ኢትዮጵያዊው ቢስማርክ ዳግማዊ ምኒልክ፣ አገር ለማስገበር ካደረጓቸው ዘመቻዎች ውስጥ ትልቅ ምከታ የገጠማቸው አርሲ ላይ ነው፡፡ ምኒልክ በአርሲዎች ክንድ ተከታታይ ሽንፈት ከቀመሱ በኋላ፣ በራስ ወልደ ገብርኤልና በራስ ዳርጌ እልክ አስጨራሽ ዘመቻ አማካኝነት፣ አሸንፈው አርሲን ወደ ግዛታቸው ቀላቀሉት፡: በጦርነቱ ከአስገባሪውና ከገባሪው ወገን አያሌ ወታደሮች አልቀዋል፡፡
ውጊያው የተካሄደው፣ነፍጥ በታጠቁ የንጉሱ ወታደሮችና ከጦርና ጋሻ ፈረስ ውጭ ምንም በሌላቸው የአርሲ ጎበዞች መካከል በመሆኑ፣ ከተከላካዩ ወገን ያለቀው በቁጥር እንደሚልቅ እሙን ነው፡፡ የአርሲ ጦርነት ከተካሄደ ከጥቂት አመታት በኋላ፣ ወደ ኦሮሞ ምድር የደረሰው ደ ሳልቪያክ የተባለ የፈረንሳይ ሀዋርያ ከአርሲዎች በሰበሰበው መረጃ ተመስርቶ እንደጻፈው፣ ራስ ወልደገብርኤል የአርሲዎችን አይበገሬነት ለመስበር ባንድ ቀን ብቻ የአራት መቶ አንጋፋዎችን ክንድ አስቆርጠዋል፡፡ይህ ጻሀፊ፣ ክንዳቸውን ካጡት ትልልቅ ሰዎች ጥቂቶቹን ባይኔ በብረቱ አይቻለሁ ብሏል፡፡

ይህ የታሪክ ዘገባ በዘመናችን ፖለቲከኞች ሁለት ዓይነት ምላሽ እየተሰጠው ነው፡፡ የመጀመሪያው ምላሽ ክስተቱን ‹‹አይደረግም›› ብሎ መካድ ሲሆን፤ በተቃራኒ ወገን ያለው ደግሞ በማጋነንና በማራገብ ተጠምዷል፡፡ባለፈው ሳምንት ሀብታሙ አያሌው የተባለ ጸሀፊ በዚህች መጽሔት ላይ ሲጽፍ፣ የአርሲን የበደል ታሪክ፣ የቡርቃ ዝምታ ልቦለድ ውጤት እንደሆነ ሊያሳምነን ይፈልጋል፡፡ በኔ አስተያየት ይሄ አይነቱ ድርቅና ማንንም አይጠቅምም፡፡ አርሲ በስጦታ ወይም በስምምነት የተደባለቀ አገር አይደለም፡፡ የተገኘው በብዙ አገሮች እንደተደረገው፣ በጉልበትና በነውጥ ነው፡፡በወቅቱ ሰብአዊ ጥሰቶች በገባሪው ወገን ላይ መድረሳቸውን መካድ አስፈላጊ አይደለም፡፡
ሌላው ‹‹እፍኝ ቆሎ ይዞ ወደ አሻሮ›› የሚጠጋው የብሄርተኛው ወገን ነው፡፡ ይህ ወገን፣ የእምቢተኛ ወታደር እጅ ተቆረጠ ሲባል፤ ‹‹ሰላማዊ ሴቶች በሰልፍ እንዲያልፉ ተደርጎ ጡታቸው ተቆረጠ፣ አባዱላዎች ተመርጠው እንዲኮላሹ ተደረገ፡፡ ሚኒልክ ነፍጥ አልበቃ ብሏቸው፣ ፈንጣጣ ፈብርከው ህዝባችንን ፈጁ››እያለ በተደረገው ላይ ያልተደረገ የምናብ ፍሬ እየጨመረ የሚተርት ነው፡፡በተለይ አንዳንድ ምሁራን ከዚህ አልፈው ጦርነቱ በወራሪው አማራና በሰላማዊው ኦሮሞ መካከል እንደተካሄደው አድርገው ለማቅረብ መሞከራቸው አሳዛኝ ነው፡፡ የዚህ ዓይነቱን ፕሮፖጋንዳ ውጤት፣ ዛሬ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች እያየነው ነው፡፡

በሌላ በኩል በጉልበት ሌላውን ማስገበር አያሌ ህዝቦች በፈረቃ ያደረጉት ሆኖ ሳለ፣ አንድ ንጉስና አንድ ብሄረሰብ ብቻ በሞኖፖል የያዘው አድርገው ለማሳየት የሚሞክሩ አሉ፡፡ የዚህ ጽሁፍ አላማ፣ ከላይ የተጠቀሱትን ጠማማ አስተሳሰቦች ማቃናት ነው፡፡ እስቲ ምኒልክን በጭራቆች ወይም በመላእክት ቦታ ለመመደብ ከመቸኮላችን በፊት፣ ከምኒልክ በፊት ገባር ህዝቦች ምን አይነት ያኗኗር ዘይቤ ይከተሉ እንደነበር እንመልከት፤ ከአርሲ እንጀምር፡፡
ቅድመ-ምኒልክ አርሲ
ዊልያም ሐሪስ የተባለ በምኒልክ አያት በሳህለስላሴ ዘመን ሸዋንና አካባቢውን የጎበኘ አሳሽ፣ በጊዜው ስለነበረው የአርሲ ማህበረሰብ ሲነግረን እንዲህ ይላል፡-
‹‹Sahlesilase has never attempted an expedition I person against these war-hawks nestled in the lap of the mountains who fight stark naked and are besmeared with lard from head to foot. Merciless, and predatory habits, they are represented as extremely powerful in a battle and are the terror of every surrounding tribe (257)››
(‹‹ሳህለስላሴ በተራራ እቅፍ ውስጥ ለሚኖሩት፣ከላይ እስከታች ሰውነታቸውን በስብ ተለቅልቀው ራቁታቸውን የመዋጋት ልምድ ያላቸውን የጦር-ጭልፊቶች የሚመራ ጦር መርተው ሊዘምቱባቸው አልሞከሩም፡፡ ርህራሄ አልባና ሌላውን በማጥቃት ልማድ ያላቸው ሲሆኑ በጦር ሃያላንና በዙርያቸው ያሉትን ጎሳዎች የሚያሸብሩ እንደሆኑ ይነገርላቸዋል፡፡>>)
ሀሪስ ገለጻውን በመቀጠል፣ የዘመኑ አርሲ ወንዶች በውጊያ ላይ አንዱን ፈረስ ለሁለት ተፈናጠው እየተጋገዙ እንደሚዋጉ፤ እንደ መጋዝ ጥርስ ያለው ጦርና በኤሊ ድንጋይ አምሳል የተሰራ ጋሻ ለውጊያ እንደሚጠቀሙ መዝግቧል፡፡ በማስከተልም፡-

‹‹Subsisting entirely by plunder, the cultivation of their high cold hills is but little attended (257)››
(‹‹ሙሉ በሙሉ በዘረፋ ስለሚኖሩ በአብራጃው ያለውን አዝመራቸውን እምብዛም አይደክሙበትም፡፡››) ሀሪስ ባካባቢው በነበረበት ወቅት አንድ የአርሲ ቡድን በከረዩ አርብቶ አደሮች ላይ አደጋ ጥሎ፣አርብቶ አደሮቹን ሁሉ በጦር በመግደል፣ ከብት ዘርፎ መሸሹን ዘግቧል፡፡
የጥንቶቹ አርሲዎች በገዳ ሥርአት በመተዳደርና በቋንቋ ከሌላው የኦሮሞ ጎሳዎች ጋር አንድ ቢሆኑም ያኗኗር ስርአታቸው ከሌሎች በበለጠ ነውጠኛ ነበር ይባላል፡፡ ሀንቲንግፎርድ ‹‹The Oromo of Ethiopia, the Kingdoms of kafa and Janjero›› በተባለው መጽሐፉ፡-

‹‹Even the rest of the Oromo themselves looked up on Arsi as especially ferocious, for them to murder at the time of great festivals, is both an honor and a social necessity ,though if an Arusi kills a fellow-tribesman it is believed that he will get leprosy; but inter-tribal murders are allowed without penalty, particularly at the end of each Luba period. Before setting out to commit a “murder for honor>> the Arusi drinks large quantities of blood, which produces a condition of frenzy. Since the murder nearly always a cowardly one, they hide and kill unsuspecting wayfarers, emasculating them and taking home the genitals a trophy .On their return the murderers enact the scene, with cries of triumph and derisive imitation of the victim’s anguish. Only after such a murder may a man wear a copper ring in his ear. When several men take part in a murder, the honor goes to him who strikes the first blow. Hence there is often much quarreling. A man who sets out before a festival to kill and returns unsuccessful is not only ridiculed, but is branded on the forehead and given a small jar of milk which he has to make into butter as a sign that he is not a man.no man could hold a position in the gadaa-government unless he had killed a man or a large animal (p 64)
(ትርጉሙ ከሞላ ጎደል እንደሚከተለው ሊቀርብ ይችላል፡፡
“ሌሎች የኦሮሞ ጎሳዎች ሳይቀሩ አርሲዎች የተለየ ጭካኔ እንደነበራቸው ያምኑ ነበር፡፡ለነሱ እያንዳንዱ ክብረ- በአል መጨረሻ ላይ ሰው መግደል የክብር ምልክት እና ማህበራዊ ግዴታ ተደርጎ ይወሰድ ነበር፡፡አንድ አርሲ ሌላውን አርሲ ከገደለ በለምጽ ይመታል የሚል እምነት ነበር፡፡ይሁን እንጂ የሌላውን ጎሳ አባል እንዲገድል ተፈቅዶለታል፡፡አንድ አርሲ ለግድያ ከመሰማራቱ በፊት ለወኔው ማነሳሻ ብዙ የከብት ደም ይጠጣል፡፡ከዚያም አገር አማን ነው ብሎ የሚሄደውን መንገደኛ አድብቶ ይገድልና ብልቱን ቆርጦ ወደ ጎጆው ይመለሳል፡፡ሲመለስ ፉከራ ያሰማል፡፡እንዲሁም የተገደለው ሰውየ ያሰማውን የጣእር ድምጽ አስመስሎ በመጮህ ያፌዛል፡፡አንድ ወንድ ይህንን ማድረግ ከቻለ ብቻ ነው በጆሮው ላይ የብር ሎቲ ማንጠልጠል የሚፈቀድለት፡፡
ግድያው የተፈጸመው በቡድን ከሆነ፣ የመጀመርያውን በትር ያሳረፈው የገዳይነቱን ክብር ይቀዳጃል፡፡ በዚህ ምክንያት ( እኔ ነኝ የቀደምሁ በሚል ፉክክር) ጠብ የሚቀሰቀስበት አጋጣሚ ብዙ ነው፡፡ከክብረበአሉ በፊት ሰው ገድሎ መመለስ ያልቻለ ሰው ውርደት ይከናነባል፡፡..አንድ ሰው ትልቅ አውሬ ወይም ሰው ካልገደለ በቀር በገዳ ስርአት ውስጥ ቦታ አይኖረውም፡፡”)

የምኒልክ ሰራዊት ፈጸመ የሚባለውን ግፍ ከዚህ ታሪካዊ መደላደል ላይ ቆምን ካላየነው በቀር ቀና ፍርድ ልንፈርድ አንችልም፡፡በቅርቡ፣መብራትና ውሀ ብርቅ በሆነበት የአርሲ ገጠራማ መንደር ውስጥ ሀያ ሚሊዮን ብር የፈጀ ሀውልት ተገንብቷል፡፡ከሀውልቱ ጀርባ ያሉ ፖለቲከኞችና ባለስልጣኖች ለምን ይህን አደረጉ? ምናልባት በማስገበር ጦርነቱ የወደቁትንና አካላቸው የጎደለባቸውን ማሰብ ፈልገው ይሆናል እንበል፡፡ጉዳዩን እስቲ በሰብአዊነት ሚዘን እንመልከተው፡፡ በምኒልክ የጦር አበጋዞች አማካኝነት በነፍጥ ለረገፉና እጃቸውን ለተቆረጡ የአርሲ ወታደሮች የሚቆረቆር ዜጋ፣ እግረመንገዱን ቀደምት አርሲዎች ለክብር ሲሉ በየጊዜው በወጡበት የሚያስቀሯቸውን የሌላ ብሄር ተወላጆችን ግፍ ማስታወስ አይጠበቅበትምን?? ማስታወስ ማለት የተወጋነውን ብቻ መርጦ ማስታወስ ማለት አይደለም፡፡ በአባቴ ላይ የደረሰውን ግፍ አልረሳም የሚል ሰው አባቱ በሌሎች ላይ ያደረሰውን ግፍም አብሮ ለማስታወስ ወኔው ሊኖረው ይገባል፡፡ አለበለዚያ የአንዱ ሕይወት ከሌላው ህይወት የበለጠ ዋጋ አለው ወደሚል አድልኦ ይመራል፡፡ይህ ደግሞ ከዘረኝት ውጭ ሌላ ሊሆን አይችልም፡፡
ጆርጅ ኦርዌል ‹‹on nationalism›› በተባለው ዝነኛ መጣጥፉ ‹‹ብሄርተኛው የራሱ ወገን የፈጸመውን ግፍ አለማውገዝ ብቻ ሳይሆን ግፉን ለመደበቅ ያለው ችሎታም አስገራሚ ነው፡፡›› ይላል፡፡ ይህን ችሎታ ለአብነት ያህል፣ የአኖሌ ርእዮተ- አለም ዋና አቀንቃኝ በሆኑት በፕሮፌሰር ሀጂ አባስ ገናሞ ሀሳቦች ውስጥ ማየት ይቻላል፡፡ ፕሮፌሰሩ፣ በቅርቡ ‹ኦፕራይድ› በተባለ ብሎግ ላይ በሰጡት ቃለ-መጠይቅ የምኒልክን ሠራዊት የአርሲ ሴቶችን በመጨፍጨፍ ከወነጀሉት በበኋላ፡-
‹‹in Oromo culture women are woyuu (sacred) and were not the object of targeted attacks or killing during atrocious wars›› (በኦሮሞ ባህል ውስጥ ሴቶች ቅዱሳን ናቸው፡፡ጭካኔ በተሞላበት ጦርነት ውስጥ የጥቃት ኢላማ አይሆኑም፡፡አይገደሉም፡፡››) በማለት የራሳቸው ወገን ሴትን በጦርነት እንደማይጎዳ ይነግሩናል፡፡

ይህ በኔ እይታ መመጻደቅ ይመስለኛል፡፡እንኳን ያኔ፣ የተሻሻሉ የጦርነት ህጎች በሰፈኑበት በዛሬው ዘመን እንኳ፣ ለወንዶች የተደገሰው ሞት ለሴቶችም ሲተርፍ በየሚድያው እናያለን፡፡ ጸሐፌ ትእዛዝ ገብረስላሴ ታሪክ ዘመን ዘዳግማዊ ምኒልክ ‹‹በተባለው መጽሀፋቸው፣ በአርሲና በንጉሱ ሰራዊት መካከል የተደረገ አንድ ውጊያ ከዘገቡ በኋላ‹‹በዚያን ቀን ኮጂ የሚባል አሩሲ ጦርነቱ ከቀኑ ሌት ነውና ከደጃች ወልዴ ሰፈር አደጋ ጥሎ ሴትም አሽከርም(ትንንሽ ልጆች ለማለት ነው) ሰባት መቶ ያህል ገደለ፡፡›› (ገጽ…139) ይላሉ፡፡
ይህን ዘገባ የተጉለቴ ደብተራ ድርሰት ነው ብለው ሊያጣጥሉት የሚሞክሩ እንደሚኖሩ እገምታለሁ፡፡ይሁን እንጂ ዘገባው እነ ፕሮፌሰር አባስ ዋቢ በሚጠሯቸው ምስክሮች ሳይቀር የተረጋገጠ ነው፡፡እኒህ ፕሮፌሰር‹‹በሀቀኛ ዘጋቢነቱ››የሚመኩበት ማርቲያል ደ ሳልቪያክ ከአርሲ ወታደሮች የሰማውን ገድል ሲተርክልን፣ የአርሲ ወታደሮች የምኒልክን ሰፈር ሲቆጣጠሩ ዘማቾችን ተከትለው የመጡትን ሴቶች የደገጠማቸውን እጣ እንደሚከተለው ይተርክልናል፡-
‹‹The Abyssinian women witness of a complete disaster threw their children into the abyss and threw themselves down. The Oromo arriving unexpectedly threw down those that remained›› ይላል፡፡
(‹‹የአቢሲኒያ ሴቶች የመጣውን መአት ሲያዩ ልጆቻቸውን ወደ ገደል ወርውረው እነሱም ተወረወሩ፡፡ኦሮሞዎች ባልተጠበቀ ሁኔታ ደርሰው የተረፉትን ወረወሯቸው፡፡››) ይላል፡፡
ይህንንእና ሌሎች ለጊዜው የማቆያቸውን አያሌ መረጃዎችን ስናይ፣ በጦርነት ወቅት ሴትን ማጥቃት በጊዜው የነበሩት ሁሉ ያደርጉት የነበረ እንጂ፣ ለአንድ ብሄረሰብ ብቻ የተሰጠ እንዳልነበረ እንገነዘባለን፡፡

የጎሳ ፖለቲካ የታሪክ አተረጓጎም ዋናው ችግር፣ ታሪካዊ በደሎች የመነጩት ከዘመኑ መንፈስ ሆኖ ሳለ ከአንድ ብሄር ተፈጥሮአዊ ጠባይ የተቀዱ አስመስሎ ማቅረቡ ነው፡፡ ብሄረሰቦች በባህልና በቋንቁ ቢለያዩም፣ ዞሮ ዞሮ የአንድ ዘመን ባሮች ናቸው፡፡ ለምሳሌ የንጉስን ክብር የደፈረን ዜጋ አካል በማጉደል መቅጣት በዮሐንስም ሆነ በምኒልክ ህገ-መንግስት በነበረው ፍትሐነገስት የተደነገገ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ከፍትሐነገስት ውጭ የነበረው ለኦሮሞ ማህበረሰብም ለዚህ አይነቱ ቅጣት እንግዳ አልነበረም፡፡ ለምሳሌ በኦሮሞ ህግ ከሌላ ሰው ጋር ሲያመነዝር እጅ ከፍንጅ የተያዘ ሰው እጅና እግሩን ይቆረጥ እንደ ነበር ዲአባዲን ጠቅሶ ሀንቲንግፎርድ ዘግቧል፡፡ (ሀንቲንግፎርድ፣ ከላይ ከተጠቀሰው ገጽ 62)
ይሁን እንጂ ከጥንት ጀምሮ በሰውነት ድካማቸው የተነሳ እጅና እግራቸውን ስላጡ ኦሮሞዎች ተቆርቁሮ ሀውልት ለማቆም የሞከረ አልነበረም፡፡ስለዚህ ጉዳዩ ጭካኔን የማውገዝ፣ ሰብአዊነትን የማክበር ጉዳይ ሳይሆን፣ አንዱን ወገን ጭራቅ አድርጎ ለማሳየት ይመስላል፡፡
ምኒልክ ባደረጉት የማስገበር ዘመቻ የተሳተፈው ሰራዊት ህብረ-ብሄራዊ መሆኑ እሙን ነው፡፡ይልቁንም ኦሮሞ ያልተሳተፈበትን የምኒልክ ዘመቻ ማግኘት ከባድ ነው፡፡ ወላይታንና ከፋን ለማስገበር በተደረጉት ዘመቻዎች አባ ጅፋር የኦሮሞ ፈረሰኛ ጦር ይዞ ከመዋጋቱ በላይ፣ የምርኮ ተካፋይ እንደ ነበር በሌላ መጣጥፍ በዝርዝር ለማየት እንሞክራለን፡፡ በአርሲም ከዚህ የተለየ አይደለም፡፡ ቸሩሊ ‹‹የኦሮሞ ሕዝብ ሥነቃል›› በተሰኘው ስራቸው መዝግበው እንዳቆዩልን፣ በአርሲ ዘመቻ ግንባር ከሚኒልክ ወገን ቀደም ዘማቾች አንዱ ፊታውራሪ ዱፌራ የሚመራ የኦሮሞ ጦር ነበር፡፡ ባስገባሪውና በገባሪው በኩል የቀረቡ ተቃራኒ ይዘት ያላቸው የኦሮምኛ ፉከራዎች ይህንኑ ሐቅ ያረጋግጣሉ፡፡አሌክሳንደር ቡላቶቪች የተባለው የሩስያ ወዶገብ ወታደር በዘመኑ የታዘበውን ሲመሰክር፣ in recent subjugation of the Oromo by the Abyssinians,the most violent fighters in the ranks of the Abyssinians were themselves Oromo.›› ይላል፡፡
(‹‹ኦሮሞን ለማስገበር በቅርቡ ባበሻዎች በተደረገው ባበሻው ሰራዊት ውስጥ እጅግ ነውጠኛ የሚባሉት ተዋጊዎች ራሳቸው የኦሮሞ ተወላጅ ነበሩ፡፡›› ነገሩን የጠቀስኩት አሮሞዎች ከሌላው የበለጠ ነውጠኞች ነበሩ የሚል መልክት ለማስተላለፍ አይደለም፡፡የምኒልክ ሰራዊት ከብዙ ብሄር የተውጣጣ ሰራዊት መሆኑን ለማስታወስ ያክል ነው፡፡ይሄን ማስታወስ ‹‹የሞትንም እኛ ያለንም እኛ›› የሚለውን እውነታ አስረድቶ ያቻችለናል፡፡

አንዳንድ ሰዎች እንደሚሉት በአርሲ ጦርነት የሴቶች ጡት ተቆርጦ ከሆነ፣ በጊዜው የነበሩት የታሪክ ጸሐፊዎች ለምን አልመዘገቡትም፡፡ የሸዋ ጸሐፊዎች አለቃ አጽሜና አለቃ ገብረስላሴ በዚህ ጉዳይ ላይ የመዘገቡት ነገር የለም፡፡ እኒህ ጸሐፊያን የራሳቸው ወገን የሆነው ሠራዊት የሚፈጽመውን ግፍ በኩራት አልፎ አልፎም በወቀሳ የመዘገብ ልምድ እንዳላቸው ስናይ፣ ሆን ብለው ዘለውት ነው የሚለውን ድምዳሜ መቀበል ያቅተናል፡፡
ስለአርሲ ጦርነት መረጃ የሰበሰቡ የኦሮሞ ወዳጅ የምኒልክ ነቃፊ የሆኑ የአውሮፓ መንገደኞች ስለ ጉዳዩ ያሉት ነገር አለመኖሩ ጥርጣሬያችንን የበለጠ ያጎላዋል፡፡ ለምሳሌ ማርቲያክ ደ ሳልቪያክ ከጦርነቱ ጥቂት ጊዜ በኋላ መጥቶ፣ ከአርሲዎች በሰበሰበው መረጃ ስለጡት መቁረጥ በመጽሀፉ ውስጥ አንድም ቦታ አልዘገበም፡፡ ይህ ጸሀፊ የምኒልክ ሠራዊትን ‹‹ጭካኔ ማጋለጥ›› የህይወቱ አንድ ትልቅ ተልእኮ አድርጎ የሚቆጥር ሰው እንደመሆኑ መጠን ፣ጡት ቆረጣው ተፈጽሞ ቢሆን ኖሮ ሳይመዘግብ አያልፈውም ነበር፡፡
ጁልየ ቦረሊ የተባለው ሌላው በወረራው ዘመን የነበረ የፈረንሳይ ጎብኝ፣ ከአርሲ ዘመቻ በኋላ የወቅቱን አባ ሙዳ አነጋግሯል፡፡ከኦሮሞ ጓደኞቹ መረጃዎችን አሰባስቧል፡፡ የጡት ቆረጣን አስመልክቶ ግን ያስቀረልን አንዳች ነገር የለም፡፡ይህ ጸሐፊ ምኒልክና ጣይቱን ውሀ ቀጠነ ብሎ በመዝለፍ የታወቀ በመሆኑ፣ የንጉሱን ገመና ይደብቃል ተብሎ የሚጠረጠር አይደለም፡፡ ስለዚህ በየትኛውም አግባብ እንዲህ አይነቱን አብይ ዜና ሰምቶ ሊያልፍ የሚችልበት ምክንያት አልነበረም፡፡እንድያውም ቦረሊ በመጽሀፉ ፣ምኒልክ በአርሲ ጦርነት ወቅት አንድ በአስገባሪው ሠራዊት በኩል የተሰለፈ ወታደር(ወታደሩ ብሄሩ አልተገለጸም ) የወደቀ አርሲ ሲሰልብ አግኝተውት ሞት እንደፈረዱበት ዘግቧል፡፡ምኒልክ ብሄርተኞች እንደሚስሉት ዓይነት ጭራቅ ቢሆኑ ኖሮ፣ ሰላቢውን ወታደር ሹመት እንጂ ሞት አያቀዳጁትም ነበር፡፡
ቸሩሊ የተባሉት የጣልያን ሊቅ ‹‹የኦሮሞ ህዝብ ስነ-ቃል›› በሚል ጥናታቸው በአርሲ ወረራ ወቅት በአርሲዎች የተገጠሙ አያሌ ግጥሞችን፣ እንጉርጉሮዎችን እና ሽለላዎችን አጠራቅመው አሳትመዋል፡፡ ይሁን እንጂ ከተሰበሰቡት ግጥሞች መካከል ስለ ጡት ቆረጣ የሚያወሳ አንድም ስንኝ የለም፡፡ ይሄን የመሰለ ክስተት ደርሶ ከሆነ፣ ከአዝማሪዎች እንጉርጉሮ እንዴት አመለጠ?
በአጠቃላይ በምኒልክ ተፈጸመ የተባለው ያኖሌ ጡት ቆረጣ፣ የአገር ውስጥም ሆነ የውጭ አፍቃሬ ኦሮሞ ሰነዶች ላይ ያልተመሰረተ ለመሆኑ ይሄ በቂ ማስረጃ ይመስለኛል፡፡

አምስት ሚሊዮን ኦሮሞ?
የምኒልክን ጨፍጫፊነት ለማሳየት በብሄርተኞች ከሚጠቀሱት ጽሁፎች ዋናውና ዝነኛው፣ከሩሲያዊው ወታደር ከአሌክሳንደር ቡላቶቪቼ መጽሀፍ የተወሰደ አወዛጋቢ አንቀጽ ነው፡፡አንቀጹ በሪቻርድ ሰልተር ትርጉም እንደሚከተለው ይነበባል፡፡
‹‹በወረራው ወቅት በደረሰው ከግማሽ በላይ የሚገመተው ሕዝብ እልቂት፣ኦሮሞ ማናቸውም አይነት አመጽ የማስነሳት እድሉን አክሽፎበታል፡፡››
(The dreadful annihilation of more than half of the population during the conquest took away from the Galla all the possibility of thinking about any sort of uprising.)
ይህን ጥቅስ በመጥቀስ ምኒልክ አምስት ሚሊዮን ኦሮሞ ጨፍጭፏል የሚለውን ውንጀላ የሚያንጸባርቁ ምሁራን ጥቂት አይደሉም፡፡ ለዋቢነት ፕሮፌሰር አሰፋ ጃለታ ሩስያዊው በደፈናው‹‹እልቂት››ብሎ የጠራውን እሳቸው<<massacre>>(በጦር መሳርያ የሚደረግ ፍጅት)በሚል አጥብበው ሊተረጉሙት ሞክረዋል፡፡አንባቢ የራሱን ፍርድ እንዲሰጥ ፕሮፌሰሩ ያሉት ቃል በቃል ይሄ ነው፡፡ ‹‹የኢትዮጵያ መንግስት በቅኝ ግዛቱ መስፋፋት ጊዜ ግማሽ የሚሆነውን የኦሮሞ ህዝብ (5 ሚሊዮን) እና አመራሮቹን ፍጅቷል፡፡››
(The Ethiopian government massacred half of the oromo population (5 million) and their leadership during its colonial expansion according to Alexander Bulaovichi፡፡)
መቼም በሰናድርና በወጨፎ አምስት ሚሊዮን ህዝብ መጨረስ እንደማይቻል ለማወቅ ፈላስፋ መሆን አይጠይቅም፡፡ ይህንን ቀላል እውነት ለመረዳት ጥቂት የሂሳብ ስሌት ብቻ በቂ ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ ሚኒልክ አቶሚክ ቦምብ ቢጥሉ እንኳ ይሄን ያህል ሰው መግደል አይችሉም ነበር፡፡ ለማነጻጻርያ አሜሪካ በሄሮሺማ ላይ የጣለችው አቶሚክ ቦምብ መግደል የቻለው ሰማንያ ሺህ ሕዝብ መሆኑን እናስታውስ፡፡ ዳግማዊ ምኒልክ አምስት ሚሊዮን ሕዝብ መፍጀት ችለዋል ማለት፣ ከአቶሚክ ቦምብ እጅግ ብዙ የሚልቅ መግደያ ማሽን ነበራቸው ማለት ነው፡፡አለያም ከባድ መሬት መንቀጥቀጥን የሚያዝ መለኮታዊ ሀይል ነበራቸው ማለት ይሆናል
በመሠረቱ ሩስያዊው ወዶ ገብ ወታደር እዚህ ድምዳሜ ላይ የደረሰው ሳይንሳዊ የህዝብ ቆጠራ አድርጎ አልነበረም፡፡ የጣልያን ቄሳር መንግስት በአገራችን እስኪመሰረት ድረስ የነበረው የሕዝብ ቆጠራ፣ በግምት ላይ የተመሠረተ እንደነበር የታወቀ ነው፡፡ ከግምት ውጭ የነበረው የመረጃ ምንጭ የአስገባሪውን ሰራዊት አባል ስንት ጠላት እንደገደሉ በመጠየቅ የሚሰበሰብ ነበር፡፡ የዚህ አይነቱ መረጃ አሰባሰብ አስተማማኝ አልነበረም፡፡ ተጠያቂ ወታደሮች ለዝና እንዲመቻቸው ብዙ መግደላቸውን እያጋነኑ ስለሚናገሩ፣ የተጋነነ ድምር ማግኘት የማይቀር ነበር፡፡ ለምሳሌ በወላይታ ዘመቻ የተሳተፈው ፈረንሳዊው ጀብደኛ ቫንዳርሀይም በዚህ መንገድ ከወታደሮች በሰበሰበው መረጃ በጦርነቱ 96 ሺህ ሰው መሞቱን ገምቶ ነበር፡፡ወድያው ግን ይሄ ቁጥር ከተመለከተው እውነታ ጋር የማይጣጣም ሆኖ ስላገኘው፣ ቁጥሩን ወደ ሃያ ሺህ አካባቢ አውርዶታል፡፡
እርግጥ ነው፣ የቡላቶቪች አንቀጽ ፍሬ ሀሳብ በራሱ ስህተት ወይም ውሸት አልነበረም፡፡ በማስገበር ጦርነቱ ወቅት አያሌ ገባሮች አልቀዋል፡፡ይሁን እንጂ የእልቂቱ ዋና ሞተር በጊዜው የደረሰው የተፈጥሮ መቅሰፍት መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል፡፡ለዚህ ማስረጃ የሚሆኑ ሰነዶችን እንዳሳይ ይፈቀድልኝ፡፡
የኦሮሞ አገር ሀዋርያ ደ ሳልቪያክ ጦርነቱ የተካሄደበትን ክፉ ዘመን አስመልክቶ ሲጽፍ የሚከተለውን ይላል፡፡ ‹‹ሰማይ ራሱ የኦሮሞ ባላጋራ ሆኖ ነበር፡፡በረጅም ጊዜ ድርቅ ምክንያት የተከሰተ ርሀብ፣ፈንጣጣና የከብት በሽታ ነዋሪዎችን ወተትና ስጋ አሳጥቶ መከላከያቸውን አዳክሞት ነበር፡፡››
(The sky itself was against the Oromo, and conjured elements, famine caused by long drought ,small pox, epizootic disease which deprived the inhabitants of milk and meat all cut down their ranks to eye sight.)
ይሄው ጸሐፊ ወረድ ይልና የሚከተለውን ይጨምራል ‹‹የደቡብ አርሲዎች ከሰሜን ወንድሞቻቸው ጋር እምብዛም የጋራ አላማ አልነበራቸውም፡፡ ወረርሽኙ፣ በህዝቡ ላይ ያደረሰው ፍጅት ተባብሮ የመነሳትን እድል አምክኖታል፡፡››
But the Arsi of the south rarely have common cause with their brothers of the North.The epidemics swept the population and suffocated all start of powerful coalition.
ከላይ ሩሲያዊው ወታደር የጠቀሰው‹‹annihilation>>በጊዜው የከኒህ ክስተቶች ጋር ተጣጥሞ ሲታይ ትርጉም ይኖረዋል፡፡ በወቅቱ የደረሰው እልቂት በጦርነት ብቻ ሳይሆን፤ ፈረንሳዪ ጸሀፊ በመዘገበው ድርቅ፣ የእንስሳ በሽታ፣ ርሀብና የፈንጣጣ ወረርሽኝ አማካኝነት የተከሰተ መሆኑ ግልጽ የሆነልን ይመስለኛል፡፡ይህ ተፈጥሮአዊ መቅሰፍት አብዛኛውን የኢትዮጵያ ክፍል ጭምር ያደቀቀ እንጂ አርሲን ብቻ በልዩ መርጦ፣ ያጠቃት አልነበረም፡፡ለምሳሌ አንኮበር በዚህ ርሀብና ወረርሽኝ አብዛኛው ህዝብ እልቂት ስለደረሰበት ከተማዋ በአውሮፓዊው ጎብኝ ቫንዳርሀይም ‹‹የሞት ከተማ›› ተብላ እስከመጠራት ደርሳለች፡፡
አንዳንድ ሰዎች፣ ፈንጣጣን ወደ አርሲ ያመጣው ምኒልክ ነው ብለው ሳያፍሩ ጽፈዋል፡፡ይህ ውንጀላ በኩረጃ የተገኘ መሆኑን ለማሳየት ብዙ ምርምር አይጠይቅም፡፡ የአሜሪካን ታሪክ የሚያውቅ ሰው አቅኝ ነጮች ወደ አሜሪካ ሲመጡ፣ቀይ ህንዶችን ለማጥፋት ፈንጣጣ አስገቡ የሚል ታሪክ መስማቱ ወይም ማንበቡ የማይቀር ነው፡፡ለምሳሌ ኤች ሊንግል የተባሉ ታሪክ ጸሀፊ፡- ‹‹ህንዶች ከነጮች የተወሰነ የክርሰትና ገጽታዎችን፣ አልኮል መጠጥና አውዳሚና በካይ የሆነውን ፈንጣጣ ወስደዋል›› ማለት ነው፡፡
(From the white man the Indians quickly picked up…facets of Christianity, liquor and the lethal and infectious smallpox virus.)
ጥቂት ጸረ- ምኒልክ ምሁራን ይህንን ታሪክ በመኮረጅ በቀይ ህንድ ቦታ ኦሮሞን ፣ በነጭ ሰፋሪዎች ቦታ ደግሞ ምኒልክን ተክተው አቅርበውልናል፡፡
በመሰረቱ ፈንጣጣ ከምኒልክ በፊት በኦሮሞ ማህበረሰብ ዘንድ እንግዳ ስላልነበረ ምኒልክ አስገባው የሚለው ተቀባይነት ሊኖረው አይችልም፡፡ይህን ለማረጋገጥ የሚፈልግ ያባ ማስያስንና በዘመነ መሳፍንት ዘመን ኢትዮጵያን የጎበኘውን የፕላውደንን ማስታወሻዎች ማንበብ ይችላል፡፡

ዋቢ መጻሕፍት

- Harris W.C; The highlands of Ethiopia vol3
- Alexander Bulatovich; Ethiopia through Russion Eyes, trans by Richard Seltzer
- Martial de saliviac; the Ancient people Great African Nation; translated from French by Ayalew Kanno
- G.W,B Huntingford; The Oromo of Ethiopia, the Kingdoms of kafa and Janjero
- Martial de Salviac ,The Oromo
- H.L.Ingle ,American History
- M.Vanderheym,Une expédition avec le négous Ménélik; vingt mois en Abyssin
- Borelli J, Ethiopie Meridionale
No comments:
Post a Comment