
Oct 29, 2013
የስንፈተ ወሲብ አማራጭ ህክምናዊ መፍትሄዎች ለወንዶች (Reactive Dysfunction & Premature Ejaculation)
Geez Bet | Tuesday, October 29, 2013

ተሰባስበን በመጠጣት ላይ እያለን እንዳጋጣሚ አንዱ ጓደኛችን ቪያግራ ስለሚባለው
የስንፈተ ወሲብ መድኃኒት አነሳን፡፡ እሱ እንደነገረን ግን የስንፈተ ወሲብ ሳይሆን ለረጅም ጊዜ በሞቀ ስሜት
ለመቆየት የሚያስችል እና በቅርብ ጓደኛው ከዱባይ እንዳመጣለት ነገረን፡፡ የተወሰኑት በእረፍትና በድፍረት መሀከል
ሆነው እስኪ እንሞክረው ሲሉ ተስማሙ፡፡
እኔና አንዱ ጓደኛችን በድምፅ ተአቅቦ ዝም ብለን ማዳመጥ ቀጠልን፡፡ እርግጥ
አልፎ አልፎ ከባለቤቴ ጋር ወሲብ ለመፈፀም ስፈልግ ስሜቴ ስለማይነቃቃ ባለቤቴ ላይ መከፋት አያለሁ፡፡ እናም
እንዲህ አይነት ሁኔታ ሲፈጠር እንደጓደኞቼ ምን አለ ብጠቀም ብዬ አስባለሁ፡፡ ግን ግን ስጋቴ ከዛ በኋላስ ምን
ሁኔታ ውስጥ እገኛለሁ ብዬ ሳስብ ይጨንቀኛል፡፡ ታዲያ ለዚህ ብዬ ባለሙያዎችን ለማማከር ወደ ህክምና ብሄድ ቅብጠት
ይሆንብኛል ብዬ አስባለሁ፡፡...
Oct 29, 2013
ሠላይና ተሠላይ፤ ወዳጅና ጠላት
Geez Bet | Tuesday, October 29, 2013

አሜሪካዊ እንደራሴና የሥለላ ጉዳይ አዋቂ ፔተ ሆክስትራን የሚያስደንቀዉ ግን የአሜሪካ ሰላዮች የጀርመንዋ
መራሒተ-መንግሥትን ስልክን መጥለፋቸዉ አይደለም።የነፍሬድሪሽ ቁጣና ብስጭት እንጂ።ሆክስትራ እንደሚሉት
ካስደነቀ-የሚያስደንቀዉ የጀርመን
መሪ ሥልክ መጠለፉን ፍሬድሪሽ የሚመሩት የጀርመን የስለላ ድርጅት አለማወቁ ነዉ። ለካሳትሮ፥ ለብሬዥነቭ፥ ለማኦ፥ ለ ደጎል፥ ለንጎ በርግጥ አዲስ አልነበረም። አይደለምም።የኤንርኮ ፔና ኔቶ ኢሜል
መጠለፍ- ጉድ አሰኝቶ ነበር።የዲልማ ሮሴፍ-ኢሜል መጠለፍ-አስደንቆ ነበር።የሜርክል ሥልክ መጠለፍስ? ጉዱን ጉድ
ዘለቀዉ-እንበል ይሆን።የስላላዉ ቅሌት መነሻ፥ዳራዉ ማጣቃሻ፥ የፖለቲካዉ እድምታዉ መድረሻችን ነዉ-ላፍታ አብራችሁኝ
ቆዩ።
ሚዚያ ሃያ-አንድ 1943 (ዘመኑ በሙሉ እንደ ጎርጎሮሳዉያኑ አቆጣጠር ነዉ።) ፈረንሳይን ከናዚ ጀርመኖች አገዛዝ
ነፃ...
Oct 28, 2013
የሙሶሊኒና የቫቲካኑ ፖፕ ፓየስ 11ኛ ፋሺሽታዊ ሕብረት ሐቅ
Geez Bet | Monday, October 28, 2013

የቀድሞ አምባሳደር፤ ዘውዴ ረታ፤ ቫቲካንን ከኃላፊነት ነጻ ለማድረግ ስላደረጉት ሙከራ
ኪዳኔ ዓለማየሁ
መግቢያ፤
በቅርቡ፤ አምባሳደር ዘውዴ ረታ የደረሱት፤ “የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ መንግሥት” መጽሐፍ(1)፤ በሰሜን አሜሪካ፤ በልዩ ልዩ
ከተሞች እየተሸጠ በመሆኑ፤ አንድ ወዳጄ፤ ለኔም ልኮልኝ አንብቤዋለሁ። ይህን መጣጥፍ የማቀርበው ግን፤ ስለ መጽሓፉ
በአጠቃላይ ለመተቸት ሳይሆን፤ በተለይ ከገጽ 295 እስከ 314፤ “የቫቲካን አቋም በኢትዮጵያ ጉዳይ” በተሰኘው ምእራፍ፤
የቫቲካኑ ካሕን የፋሺሽቱን ጦር ሲባርኩ
የቀድሞ አምባሳደሩ፤ ፋሺሽት ኢጣልያ በኢትዮጵያ ላይ ለፈጸመችው ግፍና የጦር ወንጀል ሁሉ ቫቲካን ተጠያቂ አይደለችም
ያሉት፤ ከሐቅ የራቀ፤ የውድ ሐገራችንን፤ የኢትዮጵያን ክብርና ፍትሕ የሚያጓድል በመሆኑ፤ በማስረጃ የተደገፈ እውነት
ለማቅረብ ነው። በመጽሐፉ የቀረቡትን ጉድለቶች እራሳቸው...
Oct 28, 2013
Oct 26, 2013
የቅሪተ አፅም እድሜ እንዴት ይታወቃል?
Geez Bet | Saturday, October 26, 2013

የቅሪተ አፅም እድሜ መለክያዉ እንዴት ነዉ፤ ረጅም እድሜ እንዳለዉ የሚነገረዉ ቅሪተ አፅምስ መገኛ ቦታዉ እንዴት
ይታወቃል? ከመቶ ሽ በላይ እድሜ ያላቸዉን ቅሪተ አፅሞች እድሜ መለክያ ዘዴ እጅግ ቀላሉ ነዉ ያሉን ዶክተር ብርሃኔ
አስፋዉ ሉሲ «ድንቅነሽ» ስትገኝ ከነበሩ ተመራማሪዎች መካከል አንዱ ነበሩ።
በዓለም ዉስጥ እጅግ ግዙፍ እድሜ ካላቸዉ አስረ አንድ ቅሪተ አፅሞች መካከል ዘጠኙ ኢትዮጵያ ውስጥ መገኘታቸው
ይነገራል ። በምስራቅ ጎጃም ማችክል ወረዳ ነዋሪ የሆኑት አድማጫችን አቶ አማኑኤል ከተማ እባካችሁ፤ ግዙፍ እድሜ
እንዳላቸዉ የሚነገርላቸዉ ቅሪተ አፅሞች መገኛ ቦታ እንዴት ይታወቃል? የቅሪተ አፅሙ እድሜስ እንዴት ነዉ የሚለካዉ
ብለዉ የላኩልንን ጥያቄ ይዘን በዛሪዉ ዝግጅታችን መልስ የሚሰጡንን ባለሞያ ጋብዘናል።
አርዲ የሚል መጠርያን ያገኘችዉና በአዋሽ ሸለቆ...
Oct 26, 2013
የሜርክልን የእጅ ስልክ አሜሪካ ጠለፈች!
Geez Bet | Saturday, October 26, 2013

የጀርመን መራሂተ-መንግስት አንጌላ ሜርክል የእጅ ስልክ በዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት የስለላ ተቋም ተጠልፏል የሚለዉ
ዜና እያነጋገረ ነዉ። ዩናይትድ ስቴትስ ድርጊቱን እንዳልፈፀመች በመጥቀስ አስተባብላለች። ጉዳዩ በአውሮጳ መሪዎች
ዘንድ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶታል።
ጀርመን የመራሂተ መንግስቷ ስልክ ሳይሰለል አይቀርም በሚል በበርሊን የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደርን
ዛሬ ለማነጋገር መጥራቷ ተዘገበ። የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጊዶ ቬስተርቬለ በጀርመን ለአሜሪካኑ አምባሳደር ጆን
ኤመርሰን በዚህ ረገድ የጀርመንን ግልጽ አቋም እንደሚያቀርቡም ተገልጿል። የጀርመን መገናኛ ብዙሃን የአሜሪካን
የስለላ ተቋም NSA የመራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክልን የእጅ ስልክ ሳይጠለፍ አልቀረም የሚል መረጃ ይፋ
አድርገዋል። ዋሽንግተን ግን አስተባብላለች። ይህ ከተሰማ በኋላም ሜርክል ራሳቸዉ ለፕሬዝደንት...
Oct 22, 2013
ፀረ ዘመናዊ ባርነት ትግል
Geez Bet | Tuesday, October 22, 2013

በዓለም ላይ ሰላሳ ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች በዘመናዊ ባርነት እንደሚማቅቁ ባርነትን ለማጥፋት የሚታገል አንድ ዓለም አቀፍ ተቋም ባለፈው ሳምንት አስታውቆል።
« ዎክ ፍሪ ፋውንዴሽን» የተባለው ይኼው አዲስ ተቋም በርካታ መረጃዎችን አሰባስቧል። አላማው ዘመናዊውን ባርነት በተቻለ ፍጥነት ማስቀረት ነው።
ሊዊዘ የ 14 ዓመት ልጅ ነበረች ቀጣሪዋ የወሲብ ጥቃት ሲያሰርስባት እና ሲደበድባት። ይህም አልበቃ
ብሎ አፍሪቃ የሚኖሩት ዘመዶቿ እንደተገደሉ ትሰማለች። ቀጣሪዋም ገዳዮቹን የላከው እሱ እንደሆነ ይነግራታል። ወጣቷ
ከአንድ አመት በፊት ከምትኖርበት መንደር ወደ ጀርመን ስትመጣ ቀጣሪዋ ትምህርት ቤት እንደምትሄድ ነበር ቃል
የገባላት፣እዚህ ስትመጣ ግን የጠበቃት ሌላ ነው። አማራጭ ያጣችው ወጣት ወደ ሴተኛ አዳሪነት ስራ ትገባለች።«
ለሶስት አመት ያህል ደሙ አላቆመልኝም።»...
Oct 22, 2013
የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ይዞታ
Geez Bet | Tuesday, October 22, 2013

ዓለም ዓቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሚዋጋች ድርጅት ሂዩማን ራይትስ ዎች ባለፈው ዓርብ በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ይዞታ
ላይ ያተኮረ በተለይም አዲስ ኣበባ በሚገኘው እና ማዕከላዊ ተብሎ በሚታወቀው የፌደራሉ የምርመራ ማዕከል በእስረኞች
ላይ ይፈጸማሉ ባላቸው ሰብዓዊ ሰቆቃዎች ላይ ያነጣጠረ አዲስ ሪፓርት ይፋ ኣድርገዋል።
ሰብዓዊ መብት ሲባል በነገስታት መልካም ፈቃድ የሚቸሩ ወይንም መንግስታት ከሚመሩባቸው ህግጋተ መንግስታት የሚመነጩ
ብቻ ሳይሆኑ በ ተ መ ድ የሰብዓዊ መብቶች ድንጋጌዎች መሰረት ሰዎች ሰው በመሆናቸው ብቻ በተፈጥሮ የተቀዳጁኣቸው
መሰረታዊ የሰው ልጅ መብቶች ናቸው። በእነዚህ ህጎች መሰረት ደግሞ እንደ መኖ ኣልባሳት እና መጠለያ የመሳሰሉ የሰው
ልጅ መሰረታዊ ፍላጎቶችን ጨምሮ ዜጎች እንደ ህክምና እና ትምህርት የመሳሰሉ ማህበራዊ ፍላጎቶችን ሁሉ የማግኘት
መብት ኣላቸው።
እናም...
Oct 17, 2013
በውኃ ላይ የታነፀው ይምርሐነ ክርስቶስ የ“ወርልድ ሞኑመንትስ ፈንድ የ2014 ተመራጭ መካነ ቅርስ” ሆነ
Geez Bet | Thursday, October 17, 2013

ከዛጒዌ ስመ ጥር ነገሥታት አንዱ በነበሩት በንጉሥ ይምርሐነ ክርስቶስ ዘመነ መንግሥት ከተሠሩት ኪነ ሕንጻዎች አንዱ
የኾነው ይምርሐነ ክርስቶስ፤ የወርልድ ሞኑመንትስ ፈንድ የ2014 ተተኳሪ መካነ ቅርስ (2014 World
Monuments Watch) ሆኖ ተመረጠ፡፡ፈንዱ መስከረም 28 ቀን 2006 ዓ.ም. ዋና ጽ/ቤቱ በሚገኝበት
በኒው ዮርክ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቀው÷ እ.አ.አ በ2014 ዓለም በትኩረት ሊያውቃቸው፣ ሊጠብቃቸውና
ለትውልድ ሊያስተላለፍላቸው ይገባል ካላቸው የ41 አገሮች ባህላዊና ታሪካዊ ቅርሶች መካከል ልዩ የኪነ ሕንጻ ጥበብ
የሚታይበት የይምርሐነ ክርስቶስ መካነ ቅርስ አንዱ ኾኖ መመረጡ ተገልጧል፡፡“ወርልድ ሞኑመንትስ ዎች”
በተሰኘው ፕሮግራሙ ለአደጋ የተጋለጡና ዝነኛ የቱሪስት መስሕብ የኾኑ ታሪካዊ ኪነ ሕንፃዎችንና...
Oct 17, 2013
አፍሪቃ እና የአደንዛዥ እፅ ዝዉዉር
Geez Bet | Thursday, October 17, 2013

ዚምባቡዌ ላይ የአደንዛዥ እፅ ዝዉዉርና አጠቃቀምን አስመልክቶ የሚካሄደዉ ጉባኤ፤ መሪዎቹ ወሳኝ ርምጃ ካልወሰዱ
የአህጉሩን መረጋጋት ሊጎዳ እንደሚችል አመለከተ። የምዕራብ አፍሪቃ የኤኮኖሚ ማኅበረሰብና በተመድ የእፅ ተከታታይ
ጽ/ቤት አፍሪቃ ዉስጥ ሕገ ወጥ የአደንዛዥ እፅ ዝዉዉርን ለመግታት የሚያስችል አዲስ ርምጃ ላይ እየመከሩ ነዉ።
የአፍሪቃ ኅብረት የማኅበራዊ ጉዳይ ኃላፊ ዶክተር ኦላዋሌ ማየጉን እንደሚሉት አፍሪቃ በአህጉር ደረጃ የHIV ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት ባደረገችዉ ጥረት ዉጤት እንዳስመዘገበች ሁሉ፤ ቀጣይ ዘመቻዋን ሕገ ወጥ የአደንዛዥ እፅ ዝዉዉርንና አጠቃቀምን መግታት መሆን ይኖርበታል፤
«የበሽታዉ ስርጭት በአዲስ መልክ ይነሳል የሚል ፍራት ከኖረ ሊሆን የሚችለዉ የአደንዛዥ እፅ
ተጠቃሚዎችን በመርፌ በመዉጋት ነዉ የሚሆነዉ።...
Oct 17, 2013
የምግብ እጥረትና ብክነት
Geez Bet | Thursday, October 17, 2013

ዓለም የምግብ እና የእርሻ ድርጅት በዓለማችን ከስምንት መቶ ሚሊዮን በላይ ሕዝብ
እየተራበ የሚታየዉ የምግብ ብክነት ተቀባይነት እንደሌለዉ አመለከተ። ድርጅቱ ዛሬ ይፋ ባደረገዉ ዘገባዉ የምግብ
ማጣት ብቻ ሳይሆን የተመጣጠነና በቂ ምግብ አለማግኘት አካላዊ እድገታቸዉ ለእድሜያቸዉ የማይመጥን ልጆች ቁጥርም
165 ሚሊዮን መድረሱንም አስታዉቋል።
ኢትዮጵያ ዉስጥ ያለፈዉ ዓመት የመኸር ዝናብ መጠንና ስርጭት የተሻለ ምርት እንደሚገኝ ተስፋ አሳድሯል። የምግብ ርዳታ የሚጠብቀዉም ሶስት ሚሊዮን አይሞላም።
በዓለማችን በአንድ ወገን የተትረፈረፈ ምግብ እየተመረተ ለብክነት ሲዳረግ በሌላዉ በኩል ደግሞ የዕለት
ጉርስ የሚሻዉ ወገን በረሃብ አንጀቱ መታጠፉ አግባብነት የለዉም ይላል የዓለም የምግብና የእርሻ ድርጅት ማለትም
FAO። እንድርጅቱ ዘገባ ከሆነም በየዓመቱ በዓለም ከሚመረተዉ...
Oct 17, 2013
የአፍሪቃ መሪዎች እና ICC
Geez Bet | Thursday, October 17, 2013

በዘር ማጥፋት፥በሰብአዊ ፍጡር ላይ በተፈፀመ ወንጀል እና በጦር ወንጀል የሚጠረጠሩ ፖለቲከኞችን እንዲመረርምር፥
በተረጋገጠባቸዉ ላይ እንዲፈርድ የተቋቋመዉ ዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት ግን እስካሁን ክስ የመሠረተዉ በስምት የወንጀል
ጭብጦች ነዉ።በስምንቱም ጉዳዮች የከሰሳቸዉ፥ ወይም የፈረደባቸዉ ፖለቲከኞች በሙሉ ግን አፍሪቃዉያን ናቸዉ።
በ1919 (ዘመኑ በሙሉ እንደ ጎርጎሮሳዉያን አቆጣጠር ነዉ) የጦር ወንጀለኞችን የሚቀጣ ዓለም አቀፍ
ፍርድ ቤት እንዲቋቋም ሐሳቡ ሲነሳ፣ ሲወድቅ፣ በ1948 ዳግም ሲነሳ፣ ደንቡ ሲረቀቅ፣ ረቂቁ ሲወድቅም አብዛኞቹ
አፍሪቃዉያን ከአዉሮጳ ቅኝ ገዢዎች ነፃ ለመዉጣት ገና እየገደሉ ይሞቱ ነበር።1975 በደራዉ ክርክር ዉስጥም
አፍሪቃዉያን አልነበሩበትም።በ1998 የመመሥረቻ ዉሉን ለመፈረም፣ በ2002 ለማፅደቅ ግን አፍሪቃ ይንጋጋ
ገባ።ለፍርድ ቤቱ በርካታ...
Oct 8, 2013
ግብጻውያን ምሁራን የህዳሴ ግድብ ግንባታ ለግብጽ የውሃ ዋስታና አደጋ ነው አሉ
Geez Bet | Tuesday, October 08, 2013

ዋሽንግተን ዲሲ — The Group of the Nile Basin”
የተባለው ቡድን ያቀረበው የጥናት ዘገባ የግብጽን የውሀ አቅርቦት በማረጋገጥ ጉዳይ ላይ ያልታሰቡ ተከታታይ የውጭ
ተግዳሮቶች ተደቅነዋል ይላል። የእነዚህ ተግዳሮቶች ምንጮች የኢትዮጵያ መንግስት በብሉ ናየል ወንዝ ላይ አራት
ግድቦች ለመገንባት ማቀዱ ነው።
ዋናው አደጋ ግን የኢትዮጵያ መንግስት የግርጌ ተፋሰስ ሀገሮች የሆኑትን ግብጽንና ሱዳንን ሳያማክር የታላቁ የህዳሴ
ግድብ ግንባታ መጀመሩን የሚያመለክተው የአባይ ወንዝ ውሀ የፍሰት አቅጣጫ መቀየሩን ማስታወቁ ነው ይላል ዘገባው።
ይህ ተግባርም በአብዛኞቹ ግብጻውያን አመለካከት በመላ መሰረታዊ ህጎችና በአለም አቀፍ ህጎች ላይ በግላጭ የተከፈተ
ጥቃት ነው ይላል የጥናት ጽሁፉ።
የጥናቱ ጽሁፍ ኢትዮጵያ ከግብጽና ከሱዳን ጋር የድርድር ስምምነት ላይ...
Oct 8, 2013
የዩኤስ አሜሪካ የአፍሪቃው ቀንድ የውጭ ፖሊሲ
Geez Bet | Tuesday, October 08, 2013

በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር መስሪያ ቤት ስራ ከጀመሩ ሁለት ወራት ያስቆጠሩት ምክትል ሚንስትሯ ሊንዳ
ቶማስ ግሪንፊልድ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ መንግሥታቸው በአፍሪቃ በተለይም በቀፍሪቃ ቀንድን የሚከተለውን የውጭ
ጉዳይ ፖሊሲ አብራርተዋል።
በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር መስሪያ ቤት ስራ ከጀመሩ ሁለት ወራት ያስቆጠሩት ምክትል
ሚንስትሯ ሊንዳ ቶማስ ግሪንፊልድ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ መንግሥታቸው በአፍሪቃ በተለይም በቀፍሪቃ ቀንድን
የሚከተለውን የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ አብራርተዋል።
በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚንሥትር የአፍሪቃ ጉዳዮች ምክትል ሚንስትር ሊንዳ ቶማስ ግሪንፊልድ
መንግስታቸው በአፍሪቃ ቀንድ የሚከተለውን የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ በተመለከተ ትናንት ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል።...
Oct 5, 2013
የተዘጋው የአሜሪካ መንግስትና የአሜሪካ ምስቅልቅል
Geez Bet | Saturday, October 05, 2013

ከ3 ሚሊዮን በላይ ሰራተኞች ክፍያቸውን አያገኙም800 ሺህ ሰራተኞች ያለ ምንም ካሳ ከስራ ይሰናበታሉየአገልግሎት፣ የቱሪዝም፣ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ክፉኛ ይጎዳሉየሩብ አመቱ ጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት በ0.3 በመቶ ሊቀንስ ይችላል
ባለፈው ማክሰኞ ማለዳ በይፋ የተዘጋው
የአሜሪካ መንግስት፣ መቼ እንደሚከፈት እርግጡን መናገር እንደማይቻልና የአገሪቱ ኮንግረስ የዕለት ተዕለት
እንቅስቃሴዎችን ማካሄጃ ገንዘብ የሚገኝበትን መላ ፈልጎ እስኪያገኝና የጋራ መግባባት ላይ እስኪደርስ ድረስ፣
መንግስት እንደተዘጋ መቆየቱ ግድ እንደሚሆን የዋሽንግተን ፖስቱ ዘጋቢ ብራድ ፕላመር ይናገራል፡፡ የአገሪቱ
መንግስት መዘጋቱ በይፋ ከተገለጸበት ቅጽበት አንስቶ ጉዳዩ አለምአቀፍ መነጋገሪያ ሆኗል። የመንግስት መዘጋት
በዜጎችና...
Oct 5, 2013
“ሲኖዶሱ ስለመስቀሉ
Geez Bet | Saturday, October 05, 2013

መግለጫ እስኪሰጥ ህዝቡ በትዕግስት ይጠባበቅ”ስለመስቀሉ ከሰማይ መውረድ በጀመሪያ መረጃው እንዴት ነው የደረሳችሁ?መስቀሉ
ከሰማይ ወረደ ስለሚባለው የሻለ መረጃ የምታገኙት ወረደ ከተባለበት ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪዎችና አገልጋዮች ነው።
እኛ ከሰማይ ወረደ ከተባለ ከቀናት በኋላ ነው በስፍራው የተገኘነው፡፡ ስለዚህ እነሱ እንደነገሩን እንጂ አይተናል
ሰምተናል ብለን አይደለም መረጃ የምንሰጣችሁ፡፡ እነሱ ግን እንዴት እንደወረደ አይተናል ስላሉ መረጃውን
ከእነሱ ነው ያገኘነው፡፡ ከእነሱ የተነገረን...
Oct 5, 2013
ከ3ሺህ በላይ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የኢንጂነሪንግ ተማሪዎች ከግቢ ተባረሩ
Geez Bet | Saturday, October 05, 2013
በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የአራተኛ አመትና የሁሉም የምህንድስና ዘርፍ ተማሪዎች ከትላንት በስቲያ ከግቢ መባረራቸውን
የአዲስ አድማስ ምንጮች ገለፁ፡፡ ለተማሪዎቹና ለዩኒቨርሲቲው ግጭት ምክንያት የሆነው የብቃት ማረጋገጫ ፈተና
እንደሆነም ምንጮቹ ጠቅሰዋል፡፡ የሁሉም የምህንድስና ተማሪዎች አራተኛ አመት ላይ ሲደርሱ የብቃት ምዘና ፈተና
ይወስዳሉ ያሉት ምንጮቹ፣ የዘንድሮው ተማሪዎች ግን ለእረፍት ወደየቤታቸው ሲሄዱ ሞጁል ይዘው ሄደው አጥንተው
መፈተን ሲገባቸው፣ ድንገት ተፈተኑ መባላቸው እንዳስደነገጣቸው ገልፀዋል፡፡...
Oct 2, 2013
ኢትዮጵያን ያየሁበት ዓይን
Geez Bet | Wednesday, October 02, 2013

ያን ፊሊፕ ቫይል ተወልዶ ያደገው በክሬፌልድ ከተማ ጀርመን ሀገር ሲሆን ጀርመናዊው ወጣት ገና የ14 ዓመት ልጅ ሳለ
ነው ከጓደኛው ጋ በመሆን ለኢትዮጵያ ገንዘብ ማሰባሰብ የጀመረው። ይሄው ወጣት በአሁኑ ሰዓት «ኤምራ እና ዳቦ»
የሚል ፊልም ኢትዮጵያ ውስጥ በመቅረፅ ላይ ይገኛል።
« 8ኛ ክፍል ነበርን ያኔ። በዕረፍት ሰዓት ያለማቋረጥ ቋሊማ እና ከስንዴ እና እንቁላል የተሰራ ጣፋጭ
ቂጣ( ዋፍል) እንሸጥ ነበር። ከዛም በተጨማሪ ክሪፌልድ በሚገኙ የምሽት ክበቦች የተለያዩ የአፍሪቃ ድግሶች
እናዘጋጅ እና ገንዘብ እናሰባስብ ጀመር። ከዛም 11ኛ ክፍል ስንደርስ ባንድ ጊዜ ያሰባሰብነው ገንዘብ 20 000
ዩሮ ደረሰልን።» ይህንንም ገንዘብ ያሰባሰቡት ካርል ሀይንስ በኧም ለመሰረቱት «ሰዎች ለሰዎች» ለተሰኘው ድርጅት
ነው። ያን እና ጓደኛው ለ ድርጅት ብዙ ገንዘብ ስላሰባሰቡም...
Oct 2, 2013
ግብጽ-ጋዜጠኞች ላይ የሚደረግ አፈና
Geez Bet | Wednesday, October 02, 2013

በጎ አ 2011 ዓ,ም በግብፅ የተቀጣጠለ አብዮት፤ ዋና ዓላማ በሲቢሉ ላይ የሚደረገዉን ወታደራዊ እርምጃ ለማስቆም
ነበር። ነገር ግን ከሁለት ዓመት ከመንፈቅ በኋላ ዛሪም፤ ወታደሩ በሲቢሉ ላይ የሚያካሂደዉ የሃይል እርምጃ
እንደቀጠለ ነዉ። የሰላ ብዕር የያዙ ጋዜጠኞችም፤ ሥራቸዉን እንዳይሰሩ ይታፈናሉ።
የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች፤ በበኩላቸዉ እንዲህ አይነቱን አካሄድ ለማስቀረት፤ በሀገሪቱ አዲስ ሕገ-መንግስት ላይ
በማፅደቅ ለማስቀረት ይፈልጋሉ። ካይሮ ከተማ ስትወሳ፤ ጉጉት እና ጥሩ የመረጃ ትስስር ያለባት፤ እና የሁሉ ነገር
መጀመርያ ተደርጋ ትታሰባለች።
በራሃማዋ የሲናይ ደሴት ሰዎችን ስለማዘዋወር ወንጀል በፃፈዉ ዘገባዉ ባለፈዉ ዓመት «ሳሚር ካዚር»
የተሰኘዉን የግብፅ ሽልማት ያገኘዉ የ38 ዓመቱ ግብጻዊ ጋዜጠኛ የአህመድ አቡ ዴራ፤ የሥራ ባልደረቦች፤ የሙገሳ...
Oct 2, 2013
በኢጣሊያ የጀልባ ስደተኞች እጣ
Geez Bet | Wednesday, October 02, 2013

13 ያህል ስደተኞች በጀልባ ወደ ኢጣሊያ- ሲሲሊ የባህር ዳርቻ በዋና ለመድረስ ሲሞክሩ ሰምጠዉ መሞታቸዉ ተሰምቷል።
ከጀልባ ወርደው በዋና ለመሰወር ሲሞክሩ ነው። የተባበሩት መንግሥትት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን በምህፃሩ
ዩኤንኤችሲአር እንዳስታወቀው በኢጣሊያ በኩል የሚገቡ ስደተኞች ቁጥር ካለፈው ዓመት ጋ ሲነፃፀር በ3 እጥፍ ጨምሯል።
ባለፈው ረቡዕ ነበር ከ700 በላይ ተገን ጠያቂ ስደተኖችን ያሳፈሩ ሶስትጀልባዎች ደቡብ ኢጣሊያ ሲሺሊ ግዛት የባህር
ዳርቻ ገብተው የተገኙትየኢጣሊያ ጠረፍ ጠባቂ ዘበኖች ለኣጃንስ ፍራንስ የዜና ኣገልግሎት እንደደገለጹት ሁለቱ
የመጡት በላምፔዱሳ ደሴት በኩል ነው በኢጣሊያ ደቡባዊ ጫፍ የምትገነው የላምፔዱስ ደሴት የማንነት ማረጋገጫያልያዙ
በርካታ ስደተኖች ወደ ኣውሮፓ የሚሸጋገሩባት ዋንና በር መሆንዋ ይነገርላታል ከስደተኖቹ መካከልም ገሚሶቹ...