
Dec 28, 2013
የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የደብር ሃላፊዎችና ሠራተኞች አዲሱን መዋቅር ተቃወሙ
Geez Bet | Saturday, December 28, 2013

“ዲግሪ ያላቸው በየአስተዳደሩ እንዲገቡ መደረጉ አግባብ
አይደለም” በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የአዲስ አበባ ሃገረ ስብከት፣ ካለፈው ህዳር ወር ጀምሮ
እያካሄደ ያለውን አዲስ
የመተዳደሪያ ደንብ የማፅደቅ ሂደት እና መዋቅራዊ ለውጥ አጥብቀው እንደሚቃወሙ የሃገረ
ስብከቱ የአድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎችና ሠራተኞች ለቅዱስ ፓትሪያርኩና ለጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት አስታወቁ፡፡
ቅሬታ አቅራቢዎቹ ለፅ/ቤቶቹ ባስገቡት ደብዳቤ፤ የሃገረ ስብከቱ አዲስ መተዳደሪያ ደንብ ሁሉም የቤተክርስቲያኒቱ
ሊቃውንት ሳይሳተፉበት በጥቂት አመራሮች...
Dec 28, 2013
ካልተሳፈርኩ” ብሎ የታክሲ ሹፌሩን በሽጉጥ ገደለ
Geez Bet | Saturday, December 28, 2013

መገናኛ አካባቢ ወደ ጉርድ ሾላ በሚወስደው መስመር፣ አንድ መንገደኛ ትናንት ከምሽቱ 12 ሰዓት ላይ ሚኒባስ ታክሲ
ውስጥ ካልተሳፈርኩ ብሎ ሾፌሩን ወንደሰን ደምሴን በሽጉጥ ገደለ፡፡ “ታክሲው
ውስጥ ካልተሳፈርኩ፣ አትሳፈርም” በሚል
በተነሳው ጭቅጭቅ፣ ሾፌሩን ገድሏል የተባለውን ደጀኔ ገመቹ በቁጥጥር ስር እንደዋለ የገለፀው ፖሊስ፤ የአይን
ምስክሮችን ቃል በመቀበል ምርመራ እያካሄደ ነው፡፡ ታክሲ እየጠበቁ የነበሩ የአይን ምስክሮች በወቅቱ አቶ ደጀኔ
እጁን በማወዛወዝ ሚኒባስ ታክሲውን እንዳስቆመ ተናግረው፣ ከሾፌሩ ጋር ጭቅጭቅ እንደተፈጠረ...
Dec 26, 2013
ኢትዮጵያ ከግብፅ ጋር የተስማማችባቸውና ያልተስማማችባቸው ነጥቦች ይፋ ተደረጉ
Geez Bet | Thursday, December 26, 2013

•ግብፅ የቅኝ ግዛት የውኃ ኮታዋ እንዲከበር አሁንም ጠይቃለች
•ለመስማማት የገባችውን ቃል አፍርሳለች
የውኃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር የህዳሴውን ግድብ
ግንባታ በተመለከተ ከግብፅና ከሱዳን መንግሥታት ጋር እያደረገ የሚገኘውን ድርድር ውጤት አስታወቀ፡፡ የግብፅ
መንግሥት ያቀረባቸው የግዴታ ሐሳቦች በኢትዮጵያ በኩል ተቀባይነት አላገኙም፡፡
የውኃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከግብፅና ከሱዳን አቻ
ሚኒስቴሮች ጋር በህዳሴው ግድብ ላይ እያደረጋቸው የሚገኙ ድርድሮችን ማክሰኞ ዕለት ለባለድርሻ አካላትና ለመገናኛ
ብዙኃን ሲያሳውቅ፣ ኢትዮጵያ ከግብፅ ጋር የተስማማችባቸውንና ያልተስማማችባቸውን ነጥቦች ይፋ አድርጓል፡፡
በሚኒስቴሩ የድንበር ተሻጋሪ ወንዞች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ፈቅ አህመድ ባቀረቡት ጽሑፍ፣ ሚኒስቴሩና
ብሔራዊ የባለሙያዎች...
Dec 25, 2013
አነጋጋሪው የማንዴላ ወታደራዊ ስልጠና
Geez Bet | Wednesday, December 25, 2013

ከ 4 ዓመት ገደማ በፊት፤ ወደ ኢትዮጵያ የተጓዙ አንድ የኔልሰን ማንዴላ ድርጅት ዋና ተመራማሪ፤ ማንዴላን
በማሠልጠን ያገዙ በሕይወት የሚገኙ ሰዎችን ሁሉ ጠይቀው ያሰባሰቡት መረጃ ፣ ማንዴላ ከእሥራኤላውያን ጋር ግንኑነት
እንደነበራቸው የሚያረጋግጥ አንዳችም እውነታ አልተገኘበትም።
ማንዴላን የጨበጣ ውጊያ ፣ የጦር መሣሪያ፣ አፈታትና አገጣጠም ፤ የቦንብ አጠቃቀምና የመሳሰለውን
ያሰለጠኗቸው ኢትዮጵያ ውስጥ የነበሩ የእሥራኤል የስለላ ድርጅት(ሞሳድ) ሠራተኞች ናቸው ሲል «ሐዓሬትዝ» የተሰኘ
በእስራኤል የሚታተም ጋዜጣ አስነብቧል። ይሁን እንጂ የኔልሰን ማንዴላ ድርጅት፤ በሰጠው መግለጫ፤ ከማንዴላ የግል
ማኅደርም ሆነ ከሌላ ይህን ዜና የሚያረጋጋጥ አንዳች ፍንጭ እንደሌለ...
Dec 24, 2013
ደቡብ ሱዳን፤ ከጦርነት ወደ ጦርነት
Geez Bet | Tuesday, December 24, 2013

ከፖለቲካ ዲፕሎማሲዉ ይልቅ፥ ጠመንጃ ጦርነትን ያደጉ የኖሩበት ሳልቫ ኪር የዲንካን፥ እንደ ፖለቲከኛ-ሻጥርን፥ እንደ
ዲፕሎማት ግድምድሞሽ ዘይቤን፥ እንደ ታጋይ የጫካ ዉጊያ አጣምረዉ የያዙት ዶክተር ሪክ ማቼር የኑዌር ጎሳን፥
ከየጎናቸዉ አሰልፈዉ ተፋጠዋል።
ዛሬ-ስምት ዓመት በዚሕ ወቅት ግድም የረጅም ጊዜዉ ጦርነት፥ የሚሊዮኖች እልቂት ፍጅት ስደት አበቃለት
ተባለ።የዛሬ-ሰወስት ዓመት በዚሕ ወቅት ግድም ሕዝቧ በነፃ ዉሳኔዉ ነፃነትዋን ማስፀደቁ ተነገረ። የዓለም
ፖለቲከኞች መሠከሩለትም።ደቡብ ሱዳን።ሐምሌ-ሁለት ሺሕ አስራ-አንድ (ዘመኑ በሙሉ እንደ ጎርጎሮሳዉያኑ አቆጣጠር
ነዉ) ነፃነቷ ታወጀ።ፌስታ።
ወዲያዉ ግን ግጭት። ደግሞ ጦርነት።ዛሬም ጦርነት ላይ ናት።አዲስ ሐገር፥ ግራ አጋቢ ምድር።እንዴት ለምን? ላፍታ አብረን እንጠይቅ።
አምና ነዉ።መስከረም።አዲሲቱን...
Dec 23, 2013
የ2013 የአፍሪቃ ዓበይት ክንውኖች
Geez Bet | Monday, December 23, 2013

ሊያበቃ ጥቂት ቀናት የቀረው 2013 ዓም በአፍሪቃ በፖለቲካው እና በማህበራዊው ዘርፎች ከታዩት ዓበይት ክንውኖች ጥቂቱ ባጭሩ ይቃኛል።
እአአ መጋቢት አምስት፣ 2013 ዓም ኬንያ ውስጥ የአጠቃላዩ ምርጫ ቀን
ነበር። ብዙ ሕዝብ ነበር ድምፁን ለመስጠት የወጣው። በተፎካካሪዎቹ ኡሁሩ ኬንያታ እና በቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር
ራይላ ኦዲንጋ ደጋፊዎቹ ጎራ ውስጥ ከፍተኛ ውጥረት ነበር የታየው። በምርጫው ኡሁሩ ኬንያታ አሸናፊ ቢሆኑም፣ ድላቸው
አካራካሪ ነበር፣ ምክንያቱም፣ ከአምስት ዓመት በፊት እኢአ በ2007 ዓም የተካሄደው ምርጫ ውጤት ይፋ ከሆነ በኋላ
በተከተሉት ወራት በሀገሪቱ የ 1,200 ሰዎች ሕይወት የጠፋበትን ግጭት ቀስቅሰዋል በሚል ብዙዎች የሚወቅሱዋቸው
ኬንያታ እና በምርጫው ዘመቻ ወቅት...
Dec 21, 2013
ዶክተር አምሳሉ አክሊሉ ዐረፉ
Geez Bet | Saturday, December 21, 2013
Dec 21, 2013
የደቡብ ሱዳን የሥልጣን ሽኩቻ መዘዝ፣
Geez Bet | Saturday, December 21, 2013

የሰሜን ሱዳን የፖለቲካ ተጽእኖና ፤ የዐረብ ባህል ጫና አንገሽግሾት 22 ዓመታት መሪር ትግል ያካሄደው የደቡብ
ሱዳን ህዝብ፤ ነጻነት ባወጀ በ 2 ዓመት ከመንፈቅ ገደማ ወደ አስከፊ የእርስ በርስ ውጊያ እንዳያመራ አሥግቷል።
ባለፈው እሁድ በመዲናይቱ
በጁባ ያገረሸው ውጊያ ፣ የ 500 ያህል ሰዎችን ሕይወት ቀጥፎ ፤ 34,000 ሰዎች፤ በተባበሩት
መንግሥታት ጣቢያዎች መጠለያ እንዲሻ አስገድዷል ። የሥልጣን መቀናቀን ነው የተባለለት ውዝግብ ፣ በጎሣ ልዩነት
ተካሮ ባፋጣኝ ወደሌሎች አካባቢዎች መዛመቱ የሚታወስ ነው። ጉዳዩ ያሳሰባቸው የምሥራቅ አፍሪቃ በይነ መንግሥታት
ሚንስትሮች ፤ የአፍሪቃ ኅብረትና የተባበሩት መንግሥታት ተወካዮች ጁባ ውስጥ ከሀገሪቱ ፕሬዚዳ...
Dec 20, 2013
ደቡብ ሱዳን ዉጊያና የሠላም ጥረት
Geez Bet | Friday, December 20, 2013

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እንደሚለዉ ፕሬዝዳት ኪየር የሚወለዱበት የዲንካ እና ማቼር የሚወለዱበት የኑዌር
ጎሳዎች መልክ እና ባሕሪ የያዘዉ ዉጊያ ፈጣን መፍትሔ ካላገኘ አደገኛ ነዉ።ደቡብ ሱዳን፥ ነፃነት ያወጀችበትን
ሁለተኛ ዓመት-ከመንፈቅ፥ ከረጅም ጦርነት የተላቀቀችበትን ሥምንተኛ ዓመት፥ እነሆ በጦርነት ልታከብር ዉጊያ
ጀምራለች።
የደቡብ ሱዳን መንግሥት ጦር እና በመንግሥት ላይ ያመፁት ሐይላት ወታደሮች ባለፈዉ ዕሁድ ርዕሠ-ከተማ ጁባ ዉስጥ
የጀመሩት ዉጊያ ወደ ሌሎች የሐገሪቱ አካባቢዎች እየተዛመተ ነዉ።የቀድሞዉ ምክትል ፕሬዝዳት የሪክ ማቼር ታማኞች
የተባሉት ሐይላት ዛሬ ቦር የተባለችዉን ከተማ ተቆጣጥረዋል።በሌሎች አካባቢዎችም ዉጊያዉ መቀስቀሱ ተዘግቧል።የዉጪ
መንግሥታት ዜጎቻቸዉን ከአዲሲቱ ሐገር እያሰወጡ ነዉ።ለግጭቱ ሠላማዊ መፍትሔ ለማፈላለግ ኢትዮጵያን ጨምሮ አራት...
Dec 19, 2013
ዓመታዊው የጋዜጠኞችን ፍዳ የዳሰሰው መግለጫ
Geez Bet | Thursday, December 19, 2013

በፓሪስና በኒው ዮርክ የሚገኙት ፣ ድንበር አያግዴው የጋዜጠኞች ድርጅት (RSF) እና ለጋዜጠኞች ህልውናና መብት
ተሟጋቹ ፤ (CPJ)፣ በዓለም ዙሪያ የጋዜጠኞችን ፍዳ የሚዘረዝረውን ዓመታዊ መግለጫቸውን ይፋ አደረጉ። ለመገባደድ 2
ሳምንት ገደማ በቀረው 2013 ጎርጎሪዮሳዊው ዓመት
ውስጥ 71 ጋዜጠኞች መገደላቸውናና 178 በእሥራት በመማቀቅ ላይ እንደሚገኙ የወጣው ዘገባ ያስረዳል።
ጋዜጠኞችን አሥሮ በማሠቃየት ከተወቁት 10 ሃገራት መካከል፤ ኤርትራ ፣ ኢትዮጵያ፤ግብፅ ፣ ቪየትናም፤ ሶሪያ ፤
አዘርባጃንና ዑዝቤኪስታን ይገኙበታል። በአፍሪቃው ቀንድ የጋዜጠኞችን ይዞታ የሚከታተሉትን ፤ በምሥራቅ አፍሪቃ የ
CPJ ን ተጠሪ በማነጋገር ፤ ተከታዩን ዘገባ አቅርበናል።
በሥራ ላይ እንዳሉ ጋዜጠኞች ሕይወታቸውን ያጡባቸው አካባቢዎች ፤ እስያ፤ (24 ናቸው
የተገደሉት፤)መካከለኛው...
Dec 19, 2013
ደቡብ ሱዳንና የተሰናከለው የዴሞክራሲ ተስፋ
Geez Bet | Thursday, December 19, 2013

የሱዳን ዋና ከተማ ጁባ ከእሁዱ መፈንቅለ መንግሥት ሙከራ በኋላ ዛሬ መረጋጋትዋ ተዘግቧል ። ነዋሪዎች ዛሬ ከቤታቸው
መውጣት ጀምረዋል ። አልፎ አልፎ ተኩስ መሰማቱ ግን አልቆመም ። መንግሥት እንዳስታወቀው ከመፈንቅለ መንግሥት
ሙከራው ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩ 10 ሰዎችን አስሯል ።
ተዘግቶ
የቆየው የጁባ አውሮፕላን ማረፊያ እንዲከፈት መንግሥት ትዕዛዝ ቢያስተላልፍም አንዳንድ አየር መንገዶች ወደ ጁባ
ከመብረራቸው በፊት የፀጥታ ዋስትና ጠይቀዋል ። ዩናይትድ ስቴትስ ዜጎቿን ማስወጣት እንደምትጀምር አስታውቃለች ።
በደቡብ ሱዳን የኃይል እርምጃ ማገርሸቱ የሃገሪቱን የዴሞክራሲ ተስፋ እንዳያሰናክል አስግቷል ። በጎሳ
የተከፋፈሉ የደቡብ በሱዳን ጦር ሠራዊት አባላት ባለፈው እሁድ ለሊት ጁባ አቅራቢያ ከተታኮሱ በኋላ የተፈጠረውን
መንግሥት የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ብሎታል...
Dec 17, 2013
እልፍ አንድ ሺህ ወይስ ዐሥር ሺህ?
Geez Bet | Tuesday, December 17, 2013

By Kassahun Alemu:
፩. ምክንያተ ጽሕፈት
ይስማዕከ ወርቁ በቅርብ ጊዜ ባሳተመው ‹ተከርቸም› በሚለው 6ኛ መጽሐፉ ‹እልፍ(፼) ዐሥር ሺህን ሳይኾን አንድ
ሺህን ይወክላል› የሚል መከራከሪያ አቅርቧል፡፡ እኔም በመጽሐፉ ያቀረበውን የእልፍ(፼) ቁጥር አስተያየት
ከተመለከትኩ በኋላ መስተካከል ያለበት ጉዳይ መስሎ ስለተሰማኝ ይህንን ጽሑፍ በተወሰነ ደረጃ ሞነጫጭሬ አስቀምጨው
ነበር፤ በዕንቁ መጽሔት ተጠይቆ የሰጠውን መልስ ከተመለከትኩ በኋላ ግን መከራከሪያ ነጥቦችን ማቅረብ አስፈላጊ መስሎ
ታየኝ፡፡
ምክንያቱም በእኔ ዕይታ የይሰማዕከ የ‹እልፍ አንድ ሺህ ነው› ውሳኔያዊ መጣጥፍና አጠቃቀም ሁለት አንድምታዎች
አሰምቶኛል፡፡ አንድኛ ከዚህ በፊት የታተሙት የሊቃውንት መጻሕፍት የግዕዝ ቁጥር አጠቃቀም ስህተት መኾን ይጠቁማል፡፡
ይህ አንድምታም ‹የሀገራችን ሊቃውንት...
Dec 17, 2013
የማንዴላ አሰተምሕሮ እና ድሕረ-ማንዴላ
Geez Bet | Tuesday, December 17, 2013

ፍልስጤም-እስራኤሎች፥ ዋሽንግተን፥ ሞስኮዎች፥ ዋሽንግተን፥ ቤጂንግ፥ ዋሽንግተን ቴሕራኖች፥ ዋሽንግተን ሐቫናዎች፥
አስመራ-አዲስ አበቦች፥ ኢሕአዲግ ተቃዋሚዎች፥ ሶማሌዎች፥ ሶሪያዎች፥ ብዙ ናቸዉ። ቁጥራቸዉን መዘርዘሩ ያታክታልም።
ከማንዴላ ምግባር ጥቁቱን፥ ከዴክላክ ድፍረት ትንሹን እንኳን ገቢር አለማድረጋቸዉ በርግጥ ያጠያይቃል
ማንዴላ ተቀበሩ። ታላቁ የነፃነት፣ የእኩልነት አርበኛ ከሞቱበት እስከ ተቀበሩበት ድፍን ዓለም አዘነ፥ ወይም
ማዘኑን ገለፀ። ከቄሱ እስከ ሼኩ፥ ከዘማሪዉ እስከ ዘፋኙ፥ ከተዋኙ እስከ ስፖርተኛዉ ለዚያ ታላቅ-ክቡር ሠዉ ታላቅ
አድናቆት፥ አክብሮቱን ሲያንቆረቁር ሰነበተ። ከፕሬዝዳት ዙማ-እስከ ፕሬዝደንት ኦቦባ፥ ከጠቅላይ ሚንስትር ኃይለ
ማርያም እስከ ጠቅላይ ሚንስትር ካሜሩን የትንሽ ትልቁ ሀገር መሪ የማንዴላን አብነት ለመከተል፥ ዓላማ፥ ራዕይ...
Dec 17, 2013
የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ በደቡብ ሱዳን
Geez Bet | Tuesday, December 17, 2013

በደቡብ ሱዳን ትላንት የተሞከረው የመንግስት ግልበጣ መክሸፉን የኣገርቱ መንግስት ኣስታወቀ።
በቀድሞው ም/ፕሬዝደንት ማቻር የተመራው የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ የከሸፈው ለፕሬዝደንት ሳልቫኪር ታማኝ የሆኑ ወታደሮች የበላይነትን በማግኘታቸው ነው ተብሏል።
የቀድሞው የኣገሪቱ ም/ፕሬዝደንት ከስልጣን የተባረሩት ባለፈው ሀምሌ ወር ሲሆን ቅርበት ያላቸው ምንጮች እንደሚሉት ከዚያ ወዲህ በመንግስትም ሆነ በገዚው የSPLM ግንባር መካከል ክፍፍል ተፈጥሯል።
ከእሁድ ቀትር በኃላ ጀምሮ እስከ ዛሬ ማለዳ የዘለቀው የተኩስ ልውውጥ ኣሁን መቆሙን እና በከተማይቱ ጁባ ኣንጻራዊ መረጋጋት መስፈኑን የኣይን እማኞች ይናገራሉ።
በቀድሞው ም/ፕሬዝደንት የሚመሩ ያኮረፉ ወታደሮች እና ፖለቲከኞች በመንግስት ኃይሎች በተለይም በቤተመንግስት የጸጥታ
ኃይሎች ላይ የከፈሩት ድንገተኛ ተኩስ ከየኣቅጣጫው...
Dec 16, 2013
እምዬ ምኒልክ! (ተመስገን ደሳለኝ)
Geez Bet | Monday, December 16, 2013

ይህንን አጀንዳ ለማቅረብ ያሰብኩት ባለፈው ሳምንት ነበር፤ ይሁንና ‹‹የምስራቅ ኢትዮጵያ ፖለቲካ 2›› የሚለው ፅሁፌ አንድም ወቅቱ ‹‹የብሔር ብሔረሰቦች ቀን›› ዋዜማ በመሆኑ፣ ሁለትም በይደር የተላለፈው የዚሁ ተከታይ ፅሁፍ መቋጨት ግድ በማለቱ ነበር፡፡ እናም ‹ቦ ጊዜ ለኩሉ› እንዲል ጠቢቡ፣ የዘገየው አጀንዳችን የዕውቁ ደቡብ አፍሪካዊው የፀረ አፓርታይድ ትግል መሪ ኒልሰን ማንዴላን ህልፈት ተከትሎ ዓለም ‹በተሳሳተ የታሪክ ወንዝ› ከመፍሰሱ ጋር ተነፃፅሮ ይቀርብ ዘንድ ገፊ ምክንያት ሆኗል፡፡ በርግጥ የአጀንዳው ተጠየቅ ማንዴላን አኮስሶ፣ ዳግማዊ አፄ ምኒልክን ማወደስ አይደለም፤ ንጉሡን ያገለለውን ጨካኝ የታሪክ ፍርድ መሞገት እንጂ፤ በአናቱም ከውስጥ ጉዳይ ጋር ተያይዞ ዘመን የተሻገረ ቂም የሀገር ባለውለታን ታሪክ ማደብዘዙን መተቸት ነው፡፡
‹ምኒሊክ ተወልዶ...
Dec 16, 2013
የማንዴላ የቀብር ስነ ስርዓት ተፈፀመ
Geez Bet | Monday, December 16, 2013

የነፃነት እና የፀረ-ዘረኝነት ታጋዩ ኔልሰን ማንዴላ ስርዓተ ቀብር እሁድ ታኅሣሥ 6 ቀን 2006 ዓም ደቡብ አፍሪቃ
ኩኑ በተባለችው የትውልድ መንደራቸው ተካሄደ። ለማንዴላ ክብር በቀብር ስርዓቱ 21 ጊዜ መድፍ የተተኮሰ ሲሆን፤
የጦር ጀቶች ከዕድምተኛው በላይ ሲያንዣብቡም ታይተዋል።
ከእንስሳት ቆዳ የተሰፉ ባሕላዊ ልብሶችን የለበሱ ሀዘንተኞች ለማንዴላ ውዳሴ አሰምተዋል። የደቡብ አፍሪቃ አፓርታይድ
ስርዓት ከተገረሰሰ በኋላ የሀገሪቱ የመጀመሪያው በዲሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጡት ኔልሰን ማንዴላ ግብዓተ መሬት
የተፈፀመው በምሥራቃዊ ደቡብ አፍሪቃ በምትገኘው ኩኑ በተሰኘችው ገጠራማ መንደር ውስጥ ነው። በቀብር ስርኦቱ ላይ
በበርካታ መቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እንደተገኙ የፈረንሣይ ዜና አገልግሎት አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል። ቀደም ብሎም
በሺዎች የሚቆጠሩ ታዳሚዎች በማንዴላ...
Dec 16, 2013
በሳይንስ የኖቤል ተሸላሚዎችና ምርምራቸው
Geez Bet | Monday, December 16, 2013

ትናንት ፤ በእስቶክሆልም ፤ ስዊድን ፣ በኔልሰን ማንዴላ የመጨረሻ የስንብት ሥነ ሥርዓት ሳቢያ ታላላቅ ዓለም አቀፍ
እንግዶች ተመናምነው ፣ ሆኖም ከ 1,300 በላይ ታዳሚዎች በተገኙበት ስብሰባ ፣ በ3 ቱም የተፈጥሮ ሳይንስ
ዘርፎች ውድድር ፣ የዘንድሮዎቹ አሸናፊዎች ሽልማታቸውን ተቀብለዋል።
ለጀርመን ዓመታዊ የምርምር ከፍተኛ ሽልማት ለፍጻሜ የደረሱ 3 እጩ ተሸላሚዎች ፕሮጀክቶች ፤ ከብርሃን ጋር ግንኙነኅት ያላቸው ሲሆን፤ በተለይ ከየናው ፣ የፍሪድሪኽ ሺለር ዩንቨርስቲ ፣ ከ ቦሽና በ ሽራምበርግ ከተማ ከሚገኘው በ LASER(Light Amplification by Stimulated Emission of Radiation) ምርምር
ላይ ካተኮረው ተቋም ጋር ተባብረው ለኢንዱስትሪ የሚበጅ...
Dec 14, 2013
በእሥራኤል ደም ልገሳ ያስከተለዉ ዉዝግብ
Geez Bet | Saturday, December 14, 2013

በኢትዮጵያ ተወልደው፣ በ 3 ዓመታቸው እሥራኤል በመግባት ፤ በዚያ ያደጉ የተማሩና የፓርላማ (ክኔሰት) አባል
የሆኑት ፔኒና ታማኖ-ሻታ የተባሉት የ 32 ዓመት ወ/ሮ ፣ ከትናንት በስቲያ ደም ለመለገሥ ተዘጋጅተው ፤ በጤና
ጥበቃ ሚንስቴር መመሪያ
ደንብ መሠረት እንደማይፈቀድላቸው ከአምቡላንስ አገልግሎት እንደተነገራቸው ፣ ድርጊቱ ፣ አስቆጥቶ፣ እ ጎ
አ በ 1996 ዓ ም ተከሥቶ የነበረውን ፣ ቤተ እሥራኤላውያን ለደም ባንክ የለገሡት ደም እንዲደፋ የተደረገበትንና
ብርቱ የተቃውሞ ሰልፍ ያስከተለበትን የቁርሾ ስሜትም ቀስቅሶ በእሥራኤል ሕብረተሰብ እንደገና ዐቢይ የመነጋገሪያ
አጀንዳ ሆኖ ሰንብቷል።
የፓርላማ አባል ፤ ወ/ሮ ታማኑ ሺታ ፤ መምህርት፤ ጠበቃና የመገናኛ ብዙኀን ባለሙያ ሲሆን፤ በቅርቡ
በኔልሰን ማንዴላ የመጨረሻ የስንብት ሥነ ሥርዓት ፤ በምክትል የፓርላማ...
Dec 14, 2013
ማንዴላና የስፖርት ውርሳቸው
Geez Bet | Saturday, December 14, 2013

የስፖርት አዋቂዎች እንደሚሉት ማንዴላ ከዓለማችን ፖለቲከኞችና የመብት ተሟጋቾች በተለየ ስፖርትን በሰላም መሣሪያነት
ተጠቅመዋል ። ለስፖርት ትልቅ ቦታ ይሰጡ የነበሩት ማንዴላ በተለያዩ ዓለም ዓቀፍ የስፖርት ተቋማትና በስፖርት
ዓዋቂዎች ዘንድ ትልቅ ከበሬታ አላቸው ።
የዛሬ ሳምንት ሐሙስ በ95 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት የደቡብ አፍሪቃ ፕሬዝዳንት ኔልሰን
ማንዴላ የነፃነት ታጋይ ብቻ ሳይሆኑ ስፖርት ዓለምን የመለወጥ ኃይል እንዳለው የሚያምኑ መሪ እንደነበሩም ታዋቂ
የስፖርት ሰዎች ምስክርነታቸን እየሰጡ ነው ። የስፖርት አዋቂዎች እንደሚሉት ማንዴላ ከዓለማችን ፖለቲከኞችና የመብት
ተሟጋ...
Dec 13, 2013
‹‹የወደፊቷ ደቡብ አፍሪካ ከማንዴላ ጋር መያያዟን እጠራጠራለሁ›› ሌተና ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለ ማርያም
Geez Bet | Friday, December 13, 2013

በዚምባቡዌ የስደት ሕይወት የሚመሩት የቀድሞው ፕሬዚዳንት ሌተና ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለ ማርያም፣ ...
የኔልሰን ማንዴላን ሕልፈት በማስመልከት አውስትራሊያ
ከሚገኘው ኤቢኤስ ሬዲዮ የአማርኛ አገልግሎት ጋር ቃለ ምልልስ አድርገዋል፡፡ መንግሥቱ ለሬዲዮው በሰጡት ቃለ ምልልስ
እንደገለጹት፣ በእሳቸው በትረ ሥልጣን ወቅት ማንዴላ የአገሪቱን ከፍተኛ የክብር ሽልማት ከመጎናፀፈቸውም ባሻገር፣
የአንድ መቶ ሺሕ ዶላር ገንዘብ ተበርክቶለቸዋል፡፡ ይህና ቀሪው ንግግራቸው እንዲህ ቀርቧል፡፡
‹‹ማንዴላና የተወሰኑ ተከታዮቻቸው ወደ ኢትዮጵያ በስውር መጥተው፣ ወታደራዊ ሥልጠና አግኝተውና እግረ መንገዳቸውን ሞሮኮን ጐብኝተው ወደ ደቡብ አፍሪካ ማምራታቸውን ተገንዝቤያለሁ፡፡
‹‹በዚያን ጊዜ አሜሪካኖች በአማካሪነት ኢትዮጵያ ውስጥ ነበሩ፡፡...
Dec 12, 2013
የቤተእስራኤላውያን እሮሮ በእስራኤል
Geez Bet | Thursday, December 12, 2013

በእስራኤል ኣገር የሚገኙ ኢትዮጵያዊ ቤተእስራኤላውያን የኑሮ ውድነትን በመቃወም ኣደባባይ እየወጡ ነው።
ከመንግስት የሚደረገው ድጎማ ከኑሮ ውድነቱ ጋር ሊጣጣም ባለመቻሉ በተለይም ቤት መግዛት እንዳልቻሉም ይናገራሉ።
በዚያች ኣገር የሚኖሩ የኣፍሪካ ስደተኞችም የእስራኤል መንግስት የውጪ ስደተኞችን ከኣገሩ
ለማስወጣት የያዘውን እቅድ በመቃወም ባለፈው ሳምንት ኣደባባይ ወተው ነበር።
በኣፍሪካ ስደተኞች የልማት ማዕከል መረጃዎች መሰረት በኣሁኑ ጊዜ በእስራኤል ኣገር 60 ሺህ ያህል የውጪ ስደተኞች ይገኛሉ።
ባለፈው ሐሙስ በእየሩሳሌም እና በናታኒያ ከተሞች አደባባይ የወጡት...
Dec 12, 2013
ባራክ ሁሴይን ኦባማ: ስለ ማንዴላ
Geez Bet | Thursday, December 12, 2013

«የማንዴላን አብነታዊነት ማሟላቱ ቢያቅተኝም፥ ምሳሌያዊ ምግባራቸዉ የተሻለ ሰዉ ለመሆን እንድጥር ያበረታታኛል።» ባራክ ሁሴይን ኦባማ፥ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት። ታሕሳስ 1/ 2006
ቀኑ ዝናባማ ቢሆንም ከ80 000 በላይ ህዝብ በሲዮቶው የዓለም ዋንጫ ስታዲየም በተካሄደው ስነስርዓት ላይ መገኘቱ ታውቐል።
የማንዴላ የቀብር ስንስርዓት የፊታችን እሁድ የትውልድ መንደራቸው በሆነችው የኩኑ ቀበሌ ይፈጸማል ተብሎ ይጠበቃል።
የኔልሰን ማንዴላ የኣሸኛኘት ስነስርዓት የተካሄደው በጆሃንስበርግ ከተማ ስዌቶ በሚገኘው የዓለም ዋንጫ ስታዲየም
ነበር። ዕለቱ ከማለዳው ጀምሮ ዝናባማ ቢሆንም ከጆሃንስበርግ ከተማ እና ከተለያዩ የኣገሪቱ ከተሞች የመጡ ታዳሚዎች
ከረፋዱ ጀምሮ ነበር በስታዲየሙ ዙሪያ የተሰባሰቡት። ቀትር...
Dec 11, 2013
የምስራቅ ኢትዮጵያ ፖለቲካ ፪
Geez Bet | Wednesday, December 11, 2013

(ተመስገን ደሳለኝ):
ባለፈው ሳምንት የምስራቅ ኢትዮጵያ ፖለቲካን ተጨባጭ እውነታዎችን ቃኝቼ ተከታዩን ክፍል በይደር አቆይቼው እንደነበረ ይታወሳል፤ እነሆም ዛሬ እንዲህ እቀጥላለሁ፡-ሐረር እንደ ማሳያ
(መቼም ኢህአዴግ በብቸኝነት የሚኩራራበት የፖለቲካ ‹ስኬት›፣ ለዘመናት አንድ ሆኖ የኖረ ሕዝብን ‹ብሔር ብሔረሰቦች› በሚል ከፋፋይ የ‹ክርስትና ስም› እጥምቆ በአደባባይ ማስጨፈር ከሆነ ሰነባብቷል፡፡ ርግጥ ነው በአንድ ወቅት በፍትህ ጋዜጣ ላይ ‹‹የብሔር ብሔረሰቦች መብት እስከ መጨፈር›› በሚል ርዕስ የታተመ መጣጥፍን ተከትሎ ‹ፀረ-ብሔር ብሔረሰቦች› ተደርጌ በተመሰረተብኝ ክስ ፍርድ ቤት መመላለሴ ዛሬም ድረስ መቋጫ አላገኘም፤ ርግጥ ነው ኢትዮጵያውያን ወንድም እህቶቼ በስታዲዮሞች እየተሰባሰቡ የራስ ፀጉራቸው ላይ ላባ ሰክተው፣ ቆዳ አገልድመው እየዘለሉ ትርኢት ከማሳየት...
Dec 9, 2013
በመዲናዋ ምስጢራዊ የወሲብ ገበያ ደርቷል
Geez Bet | Monday, December 09, 2013

የትላልቅ ድርጅቶች ፀሃፊዎች፣ ሞዴሎችና ተዋናዮች አሉበት
ድንግልናን በ10ሺ ብር የሚያሻሽጡ ደላሎች ሞልተዋል
የከተማዋ ቱባ ባለሃብቶች “የአገልግሎቱ” ተጠቃሚዎች ናቸው
ሲኤምሲ
ሣሚት ማዞሪያ አካባቢ ካሉት ዘመናዊ ቪላ ቤቶች በአንደኛው 12ሺ ብር ወርሃዊ ኪራይ እየከፈለች ትኖራለች፡፡
የምታሽከረክረው ኤክስኪዩቲቭ ቶዮታ፣ በየዕለቱ የምትቀያይራቸው እጅግ ውድ ዋጋ ያላቸው አልባሳቶቿና በየመዝናኛ
ሥፍራው የምትመዘው ረብጣ ብር የተንደላቀቀ ኑሮ እንደምትመራ ይመሰክራሉ፡፡ በሳምንቱ መጨረሻ ቀናትና መዲናችን
አለማቀፋዊ ስብሰባዎችን በምናስተናግድበት ጊዜያት እሷን ፈልጐ ማግኘት የማይታሰብ ነው፡፡
ቦሌ ፍሬንድሽፕ
ሕንፃ ላይ በከፈተችው ቡቲክ የምታገኘው ገቢ ይሄን ያህል ሊያዝናናት እንደማይችል የታወቀ ነው፡፡ ገቢ ወጪዋን
አጥብቃ የማትቆጣጠርበትን...
Dec 9, 2013
ከሳውዲ ተመላሽ ዜጎች ንብረታቸው በጉምሩክ እንደተወሰደባቸው ተናገሩ
Geez Bet | Monday, December 09, 2013

ህገወጥ
ናችሁ ተብለው ከሳውዲ አረቢያ ወደ አገራቸው የተመለሱ ኢትዮጵያዊያን፤ ለበርካታ አመታት ለፍተን ያፈራነውን ንብረት
ይዛችሁ መግባት አትችሉም ተብሎ ተነጥቀናል፡፡ የፍተሻ ሰራተኞች ሻንጣዎቻቸውን በመፈተሽ፣ ሞባይል ከአንድ በላይ
ከያዙ ትርፉን በማስቀረት፣ አዳዲስ አልባሳት እና ኤሌክትሮኒክስ ቁሰቁሶች የተወሰኑትን ብቻ በመፍቀድ እና ያመጡትን
ወርቆች ግራም በመቀነስ ንብረታቸውን እየወሰዱባቸው እንደሆነ ተመላሾቹ ገልፀዋል፡፡
መሃመድ አባመጫ የተባለ የሳኡዲ
ተመላሽ፤ ከሳውዲ ስድስት ሻንጣ ይዞ መምጣቱን ገልፆ፤ ቦሌ አውሮፕላን ማረፍያ ሲደርስ ግን ከሁለት ሻንጣ በላይ ይዞ
መግባት እንደማይችል፣ ከአምስት ሞባይሎችም ሁለቱ ብቻ እነደተፈቀደለት ለአዲስ አድማስ ተናግሯል፡፡ የሳውዲ
መንግስት ከአንድ ኪሎ በላይ ወርቅ ይዛችሁ መውጣት አትችሉም የሚል መመሪያ ማሳለፉን የጠቆመው...
Dec 9, 2013
በማንዴላ ሞት የአፍሪቃውያን መሪዎች አስተያየት
Geez Bet | Monday, December 09, 2013

የተከበሩት ተወዳጁ የደቡብ አፍሪቃ ፀረ አፓርታይድ ታጋይ እና ትልቅ አመለካከት ያተረፉት አንዱ የ 20ኛው ምዕተ
ዓመት ዕውቅ ፖለቲከኛ ኔልሰን ማንዴላ ሐሙስ፣ ኅዳር 26 ቀን፥ 2006 ዓም በ95 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት
የተለዩበት ዜና በደቡብ አፍሪቃ፣ በመላ አፍሪቃ እና በዓለም ትልቅ ሀዘን አስከትሎዋል።
ከ 27 ዓመታት እስራት በኋላ በደቡብ አፍሪቃ የመጀመሪያው ጥቁር ፕሬዚደንት ሆነው እአአ በ1994 ዓም የተመረጡት
እና ሀገሪቱን እስከ 1999 ዓም የመሩት ኔልሰን ማንዴላ ለረጅም ጊዜ ለሳምባ ሕመም በሀኪም ቤት እና ካለፈው
መሰከረም ወርም በኋላ ጆሀንስበርግ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ህክምና ሲደረግላቸው ከቆዩ በኋላ ነው ያረፉት።
የደቡብ አፍሪቃው ፕሬዚደንት ጄኮብ ዙማ ተወዳጁ መሪ እና የዴሞክራሲያዊቷ ሀገር መሥራች አባት
የሆኑትን...
Dec 9, 2013
የአፄ ምኒልክ 100 ኛ ሙት-ዓመትና ክንዋኔዎቻቸው
Geez Bet | Monday, December 09, 2013

አውሮፓውያን ከዚያ በፊት ያልታዬ ከእርስ -በርስ አስከፊ ፍጅት የደረሱበት የአንደኛው የዓለም ጦርነት ሊፈነዳ 7
ወራት ገደማ ሲቀሩት ነበረ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ዳግማዊ አፄ ምኒልክ ታኅሳስ 3 ቀን 1906 ዓ ም ያረፉት።
በዘመኑ ብቸኛይቱን አፍሪቃዊት ነጻ ሀገር ይመሩ የነበሩት አፄ ምኒልክ
ህዝባቸውና የጦር አለቆቻቸውን አስተባብረው ፣ መላ ኢትዮጵያን በቅኝ ግዛት ሥር ለማድረግ የዘመተውን የኢጣልያ ጦር
ኃይል አድዋ ላይ ድል በመምታት ፣ በዘመኑም የዘመናዊ ሥልጣኔ መገለጫዎች የነበሩ ስልክና ባቡር ሐዲድ በማስገባት ፣
ት/ቤትና ባንክ የመሳሰሉትን ተቋማት በመክፈት ይታወቃሉ። በውጭው ዓለም የተፈሩ ፣ የተከበሩ ፣ በቅኝ ግዛት ሥር
ለነበሩ አፍሪቃውያንና ከባህር ማዶ...
Dec 7, 2013
የማንዴላ ሞትና የዓለም አስተያየት
Geez Bet | Saturday, December 07, 2013

ዓለም፥ ድፍን ዓለም የሩሲያዉ ፕሬዝዳት ቭላድሚር እንዳሉት «የዘመኑን ታላቅ ፖለቲከኛ» በማጣቱ ተከዘ።አብዛኛዉ
ዓለም አዘነ።ደቡብ አፍሪቃዎች ደግሞ በሐገሪቱ ፕሬዝዳት በጄኮብ ዙማ አገላለፅ «መሆን የሚፈልጉትን እንዲሆኑ
ባደረጓቸዉ» ታላቅ ሰዉ ሞት አረገዱ።
ማንዴላና ደቡብ አፍሪቃ
ማንዴላ።ከእንግዲሕ እኛ የደቡብ አፍሪቃ ታላቅ ልጅ፥ እኛ የዴሞክራቲክ ሥርዓቷ ቀንዲል፥ እኛ
የደቡብ አፍሪቃዉያን ልዩ አባት ታላቅ ምግባራቸዉ ነዉ-ቀሪ፥ መዘከሪያቸዉ።እንደገና ሒሩት መለሰ ያጠናቀረችዉን
ተክሌ የኋላ ያሰማና...
Dec 7, 2013
ማዲባ የድቡብ አፍሪቃውያን አባት
Geez Bet | Saturday, December 07, 2013

እንደ ወጣት በእልሕ፥ እንደ ወታደር በነፍጥ፥ እንደ ሕግ አዋቂ በፍርድ ቤት ታገሉ።እንደ ወንጀለኛ ታሠሩ።እንደ
ዲፕሎማት ተደራደሩ፥ እንደ ፖለቲከኛ የሕዝብ እኩልንነትን አስርፀዉ ሐገር መሩ።እና እንደ ሰዉ የምድር ሩጫቸዉን
ትናንት ጨረሹ።ዘጠና አምስት አመታቸዉ ነበር።
የሕዝብ ነፃነት፥ ፍትሕ፥ እኩልነትን ሚሊዮነ-ሚሊዮናት ይፈልጉ-ይመኙታል ። መቶ ሺሕ ዎች ይታገሉ ወይም
ለመታገል ይሞክሩታል።ሺዎች ትግሉን ያጋምሱ ወይም ይሰዉለታል።ዓላማ ትግሉን ከግብ የሚያደርሱት ግን፥- እኒያ ጥቂት
በጣም ጥቂት ቆራጦች፥ ብልሆች፥ ታጋሾች፥ ስልት አዋቂዎች፥ እና...
Dec 4, 2013
የዓለማቀፉ የሙስና ጥናት ተቋም መግለጫ
Geez Bet | Wednesday, December 04, 2013

የመካከለኛው ምስራቅሀገሮች ከጊዜ ወደ ጊዜ በሙስና እየተዘፈቁ መምጣታቸውን ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሺናል የተባለ
ኣንድ የጥናት ተቐም ኣስታወቀ። መቀመጫውን በጀርመን ሀገር ያደረገው ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሺናል ዛሬ ባወጣው
ዓመታዊ ሪፖርቱ በተለይ
በቀጠናው ከተቀጣጠለው የዓረብ ዓብዮት ወዲህ ደግሞ በመከከለኛው ምስራቅ ሀገሮች የሚታየው የሙስና ይዞታ እጅግ
ተባብሷል። በኣጠቃላይ የመካከለኛው ምስራቅ ኣገሮች ሁሉም ማለት ይቻላል ያላቸው ነጥብ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ
ከተቀመጠው ኣማካኝ የሙስና የጥብ በታች ሲሆን በትራንስፓረንሲ ኢኒተርናሺናል መመዘኛ መሰረት በዓለም ዓቀፍ ደረጃ
የተቀመጠው ኣማካኝ የሙስና ነጥብም 43 ነው
ዓለም ዓቀፉ የሙስና ጥናት ተቐም ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሺናል ዛሬ ባወጣው ዓመታዊ ዘገባ በመካከለኛው...
Dec 3, 2013
የዓርብ ግዞተኞች ፪
Geez Bet | Tuesday, December 03, 2013

(አስራት አብርሃም) ባለፈው ሳምንት በዚህ ርዕስ ልፅፈው የፈለኩትን አልጨረስኩም ነበርና እነሆ ዛሬ የመጨረሻውን ክፍል ይዤ ቀርቤያለሁ። አብዛኛውን በሰላማዊ ሰልፉ ላይ ተገኝቶ የተያዘ (ከመንገድ የተያዙም ነበሩበት) እስረኛ ቪድዮ ቀርፀው፤ ስሙንም መዝግበው ወደ አስር ሰዓት አከባቢ አስናበቱት። እኛ አስራ አምስት የምንሆን ግን ለይተው እንድንቆይ አደረጉን። ማደራችን እንደሆነ አስብኩ፤ በንጋታው ቅዳሜ በመሆኑ ከፈለጉም እስከሰኞ ሊያቆዩን እንደሚችሉም አስብኩ። ለሁሌስ ቢሆን ሊያስሩን ከፈለጉ ማን ይከለክላቸዋል፤ ወደ ቃሊቲም ሊልኩን ይችላሉ።
ብዙዎቹ ግን ምንም ጥፋት እንደሌለን እና በአጭር ጊዜ ውስጥም ልንፈታ እንደምንችል እየተናገሩ ራሳችውን አበርትተው እኛንም ያበረታቱን ነበር። ለነገሩ እዚያ በእንዲህ ባለ ሁኔታ እንድንታሰር የሆነው እኮ ወንጀል ስርተን አልነበረም። እነርሱ ሊያስሩን...
Dec 3, 2013
የምስራቅ ኢትዮጵያ ፖለቲካ
Geez Bet | Tuesday, December 03, 2013

(ተመስገን ደሳለኝ)…አውሮፕላኑ ቅዳሜ ጠዋት ሶስት ሰዓት ላይ ድሬዳዋ አየር ማረፊያ ደርሶ ከተርሚናሉ ስወጣ፣ ተጠራጥሬ ሰዓቴን ተመለከትኩ፤ የድሬ የጠዋት ፀሐይ ከተለመደው ንዳዷ ጋር የአዲስ አበባን የቀትር መራራ ፀሀይን ታስከነዳለች፤ እናም አጥበርባሪ ጨረሯን ያለምህረት ስትለቅብኝ፣ ጓደኛዬ መኪና ይዞ እቦታው እስኪደርስ መጠበቁ በገዛ ፍቃድ መለብለብ ስለመሰለኝ፣ በቀጥታ ከተደረደሩት ታክሲዎች አንዱን ይዤ ወደ ከዚራ አመራሁ፤ ድሬ የሄድኩት በዋናነት ከማህበራዊ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ምክንያት በመሆኑ ሊቀበለኝ የተዘጋጀውን ጓደኛዬን ደውዬ ከማውቃቸው የአንዱን ሆቴል ስም ጠቅሼ እዚያ እንድንገናኝ ነገርኩት፡፡
የሆቴሉ ፍተሻ ከወትሮው ጠንከር፣ ጠጠር ያለ በመሆኑ ትዕግስትን ይፈትናል፡፡ እንዲህም ሆኖ ወደ ውስጥ ስንዘልቅ ማረፊያ ክፍሎች በሙሉ መያዛቸው ተነግሮን ቀኝ ኋላ ለመዞር ተገደድን፤...