ደቡብ ሱዳን ከግብፅ ጋ የሁለትዮሽ ወታደራዊ ትብብር ስምምነት መፈራረሟን ዘገባዎች ያመለክታሉ። ጁባ ተመሳሳይ መግባባት ላይ ከሁለት ዓመታት በፊት ከተነጠለቻት ሰሜን ሱዳን ጋም መድረሷ ተገልጿል።
ሱዳን ትሪቢዩን እንደሚለዉ የደቡብ ሱዳን እና ግብፅ ወታደራዊ ትብብር መፈራረም ይፋ የተደረገዉ በጁባ መንግስት ሥር
በሚተዳደረዉ የደቡብ ሱዳን ቴሌቪዥን ነዉ። በመከላከያ ሚኒስትር ኩሎ ማንያንጋ ጁኩ የሚመራ የደቡብ ሱዳን የልዑካን
ቡድን ካይሮን በጎበኘበት ወቅት ነዉ ካይሮና ጁባ የሁለትዮሽ ወታደራዊ ትብብር ስምምነቱን የተፈራረሙት። ዝርዝር
ስምምነቱ ይፋ ባይሆንም የዜና አዉታሩ ወታደራዊ ምንጮቹን ጠቅሶ እንደዘገበዉ የወታደራዊ ኃይሎች የልምድ ልዉዉጥ፣
ልዩ ኃይሎችን የማሰልጠን እና በጋራ ልምምዶችን ማድረግን ያካትታል። ግብፅም ሆነች ደቡብ ሱዳን አሁን በሚገኙበት
ያልተረጋጋ ሁኔታ ሊፈራረሙ የሚችሉት ወታደራዊ ስምምነት