በሚኒስትሯ የትዊተር ገጽ ላይ የሰፈረው መልዕክት አነጋጋሪ ሆኗል!
-መንግሥት አካውንታቸው ተጠልፏል እያለ ነው::
የሴቶች፣ የሕፃናትና የወጣቶች ጉዳይ ሚኒስትሯ ወይዘሮ ዘነቡ ታደሰ የካቲት 17 ቀን 2006 ዓ.ም. በትዊተር ማኅበራዊ ገጻቸው ላይ፣ ‹‹በተወዳጇ አፍሪካዬ ውስጥ ጥላቻና መገለል ቦታ የላቸውም፡፡
የአለባበስ
ሥርዓት ወይም የፀረ ግብረ ሰዶማዊ ሕጐችን ማውጣት የመንግሥታት ሥራ አይደለም፤›› በሚል የወጣው መልዕክት
አነጋጋሪ ሆኗል፡፡ መንግሥት ግን የሚኒስትሯ የትዊተር አካውንት መጠለፉን ገልጾ፣ ይህ መልዕክት የሚኒስትሯንም ሆነ
የመንግሥትን አቋም አይወክልም ሲል አስተባብሏል፡፡
በዚህ
ሳምንት መጀመሪያ ላይ በኡጋንዳ የፀደቀውን ፀረ ግብረ ሰዶማዊያን ሕግ በመቃወም በሚኒስትሯ የትዊተር ገጽ ላይ
የተጻፈው ይህ መልዕክት፣ በዓለም ዙሪያ ባሉ የግብረሰዶማዊ መብቶች አቀንቃኞች አድናቆት ተችሮታል፡፡ ሆኖም ግን
የሴቶች፣ የሕፃናትና የወጣቶች ጉዳይ ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሩ አቶ ዓብይ ኤፍሬም፣
‹‹መልዕክቱ በማይታወቁ ሰዎች የተጻፈ ሲሆን፣ የእሳቸውንም ሆነ የመንግሥትን አቋም የማይገልጽ ነው፤›› ብለዋል፡፡
አቶ
ዓብይ አክለው፣ ‹‹ሚኒስትሯ ይህን የማኅበረሰብ ሚዲያ የሚጠቀሙት ሕዝቡ በቀጥታ ሊያገኛቸው የሚገቡ መልዕክቶችን
ለማስተላለፍ አዋጭ ሚዲያ በመሆኑ ነው፤›› ብለዋል፡፡ የትዊተር ገጻቸውን የሚያንቀሳቅሱት ራሳቸው ወይዘሮ ዘነቡ
መሆናቸውን የገለጹት አቶ ዓብይ፣ በገጻቸው ላይ በጠላፊዎች በተላለፈው መልዕክት ሚኒስትሯ ማዘናቸውን
አስረድተዋል፡፡
የመንግሥት
ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ ሽመልስ ከማል የሚኒስትሯ የትዊተር አካውንት መጠለፉን
አረጋግጠው፣ ‹‹የሚኒስትሯን አካውንት ጠልፈው በመግባት የእሳቸውንና የመንግሥትን አቋም የማይገልጽ