የመካከለኛው ምስራቅሀገሮች ከጊዜ ወደ ጊዜ በሙስና እየተዘፈቁ መምጣታቸውን ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሺናል የተባለ
ኣንድ የጥናት ተቐም ኣስታወቀ። መቀመጫውን በጀርመን ሀገር ያደረገው ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሺናል ዛሬ ባወጣው
ዓመታዊ ሪፖርቱ በተለይ
በቀጠናው ከተቀጣጠለው የዓረብ ዓብዮት ወዲህ ደግሞ በመከከለኛው ምስራቅ ሀገሮች የሚታየው የሙስና ይዞታ እጅግ
ተባብሷል። በኣጠቃላይ የመካከለኛው ምስራቅ ኣገሮች ሁሉም ማለት ይቻላል ያላቸው ነጥብ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ
ከተቀመጠው ኣማካኝ የሙስና የጥብ በታች ሲሆን በትራንስፓረንሲ ኢኒተርናሺናል መመዘኛ መሰረት በዓለም ዓቀፍ ደረጃ
የተቀመጠው ኣማካኝ የሙስና ነጥብም 43 ነው
ዓለም ዓቀፉ የሙስና ጥናት ተቐም ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሺናል ዛሬ ባወጣው ዓመታዊ ዘገባ በመካከለኛው
ምስራቅ ኣገሮች ሙስና እየተስፋፋ መሆኑን እና በአካባቢው የተቀጣጠለውን የአረብ አብዮት ተከትሎም ስርዓት ኣልበኝነት እየሰፈነ መሆኑን ኣጋለጠ። ዓለም ዓቀፍ ግልጽነት ወይንም ትራንስፓረንሲ ኢንረርናሺናል በየመን በሶሪያ እና በሊቢያ የሰፈነው ኣለመረጋጋት ለሙስና መስፋፋት ምቹ ሁኔታ መሆኑን ኣስታውቐል። በመካከለኛው ምስራቅ ኣገራት ይታያል ያለውን የሙስና መጠን የደረጃ ሰንጠረቭም ኣውጥቷል። በሰንጠረቩ መሰረት 0 በከፍተኛ ደረጃ በሙስና መዘፈቅን ሲጠቁም 100 ደግሞ ከሙስና ነጻ መሆንን ያመለክታል።
በዚሁ መሰረት የመን ከነበረችበት በ5 እርከን ኣሽቆልቁላ 18 ነጥብ ሲኖራት ሶሪያ ደግሞ በ9 እርከን ቁልቁል
ተንደርድራ 17 ነጥብ ተሰቷታል። ሊቢያም እንደዚሁ በ6 እርከኖች ወደኃላ ተመልሳ 15 ነጥብ ስታገኝ ኢራቅም
በ2003 ባስተናገደችው የUS አሜሪካ ወረራ ጊዜ ከተዘፈቀችበት የሙስና አዘቅት ሳትወጣ ከ18 ወደ 16 ወርዳ
ትገኛለች። በተቐሙ ዓመታዊ የሙስና ደረጃ ሰንጠረዥ መሰረት የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ከ5 4ቱ እጅ ከ50 ነጥብ
በታች ናቸው። የአካባቢው ሀገራት አማካኝ የሙስና ይዞታ 37 ነጥብ ሲሆን ይህም በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ከተመዘገበው
ኣማካኝ ነጥብ በታች መሆኑ ነው። በዓለም ዓቀፍ ደረጃ የተመዘገበው ኣማካኝ የሙስና ይዞታ ነጥብም በሪፖርቱ መሰረት
43 ነው።
ወትሮውንም በቐፍ ያለው የመካከለኛው ምስራቅ ኣገሮች የሙስና ይዞታ በተለይ ደግሞ በቀውስ ወቅት ከልክ ያለፈ እንደሚሆን የትራንስፓረንሲ ኢንተርናሺናል የመካከለኛው ምስራቅ እና ሰሜን ኣፍሪካ ቀጠና ዳይሬክተር ክሪስቶፈር ዊልኬ ኣስታውቐል። ለዓመታት በኣገሪቱ ስልጣን ላይ የነበሩት የየመን ፕሬዝዳንት ዓሊ አብደላ ሳሊህ በአመጽ መወገዳቸውን ተከትሎ በኣገሪቱ የጦር ኃይሎች የፖሊስ ሰራዊት እና በመንግስት መ/ቤቶች የተንሰራፋው ሙስና ኣሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የጠቀሰው ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሺናል ወትሮውንም ጉርሻ እና እጅ መንሻ በተለመደባት ሊቢያ ለ42 ዓመታት የዘለቀው የመዑመር ጋዳፊ ኣገዛዝ ከተወገደ ወዲህ ሙስናን በጥቂቱ ለማሻሻል እየተሞከረ መሆኑን ኣስታውቐል። ባለፈው ዓመት ለምሳሌ የሊቢያው ጠ/ሚ/ር አልዚዳን ባወጡት የቁጥጥር መመሪያ መሰረት ጋዳፊን ሲወጉ ለነበሩት ኣማጺያን ይከፈል የነበረውን ደሞዝ ወደ 3000 ዲናር($2300) ከፍ ሲያደርጉ በስም ዝርዝር ብቻ ተመዝግበው ደሞዝ ይከፈላቸው የነበሩ ነገር ግን በአካል የሌሉ 250 000 ሰው አልባ ስም ዝርዝሮች ሊጋለጡ ችሏል።በሶሪያም ከቀውሱ ጋር በተያያዘ ስርዓት ዓልበኝነት በመስፈኑ ሙስና በእጅጉ ሲስፋፋ በግብጽ ግን የሙስናው ይዞታ በነበረበት 32 ነጥብ ላይ እንደሚገኝ ሪፖርቱ ያመለክታል። የመካከለኛው ምስራቅ ኣገሮች የሙስና ጥልቀት ይላሉ የትራንስፓረንሲ ኢንተርናሺናል ዳይሬክተር ዊልኪ በእያንዳንዱ የመንግስት መ/ቤትና እንደ ፖሊስ የፍትህ አካላትና አቃቢያነህግጋት ያሉትን ሁሉ ሲያጠቃልል በህዝባዊ ተቐማት ውስጥም በተመሳሳይ መልኩ ስር የሰደደ ችግር ነው።
በዓለም ዓቀፍ ደረጃ በ177 ኣገራት ላይ በተካሄደ የሙስና ይዞታ ጥናት መሰረት ደግሞ ደንማርክ እና ኒውዚላንድ 91 ነጥብ በመያዝ በዓለማችን ሙስናን በእጅጉ ያመናመኑ ኣገሮች ሊሆኑ ችሏል። በመቀጠልም ፊንላንድ ስዊድን ኖርዌይ ኣውስትራሊያ እና ከናዳ እኩል በ81 ነጥብ ሲከተሉ ብሪታኒያም 76 ነጥብ በመያዝ 14ኛ ሆናለች። US አሜሪካ ደግሞ ከኡራጉዋይ ጋር እኩል 73 ነጥብ በማግኘት 19ኛ ስትሆን ኣፍጋኒስታን ሰሜን ኮሪያና ሶማሊያ ደግሞ እያንዳንዳቸው 8 ነጥብ ብቻ በመያዝ የዓለማችን የመጨረሻዎቹ የሙስና ዝቅጠት ውስጥ ይገኛሉ ተብሏል።
ጃፈር ዓሊ
ተክሌ የኋላ
Source: www.dw.de
ዓለም ዓቀፉ የሙስና ጥናት ተቐም ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሺናል ዛሬ ባወጣው ዓመታዊ ዘገባ በመካከለኛው
ምስራቅ ኣገሮች ሙስና እየተስፋፋ መሆኑን እና በአካባቢው የተቀጣጠለውን የአረብ አብዮት ተከትሎም ስርዓት ኣልበኝነት እየሰፈነ መሆኑን ኣጋለጠ። ዓለም ዓቀፍ ግልጽነት ወይንም ትራንስፓረንሲ ኢንረርናሺናል በየመን በሶሪያ እና በሊቢያ የሰፈነው ኣለመረጋጋት ለሙስና መስፋፋት ምቹ ሁኔታ መሆኑን ኣስታውቐል። በመካከለኛው ምስራቅ ኣገራት ይታያል ያለውን የሙስና መጠን የደረጃ ሰንጠረቭም ኣውጥቷል። በሰንጠረቩ መሰረት 0 በከፍተኛ ደረጃ በሙስና መዘፈቅን ሲጠቁም 100 ደግሞ ከሙስና ነጻ መሆንን ያመለክታል።
ወትሮውንም በቐፍ ያለው የመካከለኛው ምስራቅ ኣገሮች የሙስና ይዞታ በተለይ ደግሞ በቀውስ ወቅት ከልክ ያለፈ እንደሚሆን የትራንስፓረንሲ ኢንተርናሺናል የመካከለኛው ምስራቅ እና ሰሜን ኣፍሪካ ቀጠና ዳይሬክተር ክሪስቶፈር ዊልኬ ኣስታውቐል። ለዓመታት በኣገሪቱ ስልጣን ላይ የነበሩት የየመን ፕሬዝዳንት ዓሊ አብደላ ሳሊህ በአመጽ መወገዳቸውን ተከትሎ በኣገሪቱ የጦር ኃይሎች የፖሊስ ሰራዊት እና በመንግስት መ/ቤቶች የተንሰራፋው ሙስና ኣሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የጠቀሰው ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሺናል ወትሮውንም ጉርሻ እና እጅ መንሻ በተለመደባት ሊቢያ ለ42 ዓመታት የዘለቀው የመዑመር ጋዳፊ ኣገዛዝ ከተወገደ ወዲህ ሙስናን በጥቂቱ ለማሻሻል እየተሞከረ መሆኑን ኣስታውቐል። ባለፈው ዓመት ለምሳሌ የሊቢያው ጠ/ሚ/ር አልዚዳን ባወጡት የቁጥጥር መመሪያ መሰረት ጋዳፊን ሲወጉ ለነበሩት ኣማጺያን ይከፈል የነበረውን ደሞዝ ወደ 3000 ዲናር($2300) ከፍ ሲያደርጉ በስም ዝርዝር ብቻ ተመዝግበው ደሞዝ ይከፈላቸው የነበሩ ነገር ግን በአካል የሌሉ 250 000 ሰው አልባ ስም ዝርዝሮች ሊጋለጡ ችሏል።በሶሪያም ከቀውሱ ጋር በተያያዘ ስርዓት ዓልበኝነት በመስፈኑ ሙስና በእጅጉ ሲስፋፋ በግብጽ ግን የሙስናው ይዞታ በነበረበት 32 ነጥብ ላይ እንደሚገኝ ሪፖርቱ ያመለክታል። የመካከለኛው ምስራቅ ኣገሮች የሙስና ጥልቀት ይላሉ የትራንስፓረንሲ ኢንተርናሺናል ዳይሬክተር ዊልኪ በእያንዳንዱ የመንግስት መ/ቤትና እንደ ፖሊስ የፍትህ አካላትና አቃቢያነህግጋት ያሉትን ሁሉ ሲያጠቃልል በህዝባዊ ተቐማት ውስጥም በተመሳሳይ መልኩ ስር የሰደደ ችግር ነው።
በዓለም ዓቀፍ ደረጃ በ177 ኣገራት ላይ በተካሄደ የሙስና ይዞታ ጥናት መሰረት ደግሞ ደንማርክ እና ኒውዚላንድ 91 ነጥብ በመያዝ በዓለማችን ሙስናን በእጅጉ ያመናመኑ ኣገሮች ሊሆኑ ችሏል። በመቀጠልም ፊንላንድ ስዊድን ኖርዌይ ኣውስትራሊያ እና ከናዳ እኩል በ81 ነጥብ ሲከተሉ ብሪታኒያም 76 ነጥብ በመያዝ 14ኛ ሆናለች። US አሜሪካ ደግሞ ከኡራጉዋይ ጋር እኩል 73 ነጥብ በማግኘት 19ኛ ስትሆን ኣፍጋኒስታን ሰሜን ኮሪያና ሶማሊያ ደግሞ እያንዳንዳቸው 8 ነጥብ ብቻ በመያዝ የዓለማችን የመጨረሻዎቹ የሙስና ዝቅጠት ውስጥ ይገኛሉ ተብሏል።
ጃፈር ዓሊ
ተክሌ የኋላ
Source: www.dw.de
No comments:
Post a Comment