ካሣሁን ዓለሙ:-
ሃይማኖት በሥርዎ ቃሉ ማመንና መታመን የሚሉ ፅንሣተ-ሐሣብን የያዘ ቃል ነው፡፡ ማመን በአንድ ነገር ላይ እምነት ማሳደር ሲሆን መታመን ደግሞ ላመኑበት ነገር መታገልና መቆም ነው፡፡ ይህንን ይዘን ወደ ፍልስፍናው መከራከሪያ ስንገባ በዓለማችን የሚገኙ የሃይማኖት ይዘቶችን በሦስት ከፍለን ልንያቸው እንችላለን፡፡
1) በእግዚአብሔር ህልውነት ላይ የተመሠረተ ሃይማኖት (Theist)
የእግዚአብሔር ህልውነትን በማመንና እሱን በመመሥከር እግዚአብሔር ከፍጥረቱ ጋር ግኑኝነት የሚያደርግ በሥራው ፍፁም የሆነ አምላክ መሆኑን ይቀበላል፡፡ ስለሆነም የሰው ልጆች ከእነሱ በላይና ፍጹም ከኾነ ኃይል ጋር ግንኙነት ያደርጋሉ፤ እሱም በመገለጥ ስለ ዐለማትና ፍጥረታት አፈጣጠር፣ ስለ ሰው ልጆች መፈጠርና ህልውና ነግሯቸዋል፤ ያነጋግራቸዋል ብሎ ያምና፤ ለዚህም ጥብቅና ቆሞ ይመሠክራል፤ ይከራከራል፡፡
2) በእግዚአብሔር አለመኖር ላይ የተመሠረተ ሃይማኖት (Atheist)
ይኸ
የእግዚአብሔርን ህልውነት የሚክድና ለዚያም አቋም ጥብቅና የቆመ ሃይማኖት መሰል አስተምህሮ ነው፡፡ይህም ሃይማኖት የራሱ መታወቂያ አለው፡፡ በአንድ በኩል ሰይጣንን በግል እያመለከ የእግዚአብሔርን ህልውነት የሚቃወም ሲሆን በአብዛኛው በኢሉምናቲ የሚሥጢር ማኅበራት የሚቀነቀን ነው፤ ምሥጢራዊነቱም ያመዝናል፡፡ ስለዚህ በግልፅና በተቋማዊ አደረጃጀት የማይታወቅ ቢመስልም በአብዛኛው በሳይንስና በፍልስፍና አስተምህሮ ተወሽቆ እምነቱ ተቀባይነት አግኝቶ እንዲስፋፋ ጥረት ይደረግለታል፡፡ የዚህ ሃይማኖት አቀንቃኞች በዋናነትዝግመተ ለውጠኛችና ቁሳካላዊያን ናቸው፡፡ለምሳሌ እንደ ፈርደሪክ ኒቼ፣ ካርል ማርክስ፣ ሌኒን፣ ዳሪዊን፣ ሪቻርድ ዳውኪንስና መሰሎቻቸውን መጥቀስይ ቻላል፡፡
3) ‹አሊለም› (እግዚአብሔር አለ-የለም) ሃይማኖት (Agnostic)
የእዚህ ሃይማኖት መነሻው ልቃዊነት (Liberalism) ማሳለጫው ምንፍቅና (Skeptic) ተግባሩም
ውል
አልባነትና ግደለሽነት (indifference) ነው፡፡ የመከራከሪያ ስልቱም ዥዋዥዌ መጫወት ነው፡፡