጊ መስሎ ታየኝ፡፡
ምክንያቱም በእኔ ዕይታ የይሰማዕከ የ‹እልፍ አንድ ሺህ ነው› ውሳኔያዊ መጣጥፍና አጠቃቀም ሁለት አንድምታዎች አሰምቶኛል፡፡ አንድኛ ከዚህ በፊት የታተሙት የሊቃውንት መጻሕፍት የግዕዝ ቁጥር አጠቃቀም ስህተት መኾን ይጠቁማል፡፡ ይህ አንድምታም  ‹የሀገራችን ሊቃውንት የግዕዝ ቁጥር ዕውቀት የላቸውም› የሚል ትርጓሜንም ያመጣል፡፡ ይህንን ደግሞ ‹እነዚህ ሕዝቦች እስከ ሺህ ድረስ አልቆጠሩም እንደ?› ያስብለናል እና ‹ቀና ሲታጣ ይመለመላል ጎባጣ› የሚሉት የይስማዕከ አገላለጾቹ ምስክር ናቸው፡፡ ስጋቱ ቢገባኝም ‹ከኛ በላይ ያወቀ ቡዳ ነው› ዓይነት አቀራረቡ ግን አስተዋይነት ያለው አልመሰለኝም፡፡ ስለዚህ ጥረቱ መልካም ቢኾንም ያላስተዋላቸው ነጥቦች ስላሉ እንዲያጤናቸው እና ሌሎችም ትክክል መስሏቸው የቁጥር አጠቃቀማችን እንዳያዛቡ በሚል አመለካከት ይህንን አስተያየት አቀረብኩ፡፡
ሙሉውን አንብብ-Read More

የማንዴላ አሰተምሕሮ እና ድሕረ-ማንዴላ

Geez Bet | Tuesday, December 17, 2013
ፍልስጤም-እስራኤሎች፥ ዋሽንግተን፥ ሞስኮዎች፥ ዋሽንግተን፥ ቤጂንግ፥ ዋሽንግተን ቴሕራኖች፥ ዋሽንግተን ሐቫናዎች፥ አስመራ-አዲስ አበቦች፥ ኢሕአዲግ ተቃዋሚዎች፥ ሶማሌዎች፥ ሶሪያዎች፥ ብዙ ናቸዉ። ቁጥራቸዉን መዘርዘሩ ያታክታልም። ከማንዴላ ምግባር ጥቁቱን፥ ከዴክላክ ድፍረት ትንሹን እንኳን ገቢር አለማድረጋቸዉ በርግጥ ያጠያይቃል 
ማንዴላ ተቀበሩ። ታላቁ የነፃነት፣ የእኩልነት አርበኛ ከሞቱበት እስከ ተቀበሩበት ድፍን ዓለም አዘነ፥ ወይም ማዘኑን ገለፀ። ከቄሱ እስከ ሼኩ፥ ከዘማሪዉ እስከ ዘፋኙ፥ ከተዋኙ እስከ ስፖርተኛዉ ለዚያ ታላቅ-ክቡር ሠዉ ታላቅ አድናቆት፥ አክብሮቱን ሲያንቆረቁር ሰነበተ። ከፕሬዝዳት ዙማ-እስከ ፕሬዝደንት ኦቦባ፥ ከጠቅላይ ሚንስትር ኃይለ ማርያም እስከ ጠቅላይ ሚንስትር ካሜሩን የትንሽ ትልቁ ሀገር መሪ የማንዴላን አብነት ለመከተል፥ ዓላማ፥ ራዕይ አስተምሕሯቸዉን ገቢር ለማድረግ ቃል ገባ። ካንጀት-ይሆን ካንገት ማረጋገጪያዉ-በያኙ በርግጥ ምግባር እና ጊዜ ነዉ። ማንዴላ
ሙሉውን አንብብ-Read More

የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ በደቡብ ሱዳን

Geez Bet | Tuesday, December 17, 2013
በደቡብ ሱዳን ትላንት የተሞከረው የመንግስት ግልበጣ መክሸፉን የኣገርቱ መንግስት ኣስታወቀ። በቀድሞው ም/ፕሬዝደንት ማቻር የተመራው የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ የከሸፈው ለፕሬዝደንት ሳልቫኪር ታማኝ የሆኑ ወታደሮች የበላይነትን በማግኘታቸው ነው ተብሏል። 
የቀድሞው የኣገሪቱ ም/ፕሬዝደንት ከስልጣን የተባረሩት ባለፈው ሀምሌ ወር ሲሆን ቅርበት ያላቸው ምንጮች እንደሚሉት ከዚያ ወዲህ በመንግስትም ሆነ በገዚው የSPLM ግንባር መካከል ክፍፍል ተፈጥሯል።
ከእሁድ ቀትር በኃላ ጀምሮ እስከ ዛሬ ማለዳ የዘለቀው የተኩስ ልውውጥ ኣሁን መቆሙን እና በከተማይቱ ጁባ ኣንጻራዊ መረጋጋት መስፈኑን የኣይን እማኞች ይናገራሉ።
በቀድሞው ም/ፕሬዝደንት የሚመሩ ያኮረፉ ወታደሮች እና ፖለቲከኞች በመንግስት ኃይሎች በተለይም በቤተመንግስት የጸጥታ ኃይሎች ላይ የከፈሩት ድንገተኛ ተኩስ ከየኣቅጣጫው
ሙሉውን አንብብ-Read More

Dec 16, 2013

እምዬ ምኒልክ! (ተመስገን ደሳለኝ)

Geez Bet | Monday, December 16, 2013

   ይህንን አጀንዳ ለማቅረብ ያሰብኩት ባለፈው ሳምንት ነበር፤ ይሁንና ‹‹የምስራቅ ኢትዮጵያ ፖለቲካ 2›› የሚለው ፅሁፌ አንድም ወቅቱ ‹‹የብሔር ብሔረሰቦች ቀን›› ዋዜማ በመሆኑ፣ ሁለትም በይደር የተላለፈው የዚሁ ተከታይ ፅሁፍ መቋጨት ግድ በማለቱ ነበር፡፡ እናም ‹ቦ ጊዜ ለኩሉ› እንዲል ጠቢቡ፣ የዘገየው አጀንዳችን የዕውቁ ደቡብ አፍሪካዊው የፀረ አፓርታይድ ትግል መሪ ኒልሰን ማንዴላን ህልፈት ተከትሎ ዓለም ‹በተሳሳተ የታሪክ ወንዝ› ከመፍሰሱ ጋር ተነፃፅሮ ይቀርብ ዘንድ ገፊ ምክንያት ሆኗል፡፡ በርግጥ የአጀንዳው ተጠየቅ ማንዴላን አኮስሶ፣ ዳግማዊ አፄ ምኒልክን ማወደስ አይደለም፤ ንጉሡን ያገለለውን ጨካኝ የታሪክ ፍርድ መሞገት እንጂ፤ በአናቱም ከውስጥ ጉዳይ ጋር ተያይዞ ዘመን የተሻገረ ቂም የሀገር ባለውለታን ታሪክ ማደብዘዙን መተቸት ነው፡፡
‹ምኒሊክ ተወልዶ ባያነሳ ጋሻ›
ከአማራና ኦሮሞ ፊውዳል ቤተሰብ እንደተወለደ በህይወት ታሪኩ ዙሪያ የተሰናዱ ድርሳናት የሚያወሱለት ምኒሊክ፣ ንጉሠ ነገሥት አፄ ዮሐንስ 4ኛ በ1882 ዓ.ም. ከ‹ማሀዲስቶች› (ሱዳናውያን ያቀጣጠሉት የነፃነት ንቅናቄ መጠሪያ ነው) ጋር በተደረገ ጦርነት መሰዋቱን ተከትሎ ነው ወደ ንግስናው የመጣው፤ ሆኖም ዘውድ ከመጫኑ በፊት፣ በአፄ ዮሐንስ ስር ሆኖ የሸዋና ወሎ አካባቢዎች ‹ንጉሥ› እንደነበረ ይታወሳል፡፡ በነገራችን ላይ በ19ኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ አካባቢ የተነሳው ጀርመናዊው ቢስማርክ የተከፋፈለች ሀገሩን
ሙሉውን አንብብ-Read More

የማንዴላ የቀብር ስነ ስርዓት ተፈፀመ

Geez Bet | Monday, December 16, 2013
የነፃነት እና የፀረ-ዘረኝነት ታጋዩ ኔልሰን ማንዴላ ስርዓተ ቀብር እሁድ ታኅሣሥ 6 ቀን 2006 ዓም ደቡብ አፍሪቃ ኩኑ በተባለችው የትውልድ መንደራቸው ተካሄደ። ለማንዴላ ክብር በቀብር ስርዓቱ 21 ጊዜ መድፍ የተተኮሰ ሲሆን፤ የጦር ጀቶች ከዕድምተኛው በላይ ሲያንዣብቡም ታይተዋል።
  ከእንስሳት ቆዳ የተሰፉ ባሕላዊ ልብሶችን የለበሱ ሀዘንተኞች ለማንዴላ ውዳሴ አሰምተዋል። የደቡብ አፍሪቃ አፓርታይድ ስርዓት ከተገረሰሰ በኋላ የሀገሪቱ የመጀመሪያው በዲሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጡት ኔልሰን ማንዴላ ግብዓተ መሬት የተፈፀመው በምሥራቃዊ ደቡብ አፍሪቃ በምትገኘው ኩኑ በተሰኘችው ገጠራማ መንደር ውስጥ ነው። በቀብር ስርኦቱ ላይ በበርካታ መቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እንደተገኙ የፈረንሣይ ዜና አገልግሎት አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል። ቀደም ብሎም በሺዎች የሚቆጠሩ ታዳሚዎች በማንዴላ ቅፅር
ሙሉውን አንብብ-Read More

በሳይንስ የኖቤል ተሸላሚዎችና ምርምራቸው

Geez Bet | Monday, December 16, 2013
ትናንት ፤ በእስቶክሆልም ፤ ስዊድን ፣ በኔልሰን ማንዴላ የመጨረሻ የስንብት ሥነ ሥርዓት ሳቢያ ታላላቅ ዓለም አቀፍ እንግዶች ተመናምነው ፣ ሆኖም ከ 1,300 በላይ ታዳሚዎች በተገኙበት ስብሰባ ፣ በ3 ቱም የተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፎች ውድድር ፣ የዘንድሮዎቹ አሸናፊዎች ሽልማታቸውን ተቀብለዋል። 

ለጀርመን ዓመታዊ የምርምር ከፍተኛ ሽልማት ለፍጻሜ የደረሱ 3 እጩ ተሸላሚዎች ፕሮጀክቶች ፤ ከብርሃን ጋር ግንኙነኅት ያላቸው ሲሆን፤ በተለይ ከየናው ፣ የፍሪድሪኽ ሺለር ዩንቨርስቲ ፣ ከ ቦሽና በ ሽራምበርግ ከተማ ከሚገኘው በ LASER(Light Amplification by Stimulated Emission of Radiation) ምርምር ላይ ካተኮረው ተቋም ጋር ተባብረው ለኢንዱስትሪ የሚበጅ
ሙሉውን አንብብ-Read More

Dec 14, 2013

በእሥራኤል ደም ልገሳ ያስከተለዉ ዉዝግብ

Geez Bet | Saturday, December 14, 2013
በኢትዮጵያ ተወልደው፣ በ 3 ዓመታቸው እሥራኤል በመግባት ፤ በዚያ ያደጉ የተማሩና የፓርላማ (ክኔሰት) አባል የሆኑት ፔኒና ታማኖ-ሻታ የተባሉት የ 32 ዓመት ወ/ሮ ፣ ከትናንት በስቲያ ደም ለመለገሥ ተዘጋጅተው ፤ በጤና ጥበቃ ሚንስቴር መመሪያ
ደንብ መሠረት እንደማይፈቀድላቸው ከአምቡላንስ አገልግሎት እንደተነገራቸው ፣ ድርጊቱ ፣ አስቆጥቶ፣ እ ጎ አ በ 1996 ዓ ም ተከሥቶ የነበረውን ፣ ቤተ እሥራኤላውያን ለደም ባንክ የለገሡት ደም እንዲደፋ የተደረገበትንና ብርቱ የተቃውሞ ሰልፍ ያስከተለበትን የቁርሾ ስሜትም ቀስቅሶ በእሥራኤል ሕብረተሰብ እንደገና ዐቢይ የመነጋገሪያ አጀንዳ ሆኖ ሰንብቷል።

የፓርላማ አባል ፤ ወ/ሮ ታማኑ ሺታ ፤ መምህርት፤ ጠበቃና የመገናኛ ብዙኀን ባለሙያ ሲሆን፤ በቅርቡ በኔልሰን ማንዴላ የመጨረሻ የስንብት ሥነ ሥርዓት ፤ በምክትል የፓርላማ አፈ ጉባዔ ሥልጣናቸው ፣ እሥራኤልን በመወከል ከፓርላማው አፈ ጉባዔ ጋር ደቡብ አፍሪቃ ደርሰው መመለሳቸውም ታውቋል። እኒህ የታወቁ ሴትዮ የተጠቀሰው ዓይነትችግር ካጋጠማቸው ብዙዎች ያልታወቁ ቤተ እሥራኤላውያን ምን -ምን እየደረሰባቸው ይሆን? የእሥራኤል መገናኛ ብዙኀን ሕብረተሰቡስ ምን ይላል? ጋዜጠኛ ዜናነህ መኮንን--
ከጤና ጥበቃ ሚንስትሯ ያኤል ጀርማንም ሆነ ከሀገሪቱ
ሙሉውን አንብብ-Read More

ማንዴላና የስፖርት ውርሳቸው

Geez Bet | Saturday, December 14, 2013
የስፖርት አዋቂዎች እንደሚሉት ማንዴላ ከዓለማችን ፖለቲከኞችና የመብት ተሟጋቾች በተለየ ስፖርትን በሰላም መሣሪያነት ተጠቅመዋል ። ለስፖርት ትልቅ ቦታ ይሰጡ የነበሩት ማንዴላ በተለያዩ ዓለም ዓቀፍ የስፖርት ተቋማትና በስፖርት ዓዋቂዎች ዘንድ ትልቅ ከበሬታ አላቸው ።
የዛሬ ሳምንት ሐሙስ በ95 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት የደቡብ አፍሪቃ ፕሬዝዳንት ኔልሰን ማንዴላ የነፃነት ታጋይ ብቻ ሳይሆኑ ስፖርት ዓለምን የመለወጥ ኃይል እንዳለው የሚያምኑ መሪ እንደነበሩም ታዋቂ የስፖርት ሰዎች ምስክርነታቸን እየሰጡ ነው ። የስፖርት አዋቂዎች እንደሚሉት ማንዴላ ከዓለማችን ፖለቲከኞችና የመብት ተሟጋቾች
ሙሉውን አንብብ-Read More

Dec 13, 2013

‹‹የወደፊቷ ደቡብ አፍሪካ ከማንዴላ ጋር መያያዟን እጠራጠራለሁ›› ሌተና ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለ ማርያም

Geez Bet | Friday, December 13, 2013
   በዚምባቡዌ የስደት ሕይወት የሚመሩት የቀድሞው ፕሬዚዳንት ሌተና ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለ ማርያም፣ ...
የኔልሰን ማንዴላን ሕልፈት በማስመልከት አውስትራሊያ ከሚገኘው ኤቢኤስ ሬዲዮ የአማርኛ አገልግሎት ጋር ቃለ ምልልስ አድርገዋል፡፡ መንግሥቱ ለሬዲዮው በሰጡት ቃለ ምልልስ እንደገለጹት፣ በእሳቸው በትረ ሥልጣን ወቅት ማንዴላ የአገሪቱን ከፍተኛ የክብር ሽልማት ከመጎናፀፈቸውም ባሻገር፣ የአንድ መቶ ሺሕ ዶላር ገንዘብ ተበርክቶለቸዋል፡፡ ይህና ቀሪው ንግግራቸው እንዲህ ቀርቧል፡፡ 

‹‹ማንዴላና የተወሰኑ ተከታዮቻቸው ወደ ኢትዮጵያ በስውር መጥተው፣ ወታደራዊ ሥልጠና አግኝተውና እግረ መንገዳቸውን ሞሮኮን ጐብኝተው ወደ ደቡብ አፍሪካ ማምራታቸውን ተገንዝቤያለሁ፡፡ 
‹‹በዚያን ጊዜ አሜሪካኖች በአማካሪነት ኢትዮጵያ ውስጥ ነበሩ፡፡ እስራኤሎችም ነበሩ፡፡ ከደቡብ አፍሪካ ጋር ግንኙነት የነበራቸው በመሆኑ የማንዴላን ኢትዮጵያ ውስጥ መገኘትና ወታደራዊ ሥልጠና በመከታተል እግር በእግር እየተከታተሉ መረጃ ሲሰበስቡ ስለሰነበቱ፣ ሰውየው አገራቸው እንደደረሱ
ሙሉውን አንብብ-Read More

Dec 12, 2013

የቤተእስራኤላውያን እሮሮ በእስራኤል

Geez Bet | Thursday, December 12, 2013
በእስራኤል ኣገር የሚገኙ ኢትዮጵያዊ ቤተእስራኤላውያን የኑሮ ውድነትን በመቃወም ኣደባባይ እየወጡ ነው። ከመንግስት የሚደረገው ድጎማ ከኑሮ ውድነቱ ጋር ሊጣጣም ባለመቻሉ በተለይም ቤት መግዛት እንዳልቻሉም ይናገራሉ። በዚያች ኣገር የሚኖሩ የኣፍሪካ ስደተኞችም የእስራኤል መንግስት የውጪ ስደተኞችን ከኣገሩ 

ለማስወጣት የያዘውን እቅድ በመቃወም ባለፈው ሳምንት ኣደባባይ ወተው ነበር።
በኣፍሪካ ስደተኞች የልማት ማዕከል መረጃዎች መሰረት በኣሁኑ ጊዜ በእስራኤል ኣገር 60 ሺህ ያህል የውጪ ስደተኞች ይገኛሉ።
ባለፈው ሐሙስ በእየሩሳሌም እና በናታኒያ ከተሞች አደባባይ የወጡት
ሙሉውን አንብብ-Read More

ባራክ ሁሴይን ኦባማ: ስለ ማንዴላ

Geez Bet | Thursday, December 12, 2013

«የማንዴላን አብነታዊነት ማሟላቱ ቢያቅተኝም፥ ምሳሌያዊ ምግባራቸዉ የተሻለ ሰዉ ለመሆን እንድጥር ያበረታታኛል።» ባራክ ሁሴይን ኦባማ፥ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት። ታሕሳስ 1/ 2006

ቀኑ ዝናባማ ቢሆንም ከ80 000 በላይ ህዝብ በሲዮቶው የዓለም ዋንጫ ስታዲየም በተካሄደው ስነስርዓት ላይ መገኘቱ ታውቐል።
የማንዴላ የቀብር ስንስርዓት የፊታችን እሁድ የትውልድ መንደራቸው በሆነችው የኩኑ ቀበሌ ይፈጸማል ተብሎ ይጠበቃል።

የኔልሰን ማንዴላ የኣሸኛኘት ስነስርዓት የተካሄደው በጆሃንስበርግ ከተማ ስዌቶ በሚገኘው የዓለም ዋንጫ ስታዲየም ነበር። ዕለቱ ከማለዳው ጀምሮ ዝናባማ ቢሆንም ከጆሃንስበርግ ከተማ እና ከተለያዩ የኣገሪቱ ከተሞች የመጡ ታዳሚዎች ከረፋዱ ጀምሮ ነበር በስታዲየሙ ዙሪያ የተሰባሰቡት። ቀትር
ሙሉውን አንብብ-Read More

Dec 11, 2013

የምስራቅ ኢትዮጵያ ፖለቲካ ፪

Geez Bet | Wednesday, December 11, 2013
(ተመስገን ደሳለኝ):

ባለፈው ሳምንት የምስራቅ ኢትዮጵያ ፖለቲካን ተጨባጭ እውነታዎችን ቃኝቼ ተከታዩን ክፍል በይደር አቆይቼው እንደነበረ ይታወሳል፤ እነሆም ዛሬ እንዲህ እቀጥላለሁ፡-
ሐረር እንደ ማሳያ

(መቼም ኢህአዴግ በብቸኝነት የሚኩራራበት የፖለቲካ ‹ስኬት›፣ ለዘመናት አንድ ሆኖ የኖረ ሕዝብን ‹ብሔር ብሔረሰቦች› በሚል ከፋፋይ የ‹ክርስትና ስም› እጥምቆ በአደባባይ ማስጨፈር ከሆነ ሰነባብቷል፡፡ ርግጥ ነው በአንድ ወቅት በፍትህ ጋዜጣ ላይ ‹‹የብሔር ብሔረሰቦች መብት እስከ መጨፈር›› በሚል ርዕስ የታተመ መጣጥፍን ተከትሎ ‹ፀረ-ብሔር ብሔረሰቦች› ተደርጌ በተመሰረተብኝ ክስ ፍርድ ቤት መመላለሴ ዛሬም ድረስ መቋጫ አላገኘም፤ ርግጥ ነው ኢትዮጵያውያን ወንድም እህቶቼ በስታዲዮሞች እየተሰባሰቡ የራስ ፀጉራቸው ላይ ላባ ሰክተው፣ ቆዳ አገልድመው እየዘለሉ ትርኢት ከማሳየት ባለፈ የመልካም አስተዳደር፣ የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካ መብቶቻቸው ተጠቃሚ መሆን አልቻሉም፡፡ …እውነታው ይህ ቢሆንም ወደ አጀንዳችን /የከሸፈው ፌደራሊዝምን/ ወደ መፈተሹ በአዲስ መስመር እንመለስ፡፡
ቋንቋን መሰረት ያደረገው ኢህአዴግ ሰራሹ ‹ፌደራሊዝም› አወቃቀር የሀገሪቱ መፃኢ ዕድል የተቋጠረበት ‹የሰዓት ቦንብ› መሆኑን ለመረዳት
ሙሉውን አንብብ-Read More

Dec 9, 2013

በመዲናዋ ምስጢራዊ የወሲብ ገበያ ደርቷል

Geez Bet | Monday, December 09, 2013
  1. የትላልቅ ድርጅቶች ፀሃፊዎች፣ ሞዴሎችና ተዋናዮች አሉበት
  2. ድንግልናን በ10ሺ ብር የሚያሻሽጡ ደላሎች ሞልተዋል   
  3. የከተማዋ ቱባ ባለሃብቶች “የአገልግሎቱ” ተጠቃሚዎች ናቸው
 ሲኤምሲ ሣሚት ማዞሪያ አካባቢ ካሉት ዘመናዊ ቪላ ቤቶች በአንደኛው 12ሺ ብር ወርሃዊ ኪራይ እየከፈለች ትኖራለች፡፡ የምታሽከረክረው ኤክስኪዩቲቭ ቶዮታ፣ በየዕለቱ የምትቀያይራቸው እጅግ ውድ ዋጋ ያላቸው አልባሳቶቿና በየመዝናኛ ሥፍራው የምትመዘው ረብጣ ብር የተንደላቀቀ ኑሮ እንደምትመራ ይመሰክራሉ፡፡ በሳምንቱ መጨረሻ ቀናትና መዲናችን አለማቀፋዊ ስብሰባዎችን በምናስተናግድበት ጊዜያት እሷን ፈልጐ ማግኘት የማይታሰብ ነው፡፡
ቦሌ ፍሬንድሽፕ ሕንፃ ላይ በከፈተችው ቡቲክ የምታገኘው ገቢ ይሄን ያህል ሊያዝናናት እንደማይችል የታወቀ ነው፡፡ ገቢ ወጪዋን አጥብቃ የማትቆጣጠርበትን ይህንኑ ቡቲኳን ታናሽ እህቷ ትውልበታለች፡፡ እሷም አልፎ አልፎ “ሥራ” በማይኖራት ጊዜ ብቅ እያለች ትጐበኘዋለች፡፡ ታናሽ እህቷ ቤተሰቡን ሁሉ ቀጥ አድርጋ የምታስተዳድረው እህቷ፤ ስለምትሰራው ምስጢራዊ ሥራ አንዳችም የምታውቀው ነገር ያለ አይመስልም፡፡ እሷ የምታውቀው ከተለያዩ የውጪ አገር ሰዎች ጋር የአየር ባየር ንግድ እንደምታጧጡፍና በየጊዜው ወደተለያዩ አገራት ለሥራ ጉዳይ እንደምትመላለስ ብቻ ነው። ሥራዋ የግል ሚስጢሯ ብቻ ሆኖ እንዲኖር የምትፈልገው ህሊና (ስሟ ለዚህ ጽሑፍ የተቀየረ) ይህንን
ሙሉውን አንብብ-Read More

ከሳውዲ ተመላሽ ዜጎች ንብረታቸው በጉምሩክ እንደተወሰደባቸው ተናገሩ

Geez Bet | Monday, December 09, 2013
ህገወጥ ናችሁ ተብለው ከሳውዲ አረቢያ ወደ አገራቸው የተመለሱ ኢትዮጵያዊያን፤ ለበርካታ አመታት ለፍተን ያፈራነውን ንብረት ይዛችሁ መግባት አትችሉም ተብሎ ተነጥቀናል፡፡ የፍተሻ ሰራተኞች ሻንጣዎቻቸውን በመፈተሽ፣ ሞባይል ከአንድ በላይ ከያዙ ትርፉን በማስቀረት፣ አዳዲስ አልባሳት እና ኤሌክትሮኒክስ ቁሰቁሶች የተወሰኑትን ብቻ በመፍቀድ እና ያመጡትን ወርቆች ግራም በመቀነስ ንብረታቸውን እየወሰዱባቸው እንደሆነ ተመላሾቹ ገልፀዋል፡፡
መሃመድ አባመጫ የተባለ የሳኡዲ ተመላሽ፤ ከሳውዲ ስድስት ሻንጣ ይዞ መምጣቱን ገልፆ፤ ቦሌ አውሮፕላን ማረፍያ ሲደርስ ግን ከሁለት ሻንጣ በላይ ይዞ መግባት እንደማይችል፣ ከአምስት ሞባይሎችም ሁለቱ ብቻ እነደተፈቀደለት ለአዲስ አድማስ ተናግሯል፡፡ የሳውዲ መንግስት ከአንድ ኪሎ በላይ ወርቅ ይዛችሁ መውጣት አትችሉም የሚል መመሪያ ማሳለፉን የጠቆመው ተመላሹ፤ ንብረቱን እዚያው ጥሎ ለመመለስ መገደዱን ገልጿል፡፡ የሳኡዲ መንግስት እንኳን ከወርቅ
ሙሉውን አንብብ-Read More

በማንዴላ ሞት የአፍሪቃውያን መሪዎች አስተያየት

Geez Bet | Monday, December 09, 2013
   የተከበሩት ተወዳጁ የደቡብ አፍሪቃ ፀረ አፓርታይድ ታጋይ እና ትልቅ አመለካከት ያተረፉት አንዱ የ 20ኛው ምዕተ ዓመት ዕውቅ ፖለቲከኛ ኔልሰን ማንዴላ ሐሙስ፣ ኅዳር 26 ቀን፥ 2006 ዓም በ95 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩበት ዜና በደቡብ አፍሪቃ፣ በመላ አፍሪቃ እና በዓለም ትልቅ ሀዘን አስከትሎዋል። 
ከ 27 ዓመታት እስራት በኋላ በደቡብ አፍሪቃ የመጀመሪያው ጥቁር ፕሬዚደንት ሆነው እአአ በ1994 ዓም የተመረጡት እና ሀገሪቱን እስከ 1999 ዓም የመሩት ኔልሰን ማንዴላ ለረጅም ጊዜ ለሳምባ ሕመም በሀኪም ቤት እና ካለፈው መሰከረም ወርም በኋላ ጆሀንስበርግ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ህክምና ሲደረግላቸው ከቆዩ በኋላ ነው ያረፉት።
የደቡብ አፍሪቃው ፕሬዚደንት ጄኮብ ዙማ ተወዳጁ መሪ እና የዴሞክራሲያዊቷ ሀገር መሥራች አባት የሆኑትን የኔልሰን ማንዴላን ዜና ዕረፍት ያስከተለወን መሪር ሀዘን ለደቡብ አፍሪቃውያን እንዲህ ሲሉ ነበር በሀገሪቱ ቴሌቪዥን በይፋ
ሙሉውን አንብብ-Read More

የአፄ ምኒልክ 100 ኛ ሙት-ዓመትና ክንዋኔዎቻቸው

Geez Bet | Monday, December 09, 2013
አውሮፓውያን ከዚያ በፊት ያልታዬ ከእርስ -በርስ አስከፊ ፍጅት የደረሱበት የአንደኛው የዓለም ጦርነት ሊፈነዳ 7 ወራት ገደማ ሲቀሩት ነበረ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ዳግማዊ አፄ ምኒልክ ታኅሳስ 3 ቀን 1906 ዓ ም ያረፉት።

በዘመኑ ብቸኛይቱን አፍሪቃዊት ነጻ ሀገር ይመሩ የነበሩት አፄ ምኒልክ ህዝባቸውና የጦር አለቆቻቸውን አስተባብረው ፣ መላ ኢትዮጵያን በቅኝ ግዛት ሥር ለማድረግ የዘመተውን የኢጣልያ ጦር ኃይል አድዋ ላይ ድል በመምታት ፣ በዘመኑም የዘመናዊ ሥልጣኔ መገለጫዎች የነበሩ ስልክና ባቡር ሐዲድ በማስገባት ፣ ት/ቤትና ባንክ የመሳሰሉትን ተቋማት በመክፈት ይታወቃሉ። በውጭው ዓለም የተፈሩ ፣ የተከበሩ ፣ በቅኝ ግዛት ሥር ለነበሩ አፍሪቃውያንና ከባህር ማዶ ፣
ሙሉውን አንብብ-Read More

Dec 7, 2013

የማንዴላ ሞትና የዓለም አስተያየት

Geez Bet | Saturday, December 07, 2013
ዓለም፥ ድፍን ዓለም የሩሲያዉ ፕሬዝዳት ቭላድሚር እንዳሉት «የዘመኑን ታላቅ ፖለቲከኛ» በማጣቱ ተከዘ።አብዛኛዉ ዓለም አዘነ።ደቡብ አፍሪቃዎች ደግሞ በሐገሪቱ ፕሬዝዳት በጄኮብ ዙማ አገላለፅ «መሆን የሚፈልጉትን እንዲሆኑ ባደረጓቸዉ» ታላቅ ሰዉ ሞት አረገዱ። 

ማንዴላና ደቡብ አፍሪቃ
ማንዴላ።ከእንግዲሕ እኛ የደቡብ አፍሪቃ ታላቅ ልጅ፥ እኛ የዴሞክራቲክ ሥርዓቷ ቀንዲል፥ እኛ የደቡብ አፍሪቃዉያን ልዩ አባት ታላቅ ምግባራቸዉ ነዉ-ቀሪ፥ መዘከሪያቸዉ።እንደገና ሒሩት መለሰ ያጠናቀረችዉን ተክሌ የኋላ ያሰማናል።
ሙሉውን አንብብ-Read More

ማዲባ የድቡብ አፍሪቃውያን አባት

Geez Bet | Saturday, December 07, 2013
እንደ ወጣት በእልሕ፥ እንደ ወታደር በነፍጥ፥ እንደ ሕግ አዋቂ በፍርድ ቤት ታገሉ።እንደ ወንጀለኛ ታሠሩ።እንደ ዲፕሎማት ተደራደሩ፥ እንደ ፖለቲከኛ የሕዝብ እኩልንነትን አስርፀዉ ሐገር መሩ።እና እንደ ሰዉ የምድር ሩጫቸዉን ትናንት ጨረሹ።ዘጠና አምስት አመታቸዉ ነበር።

የሕዝብ ነፃነት፥ ፍትሕ፥ እኩልነትን ሚሊዮነ-ሚሊዮናት ይፈልጉ-ይመኙታል ። መቶ ሺሕ ዎች ይታገሉ ወይም ለመታገል ይሞክሩታል።ሺዎች ትግሉን ያጋምሱ ወይም ይሰዉለታል።ዓላማ ትግሉን ከግብ የሚያደርሱት ግን፥- እኒያ ጥቂት በጣም ጥቂት ቆራጦች፥ ብልሆች፥ ታጋሾች፥ ስልት አዋቂዎች፥ እና
ሙሉውን አንብብ-Read More

Dec 4, 2013

የዓለማቀፉ የሙስና ጥናት ተቋም መግለጫ

Geez Bet | Wednesday, December 04, 2013
የመካከለኛው ምስራቅሀገሮች ከጊዜ ወደ ጊዜ በሙስና እየተዘፈቁ መምጣታቸውን ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሺናል የተባለ ኣንድ የጥናት ተቐም ኣስታወቀ። መቀመጫውን በጀርመን ሀገር ያደረገው ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሺናል ዛሬ ባወጣው ዓመታዊ ሪፖርቱ በተለይ
በቀጠናው ከተቀጣጠለው የዓረብ ዓብዮት ወዲህ ደግሞ በመከከለኛው ምስራቅ ሀገሮች የሚታየው የሙስና ይዞታ እጅግ ተባብሷል። በኣጠቃላይ የመካከለኛው ምስራቅ ኣገሮች ሁሉም ማለት ይቻላል ያላቸው ነጥብ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ከተቀመጠው ኣማካኝ የሙስና የጥብ በታች ሲሆን በትራንስፓረንሲ ኢኒተርናሺናል መመዘኛ መሰረት በዓለም ዓቀፍ ደረጃ የተቀመጠው ኣማካኝ የሙስና ነጥብም 43 ነው
ዓለም ዓቀፉ የሙስና ጥናት ተቐም ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሺናል ዛሬ ባወጣው ዓመታዊ ዘገባ በመካከለኛው
ሙሉውን አንብብ-Read More

Dec 3, 2013

የዓርብ ግዞተኞች ፪

Geez Bet | Tuesday, December 03, 2013
(አስራት አብርሃም)
ባለፈው ሳምንት በዚህ ርዕስ ልፅፈው የፈለኩትን አልጨረስኩም ነበርና እነሆ ዛሬ የመጨረሻውን ክፍል ይዤ ቀርቤያለሁ። አብዛኛውን በሰላማዊ ሰልፉ ላይ ተገኝቶ የተያዘ (ከመንገድ የተያዙም ነበሩበት) እስረኛ ቪድዮ ቀርፀው፤ ስሙንም መዝግበው ወደ አስር ሰዓት አከባቢ አስናበቱት። እኛ አስራ አምስት የምንሆን ግን ለይተው እንድንቆይ አደረጉን። ማደራችን እንደሆነ አስብኩ፤ በንጋታው ቅዳሜ በመሆኑ ከፈለጉም እስከሰኞ ሊያቆዩን እንደሚችሉም አስብኩ። ለሁሌስ ቢሆን ሊያስሩን ከፈለጉ ማን ይከለክላቸዋል፤ ወደ ቃሊቲም ሊልኩን ይችላሉ።

ብዙዎቹ ግን ምንም ጥፋት እንደሌለን እና በአጭር ጊዜ ውስጥም ልንፈታ እንደምንችል እየተናገሩ ራሳችውን አበርትተው እኛንም ያበረታቱን ነበር። ለነገሩ እዚያ በእንዲህ ባለ ሁኔታ እንድንታሰር የሆነው እኮ ወንጀል ስርተን አልነበረም። እነርሱ ሊያስሩን ስለፈለጉ እንጂ! ስለዚህ የእኛ መፈታትና መታሰር ወይም በእስር መቆየት የሚወስነው የሰራነው ወንጅል ቅለትና ከብደት ሳይሆን የእነርሱ ፍላጎትና መልካም ፍቃድ ነው። ብቻ እኛ የታሰርነው በሀገራችን በመሆኑ፤ በሰው ሀገር እየተሰቃዩ ከነበሩት ወገኖቻችን
ሙሉውን አንብብ-Read More

የምስራቅ ኢትዮጵያ ፖለቲካ

Geez Bet | Tuesday, December 03, 2013
(ተመስገን ደሳለኝ)
…አውሮፕላኑ ቅዳሜ ጠዋት ሶስት ሰዓት ላይ ድሬዳዋ አየር ማረፊያ ደርሶ ከተርሚናሉ ስወጣ፣ ተጠራጥሬ ሰዓቴን ተመለከትኩ፤ የድሬ የጠዋት ፀሐይ ከተለመደው ንዳዷ ጋር የአዲስ አበባን የቀትር መራራ ፀሀይን ታስከነዳለች፤ እናም አጥበርባሪ ጨረሯን ያለምህረት ስትለቅብኝ፣ ጓደኛዬ መኪና ይዞ እቦታው እስኪደርስ መጠበቁ በገዛ ፍቃድ መለብለብ ስለመሰለኝ፣ በቀጥታ ከተደረደሩት ታክሲዎች አንዱን ይዤ ወደ ከዚራ አመራሁ፤ ድሬ የሄድኩት በዋናነት ከማህበራዊ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ምክንያት በመሆኑ ሊቀበለኝ የተዘጋጀውን ጓደኛዬን ደውዬ ከማውቃቸው የአንዱን ሆቴል ስም ጠቅሼ እዚያ እንድንገናኝ ነገርኩት፡፡

የሆቴሉ ፍተሻ ከወትሮው ጠንከር፣ ጠጠር ያለ በመሆኑ ትዕግስትን ይፈትናል፡፡ እንዲህም ሆኖ ወደ ውስጥ ስንዘልቅ ማረፊያ ክፍሎች በሙሉ መያዛቸው ተነግሮን ቀኝ ኋላ ለመዞር ተገደድን፤ ይሄኔም ነው የጓደኛዬ ፊት ልውጥውጥ ሲል ያስተዋልኩት፤ ጭንቅላቴን በማነቃነቅ በምልክት ምን እንደተፈጠረ ጠየኩት፤ ለአፍታ አመንትቶ ከፊት ለፊታችን በግምት አስር ሜትር ርቀት ላይ ወደቆሙ ሁለት ሰዎች ጠቆመኝ፤ ልብ ብዬ አየኋቸው፤ ሁለቱንም ከዚህ ቀደም አይቻቸው አላውቅም፤ ደግሞም በዙሪያችን ከሚርመሰመሱ ሰዎች የተለየ ምንም አይነት
ሙሉውን አንብብ-Read More

Nov 30, 2013

ነገደ ኢትዮጵያ

Geez Bet | Saturday, November 30, 2013
ይህ ጽሑፍ መሪ ራስ አማን በላይ ‹የጥንቷ የኢትዮጵያ ትንሣኤ ታሪክ› በሚል ርዕስ ከመጽሐፈ ሱባኤ ተረጎምኩት ብለው በ1985 ዓ.ም. ካሳተሙት መጽሐፍ ከምዕራፍ ሦስት በሙሉ የተወሰደ ነው፡፡ ጽሑፍ እሳቸው እንዳዘጋጁት ነው እንጂ የተጨመረበት ወይም ኤዲት የተደረገ ነገር የለውም፡፡ መጽሐፉ በያዛቸው መረጃዎችም ሆነ በምንጩ በተለምዶ ከሚታወቀው የታሪክ መጽሐፎች ይለያል፤ ስለ መጽሐፉ ይዘት፣ ምንጭና አስፈላጊነት ብዙ ማለት ቢቻልም፤ መጽሐፉ ብዙ ሰዎች በቀላሉ አግኝተውት ያላለነበቡት በመሆኑ አንዱን ምዕራፍ ብቻ እንደነበረ እንደማሳያ ማቅረብ የተሻለ መስሎ ታይቶኛል፡፡ ለማንኛውም ስለ መጽሐፉ ሁኔታ ለማወቅ በመግቢያውና በመጽሐፉ ጀርባ ከጻፉት ላይ ቀንጭቦ ማየት ጠቀሜታ ይኖረዋልና እነሆ!
(ከመግቢያው የተወሰደ)
‹‹ይሄን የጥንቷ የኢትዮጵያ ታሪክ ሱዳን አጥባራ በነበርኩበት ጊዜ የኢትዮጵያ ታሪክ ከመጽሐፈ ሲራክ እያነበብኩ ስለ ድንጋይ ጥበብና ስለሌላም ስከታተል እንደቆየሁ ጀቢል ኩራርና ጀቢል ኦባ ወደሚባለው ሃገር ሄጄ የጥንት ቤተክርስቲያን ፍርስራሽና የክርስቲያን መቃብር አገኘሁ፤ ከዚያም ጀበል ኦባ ለአንድ ሰባት ወር እንደተቀመጥኩ አንድ ሽማግሌ ሰው እንዲህ ካለ ዋሻ ውስጥ የክርስቲያኖች መጽሐፍ አለ ብለውኝ አብረን ሄድን፤ ብዙ በብራና የተጻፉና የተቀዳደዱ መጽሐፎች አገኘን፤ እንደገና ከሌላ ዋሻ ሄደን ስንቆፍር ብዙ ፅላቶችንና ቁርጥራጭ ካባዎችን፣ ቁመቱ ክንድ አንድ መቶ ስልሳ አራት ብራና የአክሱማይ ሲራክን መጽሐፍ፣ የሱባን ቋንቋና የሱባን ታሪክ የያዘ መጽሐፈ ሱባኤ፣ እንደዚሁም በጣም የረዳኝ ሁለት መቶ ብራና አራት መቶ ገጽ ያለው የኢትዮጵያ ነገሥታት ታሪክ ዘግዱር ዘእንዳ ቤት በተፈለፈለ የድንጋይ ጉድጓድ ከተልባና ከአመድ ጋር ተቀብሮ ተገኘ፡፡
መጽሐፈ ሱባኤ ከአዳም እስከ ቀዳማዊ ምኒልክ መፀሐፈ አክማይ
ሙሉውን አንብብ-Read More

Nov 29, 2013

አና ጐሜዝ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር ገንቢና ግልጽ ውይይቶችን አደረግኩ አሉ

Geez Bet | Friday, November 29, 2013
ከዘጠኝ ዓመት በፊት በተካሄደው የግንቦት 1997ቱ ምርጫ የአውሮፓ ኅብረትን በመወከል የምርጫ ታዛቢ የነበሩት ፖርቱጋላዊቷ አና ጐሜዝ በሰብዓዊ መብት አያያዝ ላይ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር መነጋገራቸውን ገለጹ፡፡
ዛሬ በሚጠናቀቀው የአፍሪካ፣ የካሪቢያን፣ የፓስፊክና የአውሮፓ ኅብረት የጋራ የፓርላማ 26ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ለመካፈል አዲስ አበባ የመጡት አና ጐሜዝ፣ በአዲስ አበባ በነበራቸው ቆይታ ከኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት ጋር ገንቢና ግልጽ ውይይቶችን ማድረጋቸውን ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

የጋራ ስብሰባው ላይ ለመካፈል ወደ አዲስ አበባ የመጡት የአውሮፓ ኅብረት ፓርላማ አባልና በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ከፍተኛ ትችት በመሰንዘር የሚታወቁት አና ጐሜዝ፣ ወደ ኢትዮጵያ ለመግባት ምንም ዓይነት የቪዛ ችግር እንዳልገጠማቸው ገልጸው ይህም አዲስ ዓይነት የፖለቲካ አተያይ እየተፈጠረ መሆኑን ያሳያል ብለዋል፡፡
ሙሉውን አንብብ-Read More

የሕዳሴ ግድብ ግንባታ እና የሙሌት ፖሊሲው

Geez Bet | Friday, November 29, 2013
ጥንታዊ ስልጣኔን ለታሪክ ትተን ከድህነት ወለል በታች ከሚፈረጁት የዓለማችን ኣገራት ተርታ ተሰልፋ የምትገኘው ኢትዮጵያ ግን ደግሞ ይህ ነው የማይባል የተፈጥሮ ሀብትም እንዳላት ይታወቃል። 
  ከተፈጥሮ ሀብቷ መካከልም ኣንደኛው የውኃ ኃብቷ ሲሆን ወንዞቿ ደግሞ ድንበር ዘለልም ጭምር ናቸው። ከዚሁ የተነሳ የምስራቅ ኣፍሪካ የውኃ ምንጭ በመባልም ትታወቃለች። ኣንዱና ዋናው ደግሞ ጥቁር ዓባይ ወይንም በውጪው ኣጠራር ብሉ ናይል ነው። 75 በመቶ የሚሆነው የናይል ውኃም የሚመጣው
ሙሉውን አንብብ-Read More

Nov 26, 2013

የኢራን ሥምምነትና ዉዝግብ

Geez Bet | Tuesday, November 26, 2013
ኢራን ድብቅ የኑክሌር ተቋም እንዳለት ከታወቀበት ከሁለት ሺሕ ሁለት ጀምሮ በቴሕራንና በምዕራባዉያን ሐገራት ፖለቲከኞችን መካከል የደራዉ ዉዝግብ ለመጀመሪያ ጊዜ-አንድ እልባት አግኝቷል። የእስራኤል-ምዕራባዉያን ልዩነት፥ የኢራን-እስራኤል ዉዝግብስ ነዉ?-የዛሬዉ ጥያቄ 
የአያቶላሕ ሩሑላሕ ሆሚኒዋ «ታላቅ ሠይጣን» የድብቅ ዲፕሎማቶች፥ ከጆርጅ ዳብሊዉ ቡሿ «የሰይጣን ዛቢያ» ስዉር መልዕክተኞች ጋር በዓለም የፖለቲካ መድረክ ብዙም በማትታወቀዉ ሐገር፥ በድብቅ ሆቴል፥ በዘወርዋራ አሳንስር ወይም ሊፍት ዉስጥ የጀመሩት ድርድር ቅዳሜ-ለዕሁድ አጥቢያ በይፋ ዉል ተቋጠረ።ዤኔቭ።
«ከከባድ ድርድር በሕዋላ ለረጅም ጊዜ፥ አጠቃላይ መፍትሔ በሚያደርሰን የጋራ የድርጊት መረሐ-ግብር ላይ ዛሬ ተስማምተናል።»
የአዉሮጳ ሕብረት የዉጪ ግንኙነት ሐላፊ ወይዘሮ ካትሪን አሽተን።የድብቅ፥ ይፋዉ ድርድር ሒደት፥ የስምምነቱ ይዘት፥ የተቃዉሞዉ እንዴትነት ያፍታ ዝግጅታችን ትኩረት ነዉ።አብራችሁኝ ቆዩ።
ሙሉውን አንብብ-Read More

Nov 25, 2013

የሳኡዲ ተመላሾች የስደት መከራቸውን በምሬት ይተርካሉ

Geez Bet | Monday, November 25, 2013
እኛ ተርፈናል፤ እዛ ላሉት ድረሱላቸው
ኢትዮጵያውያን ሴቶች ተገደው እየተደፈሩ ነው !
እስር ቤት አንዲት ነፍሰ ጡር ሞታብናለች
- የስደት ተመላሾች 
ሳኡዲ አረቢያ በህገወጥ መንገድ ወደ አገሯ የገቡ ስደተኞችን በሃይል ማስወጣት
ከጀመረች ሁለተኛ ሳምንቷን ያስቆጠረች ሲሆን ህገወጥ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ወደአገራቸው የመመለስ ዘመቻው አሁንም እንደቀጠለ ነው፡፡ ዜጐችን ከሳኡዲ ለማምጣት ባለፈው ሳምንት በቀን ሰባት በረራዎች ይደረጉ እንደነበር ያስታወሱት የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ፤ በዚህኛው ሳምንት በቀን 12 በረራዎች እየተደረጉ ዜጐችን ማምጣቱ እንደቀጠለና እስከትላንት ድረስ ከ19ሺ በላይ ዜጐች መመለሳቸውን ገልፀዋል፡፡
ሙሉውን አንብብ-Read More

ኢትዮጵያዊ ዋጋው ስንት ነው?

Geez Bet | Monday, November 25, 2013
(ተመስገን ደሳለኝ)
የዚህ ፅሁፍ ማጠንጠኛ የፖለቲካ አመለካከትን መተቸት አይደለም፤ ከዋና ዋና ሀገራዊ አጀንዳዎች ወረድ ያሉ የጉልበታሙን ስርዓት የሥራ አፈፃፀሞችን ማብጠልጠልም አይደለም፤ የተቀናቃኝ ፓርቲዎችን ስንክሳር መንቀስም… አይደለም፡፡ ኢትዮጵያዊ (አል-ሀበሽ) መሆን ለፈተና፣ ለመከራ፣ ለሰቆቃ… መዳረጉ የወለደው ብሶት እንጂ፤ መመረር-ማምረር ነው፡፡ …ይህ የእኛ ዕጣ ፈንታ የሆነበትን ምስጢር መመርመር ነው፡፡
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ
ሰሞኑን የሳውዲ አረቢያ መንግስት ታጣቂዎች እና በድጎማ የሚያድሩ የሀገሬው ተወላጆች በመሰረቱት የጥፋት ግንባር ጉልበታቸውን ገብረው፣ በላብ በወዛቸው በሚያድሩ ስደተኛ ወገኖቻችን ላይ የተፈፀመው አረመኔያዊ ወንጀል፣ የሁሉንም ኢትዮጵያዊ ልብ በከባድ ሀዘን የሰበረ፣ በቁጭት ያንገበገበ አሳዛኝ ፍፃሜ ሆኗል፡፡ ጭፍጨፋው ሃይማኖታዊው

ሙሉውን አንብብ-Read More

Nov 24, 2013

አቶ ያረጋል አይሸሹም ከ5 የሙስና ክሶች በ4ቱ ነፃ ሆኑ

Geez Bet | Sunday, November 24, 2013
በተለያዩ ከተሞች በራሳቸው፣ በባለቤታቸውና በልጆቻቸው ስም 17 ቦታዎችንና ቤቶችን ይዘዋል ከሚለው ክስ ነፃ ሆነዋል፡፡
ከባለቤታቸው ጋር ምንጩ ያልታወቀ 490ሺ ብር በባንክ አንቀሳቅሰዋል ከሚለው ክስ ነፃ ናቸው ተብሏል:: የቀድሞው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ያረጋል አይሸሹም፤ በፀረ ሙስና ኮሚሽን ከቀረቡባቸው አምስት ክሶች መካከል በአንዱ ብቻ “ጥፋተኛ ናቸው” የተባሉ ሲሆን፣ ምንጩ ያልታወቀ ሃብት አካብተዋል በሚል ከቀረበባቸው ክሶች ነፃ ሆኑ፡፡
አቶ ያረጋል አይሸሹም እና የትምህርት ቢሮ ሃላፊ የነበሩት አቶ ሃብታሙ ሂካ፣ ከሁለት የግል ድርጅት ሃላፊዎች ከአቶ ጌዲዮን ደመቀና ከቶ አሰፋ ገበየ ጋር “ጥፋተኛ ናቸው” የሚል ውሳኔ የተላለፈባቸው፤ ለሦስት የትምህርት ተቋማት ግንባታ ከወጣው ጨረታ ጋር በተያያዘ ክስ ነው፡፡ ህገወጥ የጥቅም ግንኙነት በመፍጠር  ለመምህራን ኮሌጅ፣ ለአዳሪ ት/ቤት እና ለቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት የግንባታ ጨረታ ከመንግስት መመሪያ ውጪ እንዲከናወን አድርገዋል በሚለው ክስ 4ቱ ተከሳሾች ጥፋተኛ ሆነው እንደተገኙ የከፍተኛው ፍ/ቤት ችሎት ሐሙስ እለት ገልጿል፡፡ 
ሙሉውን አንብብ-Read More

Nov 23, 2013

ኢህአዴግ ስለምን ይጮኻል?

Geez Bet | Saturday, November 23, 2013
(ተመስገን ደሳለኝ)
በረዥሙ የኢትዮጵያ ዘመነ መንግስት ታሪክ፣ በአስተዳደሩ ተመስግኖ በክብር የተሸኘ ገዥ ስለመኖሩ የሚያወሳ አንድም ድርሳን ፈልጎ ማግኘት የሚቻል አይመስለኝም፡፡ ሁሉም መንግስታት የተወገዱት በአመፅ አሊያም በተፈጥሮ ሞት ነውና፡፡ በ1983 ዓ.ም ወርሃ ግንቦት በጠብ-መንጃ ኃይል ሥልጣን የተቆናጠጠው ኢህአዴግ-መራሹ መንግስትም ቢሆን፣ በቀድሞዎቹ ገዥዎች ‹የብረት ጫማ› ውስጥ ተከልሎና ተደላድሎ ዕለተ-ስንብቱን በመጠባበቅ ላይ ያለ ይመስለኛል፡፡ ዕ
ለተ-ስንብቱ መቃረቡን የሚጠቁመው ደግሞ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ልክ እንደ ደርግ የመጨረሻዎቹ ወራት ሁሉ፣ ግንባሩና አጋር ፓርቲዎቹ ለየት ባለ መልኩ በራሳቸውና በሹማምንቶቻቸው ላይ በአደባባይ የተቃውሞ ድምፅ ማሰማት መጀመራቸው ነው፡፡ የዚህ ፅሁፍ ተጠየቅም ይህ ነውና ተጨባጭ እውነታውን ለማብራራት በቂ የሆኑ አስረጂዎችን በአዲስ መስመር በዝርዝር ለመመልከት እሞክራለሁ፡፡
ሙሉውን አንብብ-Read More

የዓርብ ግዞተኞች

Geez Bet | Saturday, November 23, 2013
አስራት አብርሃም
የሳውዲ መንግስት በወገኖቻችን ላይ እየፈፀመ ባለው ግድያ እና ግፍ ምክንያት በሰማያዊ ፓርቲ የተጠራው ሰልፍ በመንግስት በእኩል ይሁንታ እንዳላገኘ ብንሰማም የሆነው ይሁን እነርሱ በሰው ሀገር መከራና ስቃይ እየተቀበሉ አይደለ በሚል ነው ከተወሰኑ ጓደኞቼ ጋር ወደ ሰልፉ ለመሄድ የቆረጥነው። ችግር ሊኖር እንደሚችል ገምተናል።
ከሰማያዊ ፓርቲ ብርሀኑ ተክለያሬድ ጋር የት ደረሳችሁ እየተባባልን እየተደዋወልን ነበርና በመሀሉ ስልኩ ጠፋኝ። መጨረሻው ግን አራት ኪሎ እንደታገቱ ሰማንና እኔና ሌሎች ሶስት ጓደኞቼ ሆነን ወደ ሰልፉ ቦታ መሄድ ጀመርን። ከኋላችን ብዙ ሰው ቀስ እያለ እየመጣ ነበር። ወደ ሰልፉ እየተጠጋን ስንመጣ ብዙ ሰው ወደእኛ አከባቢ እየሸሸ ሲመጣ ተመለከትን። የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ወጣት ሴት ልጆች እያለቀሱ ወደ እኛ እየመጡ ነው። በዚህ ጊዜ እነ ዳዊት ከበደ፣ ኤልያሰ ገብሩ እና እስክንድር ፍሬው አግኝተናቸው ስለሁኔታው
ሙሉውን አንብብ-Read More

Nov 22, 2013

የአፍሪቃና የአውሮፓ የሰብዓዊ መብቶች ውይይት

Geez Bet | Friday, November 22, 2013
የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ድርጅት ሂዩመን ራይትስ ዋች በአንዳንድ የአፍሪቃ ሃገራት በመገናኛ ብዙሃንና በሰብዓዊ መብት ተከራካሪዎች ላይ ተጠናክሮ የቀጠለው ጥቃት እንዲቆም እርምጃ ይወሰድ ዘንድ ብራሰል ቤልጂግ ውስጥ ለተካሄደው የአፍሪቃና የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽኖች የሰብዓዊ መብቶች የጋራ መድረክ አሳስቧል ። 

የአፍሪቃ ህብረትና የአውሮፓ ህብረት በአፍሪቃ ለሰብዓዊ መብት መከበር ለሚታገሉና አውሮፓ ውስጥ ለሚገኙ የውጭ ዜጎች የተጠናከረ ጥበቃ ለማድረግ በጋራ እንዲሰሩ ተጠየቁ ። የአውሮፓ ህብረትም ለውጭ ዜጎችና ለተገን ጠያቂዎች የተሻለ ጥበቃ እንዲያደርግ ጥሬ ቀርቦለታል ። ሂሩት መለሰየአፍሪቃ ህብረትና የአውሮፓ ህብረት ኮሚስዮኖች ብራሰልስ ቤልጅየም ውስጥ ካካሄዱት ዓመታዊ የሰብዓዊ መብቶች ውይይት ዋነኛ ትኩረቶች አንዱ አፍሪቃ ውስጥ በሰብዓዊ መብት ተከራካሪዎች በጋዜጠኖችና በሲቪል ማህበራት ላይ የሚፈፀመው ጥቃት
ሙሉውን አንብብ-Read More

Nov 21, 2013

የፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጤንነት እያነጋገረ ነው

Geez Bet | Thursday, November 21, 2013
- «ፕሬዚዳንቱ በመልካም ጤንነት ላይ ይገኛሉ» አቶ የማነ ገብረመስቀል
- አሜሪካ ዜጎችዋ ወደ ኤርትራ እንዳይጓዙ አስጠነቀቀች
ከመገናኛ ብዙኃንና ከሕዝብ እይታ ከራቁ ከአንድ ወር በላይ የሆናቸው  የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጤንነት ጉዳይ እያነጋገረ ነው፡፡

አስማሪኖ የተባለውና መቀመጫውን በካሊፎርኒያ አሜሪካ ያደረገው የኤርትራ መንግሥት ተቃዋሚ ድረ ገጽ እንደጻፈው፣ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ከወትሮው በተለየ ከመገናኛ ብዙኃን ርቀዋል፡፡ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ለመጨረሻ ጊዜ በሚዲያ የታዩት ጥቅምት 1 ቀን 2006 ዓ.ም. በተካሄደው የምሥራቅ አፍሪካ የአንበጣ መቆጣጠሪያ ድርጅት የሚኒስትሮች ምክር ቤት 58ኛ ጉባዔ ላይ መሆኑን ድረ ገጹ ጽፏል፡፡
ከዚያም በጥቅምት 20 ቀን 2006 ዓ.ም. በጉበት ሕመም ምክንያት አስመራ በሚገኘው የአየር ኃይል ሐኪም ቤት ለስድስት ሰዓታት ያህል ሕክምና ተደርጐላቸው  ወደ ቤተ መንግሥት መመለሳቸውን ጽፏል፡፡ በመቀጠልም ወደ ሳዑዲ ዓረቢያ ወይም ኳታር ለተጨማሪ ሕክምና መሄዳቸው እንዳልቀረ አትቷል፡፡
ስለ ጉዳዩ የፕሬዚዳንት ኢሳያስ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ የማነ ገብረመስቀልን በትዊተር ገጻቸው ለሪፖርተር ማብራሪያ እንዲሰጡ ለቀረበላቸው ጥያቄ፣ «አስቂኝ ቅዠት ነው» የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
«ፕሬዚዳንቱ በመልካም ጤንነት ላይ ናቸው፤» በማለት መሠረተ ቢስ የሆነ ወሬ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡ «ምንም አዲስ ነገር የለም፡፡ አስማሪኖ ውሸት ማውራት ስለፈለገ ነው፡፡ ማንኛውንም የአስመራ ነዋሪ መጠየቅ ይቻላል፤ ምክንያቱም ፕሬዚዳንቱ ወደ ቢሮአቸው ሲገቡ ያዩአቸዋል፤» ብለዋል፡፡
 ከዚህ ቀደም ከሚያዝያ 4 ቀን 2004 ዓ.ም. ጀምሮ ከአንድ ወር በላይ ከመገናኛ ብዙኃን መጥፋታቸው መነጋገሪያ እንደነበር ይታወቃል፡፡ 
በተያያዘ ዜናም የአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት የቆንስላ ጉዳዮች ቢሮ ከትላንት በስቲያ ባወጣው መግለጫ፣ የአሜሪካ ዜጎች ወደ ኤርትራ ምንም ዓይነት ጉዞ እንዳያደርጉ ጠንከር ያለ ማሳሰቢያ ሰጥቷል፡፡ በአገሪቷ ላይ የሚታየውን የፀጥታ ችግር እንደ ምክንያት በመግለጽ ከአሁን በፊት በግንቦት 2 ቀን 2005 ዓ.ም. ያወጣውን የጉዞ ማዕቀብ ማስጠንቀቂያ አጠናክሯል፡፡
ስቴት ዲፓርትመንት በመግለጫው እንዳስታወቀው፣ የአሜሪካና የኤርትራ ድርብ ዜግነት ያላቸው ግለሰቦች ያለምንም ምክንያት እየታሠሩ ነው፡፡ በተጨማሪም በመርከብ የሚጓዙ የአሜሪካ ዜጎች በኤርትራ የባህር ዳርቻ እንዳይጓዙና መልህቆቻቸውን እንዳይጥሉ ጠንከር ያለ ማሳሰቢያ አስተላልፏል፡፡ 
የኤርትራ መንግሥት መቀመጫው ሶማሊያ ለሆነው የአልሸባብ አክራሪ ቡድን ድጋፍ ያደርጋል በማለት የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት በታኅሳስ 14 ቀን 2002 ዓ.ም. የመሣሪያ ማዕቀብ መጣሉ ይታወቃል፡፡ የተባበሩት መንግሥታት የሶማሊያና የኤርትራ አጣሪ ኮሚቴ ግን የኤርትራ መንግሥት ለአልሸባብ «ቀጥታ» ዕርዳታ እንደማያደርግ ሐምሌ 9 ቀን 2004 ዓ.ም. አስታውቋል፡፡
Source: http://www.ethiopianreporter.com
 
ሙሉውን አንብብ-Read More

የኢትዮጵያውያን ከሳ/አረቢያ መውጣት ያስከተለው ችግር

Geez Bet | Thursday, November 21, 2013
እአአ ከ 610 ዓ ም ጀምሮ የእስልምና ኃይማኖት መገኛ እና ማስፋፊያ ማዕከል በመሆን ትታወቃለች። በማዕከላዊው ምስራቅ በፋርስ ባህረ ሰላጤ እና በቀይ ባህር መካከል በተንጣለለው የዓረቢያ በረሃ ላይ ጆርዳን ኢራቅ ኩዌት የመን ኦማን ቀጠር እና የተባበሩት ኣረብ ኢማራት በምድር ያዋስኗታል። 
ቀድሞ ኢትዮጵያ ኣሁን ግን ከኤርትራም ጋር የባህር ማዶ ጎረቤት ናቸው። ኣሁን ያለውን ኣገራዊ ቅርጽ ይዛ በኣዲስ መልክ እንደ መንግስት የቆመችው ከ 1818 ዓ ም ጀምሮ ሲሆን ስያሜዋንም ያገኘችው እ ኣ ዘ ኣ በ 1932 ዓ ም በንጉስ አብዱልአዚዝ አል ሳዑዲ ኣማካኝነት በንጉሱ የቤተሰብ ስም ተሰይማ መሆኑ ይተረክላታል። ሳዑዲ ዓረቢያ።
በነዳጅ ዘይት ምርቷ በዓለም ቀዳሚነቱን ይዛ የምትገኘው ሳውዲ ኣረቢያ የቆዳ ስፋቷ 2 ሚሊየን ስ ኪ ሜ ገደማ ሲጠጋ በ2010 በተካሄደ ቆጠራ መሰረት 27,5 ሚሊየን ያህል ህዝብም ኣላት። ከእነዚህ መካከል 19 ሚሊየኑ ብቻ የሳውዲ ዜጎች ሲሆኑ ቀሪው ስምንት ሚሊየን ደግሞ በተለያዩ ጊዜና ሁኔታዎች ወደ ኣገሪቱ የገቡ የውጪ ዜጎች መሆናቸው ነው። ከእነዚህም መካከል ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ህጋዊ የኣገር መኖሪያ እንደሌላቸው ሲገመት ለሰሞኑ ኣስደንጋጭ ክስተትም ምክኒያት የሆነው ዘገባዎች እንደሚያመለክቱት እነዚህኑ ስደተኞች የማስወጣቱ ዘመቻ ነው።
ጤና ይስጥልኝ የተወደዳችሁ የዶቸቬሌ ታዳሚዎች በዕለቱ የማህደረ ዜና ዝግጅታችንም ይህንኑ ዘመቻ ከኢትዮጵያ ኣንጻር ለመዳሰስ እንሞክራለን።
ዘውዳዊው የሳውዲ አረቢያ መንግስት በዚህ ጊዜ የዚህ ዓይነት ግራ የተጋባ ጭፍን እርምጃ ለመውሰድ የተገደደው ቅርበት ያላቸው ምንጮች እንደሚጠቁሙት ካለፉት ሁለት ዓመታት ወዲህ በዓረቡ ዓለም የተቀጣጠለውን እና ከቱዚያ ጀምሮ ሊቢያን እና ግብጽን ያናወጠውን እንዲሁም በጎረቤት የመን ኣድርጎ እስከ ኣሁንም ሶርያን በማተራመስ ላይ ያለውን ብሶት ወለድ የዓረብ ኣብዮት ተከትሎ ከወዲሁ ለዜጎቿ የስራ ዕድል ለመክፈት ታስቦ ነው ተብሏል።
በዚሁ መሰረት የሪያድ ኣገዛዝ ህጋዊ የመኖሪያ እና የስራ ፈቃድ የሌላቸው የውጪ ዜጎች ኣንድም ሰነዶቻቸውን እንዲያስተካክሉ ኣልያም ኣገሪቱን ለቀው እንዲወጡ የ ሰባት ወር የእፎይታ ጊዜ መስጠቱ ይታወሳል። በዚህ ጊዜ ውስጥም በሳውዲ ምንጮች መረጃ መሰረት 4 ሚሊየን ያህል የውጪ ዜጎች ሰነዶቻቸውን ኣስተካክሏል። 1 ሚሊየን ገገማ ደግሞ ኣገሪቱን ለቀው መውጣታቸው ታውቐል።
የተጠቀሰው የምህረት ጊዜ ያበቃው እ ኣ ዘ ኣ ባለፈው ህዳር 3 ቀን ሲሆን ወዲያውኑ በሺዎች የሚቆጠሩ የሳውዲ ፖሊሶች በእነሱ ኣጠራር ሹርጣዎች በየአካባቢው ተሰማርተው የውጪ ዜጎችን ማሳደድ ጀመሩ። ምንም እንኩዋን እንደ ወትሮው ወደ ጎዳና የወጣ ስደተኛ ባይኖርም በስራ ቦታው እና ከየመኖሪያ ቤቱም እየገቡ ስደተኞችን ማደኑ ቀጠለ። ኣያያዙም ኃይል የተቀላቀለበት እና ስደተኞቹ እንደሚሉት ፍጹም ጭካኔ የተሞላበት ነው የነበረው።
ከፖሊስ ኃይሉ በተጨማሪ ግርግር ለሌባ ያመቻል እንዲሉ ጋጠ ወጥ የሳውዲ ወጣቶች የፖሊሶቹን ዱካ እየተከተሉ እና ቤት ሰብረው እየገቡ ገንዘብ እና ንብረት መዝረፍ ወንዶችን መደብደብ እና ሴቶችን መድፈሩን ተያያዙት። ምንም እንኩዋን ከየአቅጣጫው የሚወጡት ዘገባዎች እርስ በርሳቸው የሚጣለዙ ቢሆኑም እስከኣሁን በመቶዎች የሚቆጠሩ የአካል ጉዳት ደርሶባቿል። ጥቂት የማይባሉ ደግሞ ህይወታቸውን ኣቷል።
ይህ ሁሉ ሲሆን ግን ከስደተኞቹ አንደበት መረዳት እንደተቻለው ማሳደዱም ሆነ ጭካኔው የበረታው በተለይ በኢትዮጵያውያኑ ላይ ነው ተብሏል።
የሴቶቹ እሮሮ ደግሞ በእርግጥም ለየት ያለ እና ዘግናኝም ነው።
የሴት ኢትዮጵያውያን መደፈር በአሰሳው ወቅት በሚደርስባቸው ብቻም ኣልተወሰነም። ተይዘው ወደ ማጎሪያ ካምፕ ከተወሰዱ በኃላም ከካምፑ ተሰርቀው ይወሰዳሉ ተብሏል።
በዚያ ላይ የማጎሪያ ካምፑ እስረኞችም ቢሆኑ ለበረኃ ግመሎች ካልሆነ በስተቀር የሰው ልጅ ማቆያ ኣይመስልም የሚሉት የሪያድ እስረኞች ከዚሁ የተነሳ በርካታ ህጻናት እና እናቶች መታመማቸውንም ይናገራሉ።
በዚህ ጭፍን ዘመቻ ወቅት እጅግ ኣነጋጋሪ ከሆኑት ነገሮች መካከል የሳውዲ ወጣቶች በነቂስ ወተው ፖሊሶችን መከተል እና ስደተኞችን መዝረፍ መደብደብ እና በተለይ ሴቶችን የመድፈሩ ጉዳይ ነው።
የተገደሉትን ስደተኞች ቁጥር ኣስመልክቶም ከኢትዮጵያ እና ሳውዲ መንግስታት የወጡ ዓኃዞች ከሞላ ጎደል ተቀራራቢ ቢሆኑም ዘገባዎች ግን ቁጥሩ ሊጨምር እንደሚችል ይጠቁማሉ።
«ነሲም በተባለች ከዚህ ከሪድ ኣንድ 30 እና 50 ኪ ሜ ርቃ በምት ገኘው ከተማ ባለፈው ሐሙስ ምሽት የሳውዲ ፖሊሶች ግርግር ፈጥረው 3 ሰዎችን ገግሏል። ሶስቱም ኢትዮጵያውያን ናቸው። ብዙ ሰው እኮ ነው የተገደለብን። ሰው ሲገደል ወዲያውኑ ኣንስተው ወደማይታወቅበት ቦታ ስለሚወስዱት ለጊዝው ኣይታወቅም እንጂ በጣም ብዙ ሰው ነው የተገደለው። እኔ እራሴ የማውቃቸው ከአስር ሰው በላይ እገሌ እገሊት ብዬ ልቆጥርልህ እችላለሁ።»
እስከ ኣሁን ከ 3000 በላይ ስደተኞች ኣገር ቤት ደርሷል እየተባለ ባለበት በኣሁኑ ወቅትም ከተደበቁበት ገና ያልወጡ እና ባሉበትም በረኃብ እየተቸገሩ ያሉም እንዳሉ ለማወቅ ተችሏል።
ለዚህ ጭፍን እርምጃ የሳውዲ አረቢያን መንግስት መኮነናቸው ባይቀርም ስደተኞቹም ሆኑ በርካታ ኢትዮጵያውናን ይበልጥ የሚያማርሩት ግን ሪያድ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ኢምባሲን እና የኢትዮጵያን መንድስትም ጭምር ነው ነው።
የኢትዮጵያ መንግስት ይህንን ጉዳይ ከልብ እያየው ኣይመስለንም። እንዲያውም ውስጥ ውስጡን ከሳውዲዎች ጋር እየሰራ ያለ ነው የሚመስለው የኢትዮጵያ መንግስት። ኢምባሲው በተለይ ልክ የዚህ ኣገር ፖሊሶች ገድለው ኣስክሬን እንደሚደብቁት እሱም አብሮ እየደበቀ ነው እንጂ ይህንን ጉዳይ ፈጽሞ በትኩረት እያየው ኣይደለም።
የሳውዲዎች ዘመቻ በተለይ በኢትዮጵያ ስደተኞች ላይ ማተኮሩን ኣስመልክቶ የኢትዮጵያው የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር እርምጃውን ማውገዙ የሚታወስ ሲሆን ቃል ኣቀባዩ ኣምባሳደር ዲና ሙፍቲ ዛሬ ለዶጨቤሌ እንደገለጹት ስደተኞቹን ወደ ኣገራቸው የመመለሱ ሂደት በተቻለፍጥነት እየሄደ ነው።
የሆነ ሆኖ በሪያድ የኢትዮጵያ ኢምባሲም ሆነ ከአዲስ ኣበባም የኃይለማሪያም ደሳለኝ ኣስተዳደር በኣጠቃላይ ከዘመቻው በፊትም ሆነ ከዚያ ወዲህ ዜጎቹን ለመታደግ የወሰዷቸው እርምጃዎች በቂ ኣይደሉም ሲሉ ብዙዎች ይከሳሉ። በዚሁ ምክኒያት ጭምር ይመስላል በዓለም ዙሪያ ያሉ ኢትዮጵያውያን ከዚያ ወዲህ በቁጣ ገንፍለው ዋሽንግተን ዲ ሲ ን ጨምሮ በተለያዩ የአሜሪካ እና የኣውሮፓ ከተሞች አደባባይ ወቷል። ወደ ሳውዲ ኢምባሲ እየሄዱም ተቃውሞኣቸውን ኣሰምቷል።
በኣገር ቤት የሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችም ኣድራጎቱን በመኮነን መግለጫ ኣውጥቷል። ባለፈው ዓርብ ስማያዊ ፓርቲ የጠራው ሰልፍ ግን አዲስ ኣብባ ላይ ልክ እንደ ሪያድ በሳውዲ ፖሊስ ሳይሆን ግን በኢትዮጲያ ፖሊሶች እርህራሄ በሌለው ድብደባ መበተኑ በኣሳኝነቱ ተዘግቧል።
በተያያዘ ዜና የሰሞኑ የሳውዲ አረቢያ እርምጃ ታሪካዊ ስህተት ነው የሚሉ ወገኖችም ኣሉ። ኣንዱም ሼክ ነጂብ መሐመድ ሲሆኑ በዋሽንግተን ዲ ሲ የሚኖሩት ሼክ ነጂብ በኣሁኑ ጊዜ « ዘ ፈርስት ሂጂራ» የተባለው ዓለም ዓቀፍ መንግስታዊ ያልሆነ የኢትኆጵያውያን እስላማዊ ተቐም መሪ ናቸው።
በእስልምና ኃይማኖት እንግዳ ይከበራል እንጂ ኣይነካም የሚሉት ሼክ ነጂብ በእስላማዊው የሸሪኣ ህግ እመራለሁ የሚለው የሳውዲ ኣገዛዝ ይህንን በማድረጉ ተጠያቂ ከመሆን ኣያመልጥም ይላሉ።
ጃፈር አሊ
አርያም ተክሌ
Source: www.dw.de

ሙሉውን አንብብ-Read More

Nov 17, 2013

ሰማያዊ ፓርቲ የጠራው ሰላማዊ ሰልፍ በፀጥታ ሀይሎች ከሸፈ

Geez Bet | Sunday, November 17, 2013
በርካታ ሰዎች ተደብድበዋል በላንቻ ፖሊስ ጣቢያ ከ70 በላይ ሰዎች ታስረዋል
በሳኡዲ አረቢያ በኢትዮጵያዊያን ላይ እየደረሰ ያለውን ግድያና እንግልት ለመቃወም በትላንትናው እለት ሰማያዊ ፓርቲ ጠርቶት የነበረው ሰላማዊ ሰልፍ በፀጥታ ሀይሎች የከሸፈ ሲሆን፤ ለሰልፉ የወጡት ሰዎች፣ መንገደኞች፣ በተለያየ ምክንያት ጥቁር የለበሱና ሌሎችም ድብደባ ደርሶባቸዋል፡፡ ጋዜጠኞችን ጨምሮ ከሰባ በላይ ሰዎች በላንቻ ፖሊስ ጣቢያ ታስረዋል፡፡
በድብደባው ሲቪል የለበሱ የፀጥታ ሃይሎችም እንደተጐዱ የላንቻ ፖሊስ ጣቢያ ሀላፊ ገልፀዋል፡፡ ሰልፉን የጠራው ፓርቲ አመራሮች ከፅፈት ቤታቸው ሳይወጡ መታሰራቸው የተሰማ ሲሆን የሳኡዲ አረቢያ ኤምባሲ አካባቢ በፌደራል እና በአዲስ አበባ ፖሊስ ተከቦ ውሏል፡፡ ወደ ኤምባሲው የሚጠጋ፣ ሰብሰብ ብሎ የቆመ፣ ፎቶ ሲያነሳ የተገኘና ሌሎችም በፖሊስ ነጭ ፒክ አፕ መኪና እየተጫኑ ላንቻ አካባቢ በሚገኘው የወረዳ 18 ፖሊስ የተወሰዱ ሲሆን፤ ፖሊስ ጣቢያ ከገቡት ውስጥ የ70 አመት አሮጊት እና የ62 አመት አዛውንት ይገኙበታል፡፡
“ምንም የማውቀው ነገር የለም፤ ከልጄ ጋር መንገድ እየሄድኩ ነው የተያዝኩት” ብለዋል፤ የ70 ዓመቷ አሮጊት፡፡ ከታሰሩት መካከል በድብደባ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት ኢዮብ አርጋው የተባለ ወጣት፤ አብረውት በታሰሩት ሰዎች ጉትጐታና ለቅሶ ፖሊስ ለህክምና ወደ ሆስፒታል ወስዶታል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ ረቡዕ ማታ በሰጠው መግለጫ፤ በሰላማዊ ሰልፉ ላይ አራት ዋና ዋና ነገሮች እንደሚከናወኑ ገልፆ ነበር፡፡ ሰላማዊ ሰልፍ የሚወጡ ሁሉ በሳኡዲ የሞቱትን፣ የታሰሩትን እና የአካል ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች ለማሰብና ሀዘናቸውን ለመግለጽ ጥቁር እንዲለብሱና ጥቁር ሪቫን ክንዳቸው ላይ እንዲያስሩ፣ ሙስሊሙ በዕለቱ በጁምአ ሶላት እንዲፀልይ እንዲሁም፣ በሳኡዲ ኤምባሲ በር ላይ ተቃውሞ ከመሰማቱ በፊት ለሞቱት የህሊና ፀሎት ለማድረግና በሳኡዲ አረቢያ እየደረሰ ስላለው አጠቃላይ ጉዳት የሚያትት በመረጃ ላይ የተመሰረተ ጽሑፍ ቀርቦ ሰልፉ እንደሚበተን ገልፆ ነበር።
ሰላማዊ ሰልፉን ለማካሄድ ፓርቲው ለከተማው መስተዳድር በደብዳቤ ማሳወቁን እና መስተዳድሩ ምላሽ አለመስጠቱን፤ ይህ ደግሞ ሰልፉ መፈቀዱን የሚያሳይ እንደሆነ ኢ/ር ይልቃል ቀደም ብለው ገልፀው ነበር፡፡ የፓርቲው አባላት እንደገለፁት፤ የፓርቲው ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃልን ጨምሮ ሌሎች አመራሮች ለሰልፉ ከፓርቲው ጽ/ቤት ሳይወጡ ነው በፖሊስ የተወሰዱት፡፡ በስፍራው ተገኝተን እንደታዘብነው “ልጆቻችን ታረዱ ተገደሉ” እያሉ የሚያለቅሱ እናቶች የነበሩ ሲሆን “ፖሊስ በህዝቡ ላይ ድብደባና እንግልት ማድረሱ አግባብ አይደለም፤ ይህ ኢትዮጵያ ሳይሆን ሳኡዲ ማለት ነው” ሲሉም ተደምጠዋል፡፡ “ፎቶ አንስታችኋል” በሚል ከሌሎች ሰዎች ጋር በፖሊስ ተይዘው ወረዳ 18 ላንቻ ፖሊስ ጣቢያ ከስድስት ሰዓት እስከ ስምንት ተኩል ቆይተዋል፡፡
በፖሊስ ጣቢያው ውስጥ ከነበሩት መካከል አብዛኞቹ መንገደኞችና ስለጉዳዩ ምንም እንደማያውቁ ተናግረዋል፡፡ ከቀኑ ስምንት ሰዓት አካባቢ ጋዜጠኞች ብቻ ተጠርተን የጣቢያው ሃላፊ ያነጋገሩን ሲሆን፤ “ሰልፉ አልተፈቀደም፣ ህገወጥ ነው፤ ህዝቡ ኤምባሲውን ሰብሮ ሊገባ ሲል ዝም ብሎ ማየት አይቻልም፣ ነገሩን በክፉ አትዩት ጉዳዩን የኢትዮጵየ መንግስትና የአለም መንግስታት እየተከታተሉት ነው” በማለት ካሜራችንን እና መታወቂያችንን የመለሱልን ሲሆን አንድ ጋዜጠኛ በሞባይሉ ያነሳውን ፎቶ እንዲያጠፋ ተደርጐ ተለቀናል፡፡ ፖሊስ ጣቢያው ውስጥ የነበሩ ከ70 በላይ ሰዎች ማተሚያ ቤት እስክንገባ ድረስ በእስር ላይ እንደነበሩ የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡
Soorce: http://www.addisadmassnews.com

ሙሉውን አንብብ-Read More

Nov 16, 2013

የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት እርማጃና ተቃዉሞዉ

Geez Bet | Saturday, November 16, 2013
አዲስ አበባ ላይ በሳዑድ አረቢያ ኤምባሲ አጠገብ ሊካሄድ የነበረ የተቃዉሞ ሰልፍ በፖሊስ ተበተነ። አሶሲየትድ ፕረስ እንደዘገበዉ ፖሊስ በመቶዎች የሚቆጠሩን ሰልፈኞች ለመበታተን ኃይል ተጠቅሟል። 
  መንግስት ፈቃድ እንዳልተሰጠዉ በማመልከት ቁጥራቸዉን ባይጠቅስም የታሰሩ መኖራቸዉን ገልጿል። ሰልፉን ያስተባበረዉ የተቃዉሞ ወገን ሰማያዊ ፓርቲ በበኩሉ ሁለት ሊቃነመናብርቱን ጨምሮ አንድ መቶ ሰዎች ገደማ መያዛቸዉን አመልክቷል። የመንግስት ቃል አቀባይ አቶ ሽመልስ ከማል ፀረ አረብ ስሜት ሊፈጥር የሞከረ ያሉት ተቃዉሞ ሰልፍ አዘጋጆች ከሚመለከተዉ አካል ፈቃድ ባለማግኘታቸዉ እንደሚከሰሱ ለአዣንስ ፍራንስ ፕረስ ገልጸዋል። በፖሊስ ከተደበደቡት አንዱ እንደሆነ የገለጸዉ፤ አስፋዉ ሚካኤል መንግስት የሳዉዲ አረቢያን ድርጊት ላይ የቀረበዉን ተቃዉሞ ለምን ማገድ እንደፈለገ እንዳልገባዉ ለዜና ወኪሉ ገልጿል።
ዘገባዉ አክሎም ፖሊስ አንዳንድ ጋዜጠኞች ያነሱትን ፎቶግራፍ መደምሰሱንም አመልክቷል። የመንግስት ቃል አቀባይን አስተያየት ማግኘት እንዳልተቻለም ተገልጿል። ለተለያየ ሥራ ሳዑድ አረቢያ የሚገኙ የዉጭ ዜጎች ሕጋዊ መኖሪያ ፈቃድ እንዲያወጡ የተሰጠዉ የጊዜ ገደብ ካለቀ ወዲህ እዚያ ያሉ ኢትዮጵያዉያን ጥቃት እየደረሰባቸዉ እንደሚገኝ እየገለፁ ነዉ።
የአዲስ አበባ ነዋሪዎችም፥ በኢትዮጵያዉያን ላይ የሚፈፀመዉን በደል በመቃወም ዛሬ አዲስ አበባ በሚገኘዉ የሳዑዲ አረቢያ ኤምባሲ አጠገብ አደባባይ ወጥተዉ ነበር።ይሁንና የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር የጠቀሰዉ ጋዜጠኛ እንዳለዉ ሳዑዲ አረቢያ ዉስጥ በኢትዮጵያዉያን ላይ የተፈፀመዉ አዲስ አበባም ተደገመ።
የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት በሐገሩ በሚኖሩ ኢትዮጵያዉን ላይ የሚያደርሠዉን በደል፥ በተለያዩ ሐገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን በአደባባይ ሠልፍ እያወገዙት ነዉ።ትናንት እዚሕ ጀርመን የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ፍራንክፈርት ዉስጥ ባደረጉት ሠልፍ የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት ኢትዮጵያዉያኑን፥ ማንገላታት፥ ማሠር፥ መደብደብ መግደሉን እንዲያቆም፥ የኢትዮጵያ መንግሥትም የዜጎቹን መብት እንዲያስከብር ጠይቀዉ ነበር።የአዲስ አበባ ነዋሪዎችም፥ በኢትዮጵያዉያን ላይ የሚፈፀመዉን በደል በመቃወም ዛሬ አዲስ አበባ በሚገኘዉ የሳዑዲ አረቢያ ኤምባሲ አጠገብ አደባባይ ወጥተዉ ነበር።
ይሁንና የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር የጠቀሰዉ ጋዜጠኛ እንዳለዉ ሳዑዲ አረቢያ ዉስጥ በኢትዮጵያዉያን ላይ የተፈፀመዉ አዲስ አበባም ተደገመ።ሠልፈኞቹ ተቃዉሟቸዉን ለማሰማት ገና ከመሠብሰባቸዉ ፖሊስ ደብድቦ አብዛኞቹን በተነ፥ የተቀሩትን አሠረ።ዮሐንስ አጭር ዘገባ ልኮልናል።
ዩናይትድ ስቴትስ ርዕሠ-ከተማ ዋሽግተን-ዲሲ እና አካባቢዋ የሚኖሩ በርካታ ኢትዮጵያዉያንም የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት በኢትዮጵያዉያን ላይ የሚወስደዉን እርምጃ በአደባባይ ሠልፍ አዉግዘዋል። የዋሽግተኑ ወኪላችን አበበ ፈለቀ እንደዘገበዉ ትናንት የተጀመረዉ የአደባባይ ሠልፍና ዉግዘት በተለያዩ የሰሜን አሜሪካ ከተሞችም ይቀጥላል።
የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት ኢትዮጵያዉያንን ጨምሮ በሕገ-ወጥ መንገድ የሚኖሩ የዉጪ ሐገር ዜጎችን ከሐገሩ ማባረሩን ዛሬም እንደቀጠለ ነዉ። የጂዳዉ ወኪላችን ነብዩ ሲራክ እንደነገረን በኢትዮጵያዉያንና በሳዑዲ አረቢያ ዜጎች መካካል ሰሞኑን ተከስቶ የነበረዉ ደም አፋሳሽ ግጭት ዛሬም ጋብ ብሏል።ከዚሕ ቀደም ኮንትራታቸዉ ተቋርጦ፥ ቀጣሪዎቻቸዉ ጠፍተዉ፥ ወይም ታመዉ ጂዳ ኢትዮጵያ ቆንስላ ዉስጥ ለወራት ተጠልለዉ የነበሩ ኢትዮጵያዉያንም ወደ ሐገራቸዉ ለመመለስ ማቆያ ጣቢያ ገብተዋል። ነብዩን ከአንድ ሠዓት በፊት በስልክ አነጋግሬዋለሁ። የመጀመሪያዉ ጥያቄዬ ምን አዲስ ነገር ---የሚል ነበር።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር/ አበበ ፈለቀ
ነብዩ ሲራክ/ ነጋሽ መሐመድ
አርያም ተክሌ
Source: www.dw.de
 
ሙሉውን አንብብ-Read More

Nov 14, 2013

በሳውዲ አረቢያ የኢትዮጵያውያን ስቃይ

Geez Bet | Thursday, November 14, 2013

በሳውዲ አረቢያ የኢትዮጵያውያን ስቃይ

ሳዉድ አረቢያ የሚገኙ ኢትዮጵያዉያን ዛሬም የድረሱልን ድምጻቸዉን እያሰሙ ነዉ። የሀገሪቱ መንግስት ላለፉት ወራት ሰጥቶ የቆየዉ የምህረት ቀነገደብ ካለፈ ወዲህ በዜጎችና የጸጥታ ኃይሎች ይፈጸምብናል የሚሉት በደልም ገደብ ማለፉን ይናገራሉ።
በሕጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ ከ24ዓመታት በላይ እዚያ እንደኖሩ ለዶቼ ቬለ የገለጹት አንድ ዜጋ ደግሞ ኢትዮጵያዉያኑ ላይ ሀገሬ የሚያሳየዉ ጥላቻ ዛሬ አልተጀመረም ባይናቸዉ። ከያሉበት ታፍሰዉ በመጠለያ ስፍራ እንደተሰበሰቡ ያመለከቱ ወገኖች ደግሞ ኤምባሲዉ አልደረሰልንም፤ ካለንበት የሚያወጣን አጣን ይላሉ።

ከእነልጆቻቸዉ ታፍሰዉ መጠለያ ከተከተቱ እናቶች አንዷ ናቸዉ። እንባቸዉን እየታገሉ የሚሉት አንድ ነገር ነዉ፤ ድሃም ብትሆን ሀገር አለን። ዘገባዎች እንደሚያመለክቱት በርካቶች በአዉቶብስ ያለ ሕጋዊ መኖሪያ ፈቃድ ሀገሪቱ ዉስጥ የተገኙትን የተለያዩ ሀገር ዜጎች በመሰብሰብ ወደመጠለያ ስፍራ ያጓጉዛሉ። በስልክ ያነጋገርኳቸዉ ኢትዮጵያዉያን የት ቦታ እንዳሉ ማወቅ እንደተሳናቸዉ ቢናገሩም ወንዶችና ሴቶችን ለየብቻ ተደርገዉ በመጠለያ መታጎራቸዉን ገልጸዉልኛል። ሴቶቹ ሶስት ሺህ እንሞላለን ባዮች ናቸዉ። ይህንም በአንድ አካባቢ ብቻ መሆኑ ነዉ። እዚህ ቦታ ካሉት አንዷ እሷ ብቻ ሳትሆን ሌሎችም በተሰባሰቡበት መጠለያ ስፍራ ባለዉ መጥፎ ሽታ ምክንያት ድምፃቸዉ መዘጋቱን ለበሽታም መዳረጋቸዉን ገልጻልኛለች። ወንዶች ትላለች ወጣቷ ከአረብ ወጣቶች ጋ ጸብ ዉስጥ ገብተዋል። እንደእሷ ገለጻም ሸባቦቹ ግራ የተጋቡትን ኢትዮጵያን ሴቶች ባገኙበት አስገድደዉ ይደፍራሉ፤ ከመጠለያዉም አፍነዉ ይወስዳሉ።
ወደሳዉዲ ከተሻገረ ብዙም ወራት እንዳልሆነዉ የገለፀልኝ ከስልጤ ነዉ የመጣሁት ያለኝ ሽፋ ሸምሱ ደግሞ ወደሀገሩ ለመመለስ ተዘጋጅቷል፤ ግን ወደአዉሮፕላን ማረፊያ ይወስዳችኋል የተባለዉን አዉቶብስ መጠበቅ ቀጥሏል የተባለዉ ግን የለም ይላል።
ሳዉዲ ዉስጥ ኢትዮጵያዉያን ብቻ ሳይሆን በርካታ የዉጭ ዜጎች በሠራተኝነት ይገኛሉ። መንግስት ሕጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ ለሌላቸዉ በሰጠዉ የምህረት ጊዜ የተጠቀሙ የባንግላዴሽ፤ ፊሊፒንስ፤ ህንድ፤ ኔፓል፤ ፓኪስታንና የመን ዜጎች ቁጥር በርካታ መሆኑን ዘገባዎች ያመለክታሉ። እንደአዣንስ ፍራንስ ፕረስ ዘገባ ከሆነም ወደአንድ ሚሊዮን ገደማ የሚሆኑ ተጠሪ የሚሆኗቸዉ ቀጣሪዎች አግኝተዋል። ዘጋቢዎች ያነጋገሯቸዉ ኢትዮጵያን ግን ለዓመታት ያፈሩትን ንብረት በርካሽ ለመሸጥ ተገደዋል ገሚሱንም ለሰዎች ሰጥተዋል። በእጅ የቋጠሯትን ገንዘብም መኖሪያ ፈቃድ ለማስተካከል በደላልነት ለቀረቧቸዉ የሳዉዲ ብልጣብልጦች አጉርሰዋል። ተስፋ ያደረጉትን ግን አላገኙም።
በሺዎች የሚቆጠሩ አፍሪቃዉያን ስደተኞች በሳዉዲ መንግስት ኃይሎች ታስሰዉ ቢያዙም የኃይል ጥቃቱ የበረታዉ ኢትዮጵያዉያኑ ላይ ነዉ ይላሉ እዚያ የሚገኙት ወገኖች።
ሳዉዲ የሚገኙ ወገኖች ዛሬም ኤምባሲዉ ላይ የሚያቀርቡት ቅሬታና ለመንግስትም የሚያቀርቡትን አቤቱታ በማስመልከት ከዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ምላሽ ለማግኘት ያደረግነዉ ተደጋጋሚ ሙከራ ባለመሳካቱ የባለስልጣናቱን ሃሳብ ማካተት አልቻልንም።
ከሃገሪቱ መውጣት ያልቻሉ ዜጎች በዋና ከተማይቱ በሪያድና በሌሎችም ከተሞች በጎዳናዎች ላይ እየወጡ መንግሥት በአስቸኳይ ወደ ሃገራችው እንዲልካቸው ሲጠይቁ ከየአካባቢዎቹ ነዋሪዎች ጋር መጋጨታቸውን የጂዳው ወኪላችን ነብዩ ሲራክ ዘግቧል ።
በርካታ ኢትዮጵያውያን ዛሬም ሳውዲ አረቢያ ውስጥ በመሰቃየት ላይ መሆናቸውን እየተናገሩ ነው ። እነዚሁ ከሃገሪቱ መውጣት ያልቻሉ ዜጎች በዋና ከተማይቱ በሪያድና በሌሎችም ከተሞች በጎዳናዎች ላይ እየወጡ መንግሥት በአስቸኳይ ወደ ሃገራችው እንዲልካቸው ሲጠይቁ ከየአካባቢዎቹ ነዋሪዎች ጋር መጋጨታቸውን የጂዳው ወኪላችን ነብዩ ሲራክ ዘግቧል ። ሳውዲ አረቢያ ውስጥ ያለህጋዊ የስራና የመኖሪያ ፈቃድ የሚኖሩ የውጭ ዜጎች ህጋዊ ሰነድ እንዲያወጡ አለያም ወደ ሃገራቸው እንዲመለሱ መንግሥት የሰጠው የምህረት ቀነ ገደብ ካበቃ ዛሬ 10ኛ ቀኑን ይዟል ። በነዚህ 10 ቀናት ውስጥ ወደ 23 ሺህ የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን ለሳውዲ መንግሥት እጃቸውን መስጠታቸው ተዘግቧል ። የጂዳውን ወኪላችንን ነበዩ ሲራክን ስለ አጠቃላዩ ሁኔታ በስልክ አነጋግሬዋለሁ ።

ሸዋዬ ለገሠ / ነበዩ ሲራክ
ሂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ

Source: www.dw.de
ሙሉውን አንብብ-Read More

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በIMF እይታ

Geez Bet | Thursday, November 14, 2013
የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ኣስመልክቶ ላለፉት 9 እና 10 ዓመታት በተለይ ከመንግስት በኩል የሚሰማው እጥፍ ድርብ እድገት ወይንም በእንግሊዝኛው Double digit grorth ያውም ከ 11 በመቶ ያላነሰ ወይንም ከዚያ በላይ መሆኑ ይታወቃል። ተቃዋሚዎች በዚያች ኣገር ያንን ያህል እድገት ያውም በኢህኣዲግ የእጅ ኣዙር እዝ ኢኮኖሚ የማይታሰብ ነው እያሉ

ማጣጣላቸው ባይቀርም የዓለም ባንክ እና ዓለም ዓቀፉ የገንዘብ ተቐም IMF ግን ሙሉ በሙሉም ባይሆን የመንግስትን የዕድገት ብስራት የሚጋሩት ይመስላል። የመንግስት ባለስልጣናት ለተባለው እድገት በየዘርፉ እና በየአካባቢው እየተገነቡ ያሉ የመሰረተ ልማት ኣውታሮቶችን እና የዜጎች የነፍስ ወከፍ ገቢ መሻሻሉን እንደ ማስረጃ ሲያቀርቡ ተቃዋሚዎች እና ኣንዳንድ ገለልተኛ የሆኑ ባለሙያዎችም እንዲሁ ከወረቀት ኣልፉ መሬት ላይ ያረፈ እና የህብረተሰቡን ኑሮ የቀየረ እድገት ኣላታየም ሲሉ በተቃራኒው ይከራከራሉ። የዓለም ባንክ እና ዓለም ዓቀፉ የገንዘብ ተቐም IMF በበኩላቸው በኢትዮጵያ መጋነኑ ባይቀርም ነገር ግን ፈጣን እድገት መኖሩን እና በተወሰነ ደረጃም ቢሆን ደግሞ የህዝቡ ኑሮም እየተቀየረ መሆኑን ይመሰክራሉ።
የተለመደው የኢኮኖሚ እድገት መለኪያ ባለሙያዎችም እንሚሉት ኣጠቃላይ የኣገር ውስጥ ገቢ እና ምርት ዕድገት ሲሆን የኢትዮጵያ መንግስትም በአብዛኛው በዓማካኝ 11 በመቶ ለተባለው ዓመታዊ ዕድገት ዋንኛ መሰረቱ የግብርና ምርት እድገት መሆኑን ሲገልጽ ቆይቷል። ይሁን እንጂ የውጪው እርዳታ እና ብድር ግብዓቶችም ሆኑ የውጪ ምንዛሬውም የሚኖራቸው ድርሻ ቀላል ኣለመሆኑን መገመት ይቻላል።
የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እድገት በሚመጣውም ዓመት በተመሳሳይ መልኩ ሊቀጥል እንደሚችል የገመተው ዓለም ዓቀፉ የገንዘብ ተቐም IMF ባለፈው ወር ይፋ ባደረገው ዓመታዊ ሪፖቱ ይህንኑ ጠቁሟል። መንግስታዊ ለሆኑ የልማት ተቐማት የሚደረገው የገንዘብ ድጋፍ ክፍተት ካሳየ እና የውጪ ምንዛሪ እጥረት ካጋጠመ ግን የተባለው እድገት ላይሳካ እንደሚችል IMF ኣልሸሸገም።
በቀጣዮቹ 12 ወራት የኣገሪቱ ኣጠቃላይ የኣገር ውስጥ ምርት በዓማካኝ የ 7 በመቶ እድገት ይኖረዋል የሚለው IMF ይህ ግን የፖሊሲ ማስተካከያ ካልታከለበት ኣንድ ቦታ ላይ መቆሙ ኣይቀሬ ነው ሲልም ያስጠነቅቃል።
መንግስት መር የኢኮኖሚ ልማት ፖሊሲን የሚከተለው የኢትዮጵያ መንግስት ይላል IMF እንደ ዓባይ ግድብ የመሳሰሉ ግዙፍ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶችን በራሱ ዓቅም ለማካሄድ ወስኖ ጀምሮታል። ይህ ፕሮጀክት የ 80 ቢሊዮን የኢትዮጵያ ብር ወጪ የሚጠይቅ ሲሆን በሪፖርቱ መሰረት 10 በመቶ የሚሆነውን የኣገሪቱን ዓመታዊ የኣገር ውስጥ ገቢ መጠን ይወስዳል ማለት ነው። እናም እድገቱ በዚህ ምክኒያት እንዳይሰናከል እና ቀጣይነት እንዲኖረው ለማድረግ ከተፈለገ መንግስት የግል ባለሀብቶች በላቀ ደረጃ በኢንቨስትመንቱ ውስጥ እንዲሳተፉ በር ሊከፍትላቸው ይገባል ሲል IMF ይመክራል።
የኣገር ውስጡ የልማት እንቅስቃሴ ከፍተኛ የኢንቨስትመንት ግብዓትን ይጠይቃል። የገንዘብ ኣቅርቦቱ ግን መሰናክል የሞላበት ነው ሲልም IMF ይወቅሳል። ለዓብነት ያህልም የግል ባንኮች እንቅስቃሴ ኣለመበረታታቱ እና የመnንግስት ባንኮችም ቢሆኑ ለግሉ ዘርፍ የሚሰጡት ብድር በቂ ኣለመሆኑን IMF ይጠቅሳል። ያለ ግል ባለ ሀብቶች ንቁ ተሳትፎ ግን የተጀመረው የኢኮኖሚ እድገት ቀጣይ ሊሆን እንደማይችል ሊሰመርበት ይገባል ሲል ሪፖርቱ ይቀጥላል።
የሆነ ሆኖ ይላል ዘገባው እ ኣ ዘ ኣ ከ 2001 እና 2002 ጀምሮ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በዓማካኝ በዓመት በ 7 በመቶ እድገት ኣሳይቷል። ይህም ይላል ዘገባው በዚያች ኣገር የድህነት እርከኑን በግማሽ ቀንሶታል። ይህ ማለት በሪፖርቱ መሰረት በ 2005 60,5 የነበረው የድህነት እርከን በ 2012 ወደ 30,7 ወርዷል። ይህም የበርካቶችን ኑሮ ኣሻሽሎታል የስራ ኣጥ ቁጥርንም በእጅጉ ቀንሶታል ያለው IMF በዚህ መካከል ግን የመንግስት በተለይም የገዢው ፓርቲ ኩባንያዎች በኣገር ውስጥ የገንዘብ ኣቅርቦት ተጠቃሚ ሲሆኑ የግል ተበሪዎች ግን ገለል መደረጋቸውን ሳይጠቅስ ኣላለፈም።
2012/13 7 በመቶ የተመዘገበው እድገት በዋናነት ከግብርና ከኮንስትራክሺን እና የኣገልግሎት ዘርፎች የተገኘ መሆኑን የጠቀሰው IMF ከዚሁ የተነሳ በ 2011 40 በመቶ ደርሶ የነበረው የዋጋ ግሽበትም በ 7 በመቶ መቀነሱን ጠቅሶ ነገር ግን በ 2012 2,8 ቢሊዮን የነበረው የበጀት እጥረት በ2013 ወደ 3 ቢሊዮን ከፍ ማለቱንም በሪፒርቱ ኣመልክቷል።

በኣፍሪካ ዋናዋ የቡና ኣምራች የሆነችው ኢትዮጵያ የብድር እና እዳ ይዞታዋን በሰከነ መልኩ ለማስኬድ ያስችላት ዘንድ IMF እንደሚለው የፋይናንስ ስርዓቷን ማሻሻል ይኖርባታል። በተለይ የግል ባንኮች በብድር ባሰራጩት ገንዘብ መጠን 27 በመቶ ያህል የመንግስት ሰነድ ሽያጭ እንዲገዙ የሚያስገድደውን ደንቃራ ደንብ ማስወገድ እንደሚኖርባት ኣመልክቷል።
ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ለዓመታት ያህል በስሌቱ ላይ ስምምነት ኣልነበረንም የሚሉት በአዲስ ኣበባ የIMF ተጠሪ ሚ/ር ጃን ሚኬልሰን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መንግስት መጠነኛ ማሻሻያ ማድረጉን ይናገራሉ።
የኢኮኖሚ ባለሙያው እና በኢትዮጵያ ፓርላማ ብቸኛው የተቃዋሚ ፓርቲ ተወካይ የሆኑት አቶ ግርማ ሰይፉ ግን የ IMF ዘገባ በመንግስት መረጃዎች ላይ የተመሰረተ በመሆኑ ችግር ያለበት ነው ይላሉ።
መረጃዎችን ከመንግስት እንደሚቀበሉ ያልሸሸጉት የ IMF ተወካይ ሚ/ር ጃን ሚኬልሰን ነገር ግን በራሳችን ስልት እንመዝናቿለን ይላሉ።
የኣንድነት ለዲሞክራሲ እና ለፍትህ ፓርቲ ም/ሊቀመንበሩ አቶ ግርማ ሰይፉ በበኩላቸው የIMF መመዘኛ በተዛቡ የመንግስት መረጃዎች ላይ እስከተመሰረተ ድረስ ትርጉም ኣይኖረውም ሲሉ በደርግ ጊዜ የታዘቡትን ተመሳሳይ የእድገት መለኪያ ያስታውሳሉ።ምንም እንኩዋን መንግስት በሚያስተዋውቀው ደረጃ ባይሆንም የተጠቀሰው እድገት ህብረተሰቡን በስፋት እየጠቀመ መሆኑን IMF ያምናል ይላሉ ሚ/ር ሚኬልሰን
አቶ ግርማ ሰይፉ ግን ይህንን ኣይቀበሉትም በኣጠቃላይ ግን የኢትዮጵያ መንግስት ኣንድ ነገር ካላደረገ በስተቀር የኣገሪቱ እድገት ኣሁን ኣንድ ሊያልፈው ከማይችል ፈታኝ ደረጃ ላይ ደርሷል ይላሉ በአዲስ ኣበባ የIMF ተጠሪ ሚ/ር ጃን ሚኬልሰን።
ጃፈር ዓሊ
አርያም ተክሌ
Source: www.dw.de
ሙሉውን አንብብ-Read More