Time in Ethiopia: 03:26:40 Sunday, April 13, 2025

Apr 30, 2014

የታሰሩት ጋዜጠኞችና ጦማርያን ጉዳይ እያነጋገረ ነው

Geez Bet | Wednesday, April 30, 2014
-ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች በነፃ እንዲለቀቁ እየጠየቁ ነው:: -መንግሥት አደገኛ ወንጀል ፈጽመዋል እያለ ነው:: የመብት ተሟጋቾች ነን ከሚሉ የውጭ ድርጅቶች ጋር በገንዘብና በሐሳብ በመስማማት፣ ሕዝብን ለአመፅ ለማነሳሳትና ለማተራመስ በኢንተርኔትና በተለያዩ ማኅበራዊ ድረ ገጾች ላይ ቀስቃሽ መጣጥፎችን ለማሰራጨት ሲዘጋጁ ተደርሶባቸዋል በሚል፣ በወንጀል ተጠርጥረው የታሰሩ ጋዜጠኞችና ጦማርያን (Bloggers) ጉዳይ እያነጋገረ ነው፡፡ ሚያዝያ 25 እና 26 ቀን 2006 ዓ.ም. በፀጥታ ኃይሎች ቁጥጥር ሥር ከዋሉ በኋላ በ48 ሰዓታት ውስጥ በዕለተ እሑድ ሚያዝያ 19 ቀን 2006 ዓ.ም. በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ አንደኛ ወንጀል ችሎት በቀረቡበት ወቅት፣ የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ማዕከል (ማዕከላዊ) መርማሪ ፖሊስ፣  ተጠርጣሪዎቹ...
ሙሉውን አንብብ-Read More

Apr 28, 2014

ብቸኛው ሰው (ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም)

Geez Bet | Monday, April 28, 2014
 ጸሓፊ፡-አፈንዲ ሙተቂ:- ፕሮፌሰር መስፍንን በአካል ያየሁት ሁለት ጊዜ ያህል ብቻ ነው፡፡ በነዚህም ጊዜያት ከመጨባበጥ በቀር ሌላ ነገር ማውጋት አልቻልንም፡፡ ብንጨዋወት እንኳ በፖለቲካ አመለካከታችን የምንግባባ አይመስለኝም፡፡ ለምሳሌ እሳቸው “ኢትዮጵያ ውስጥ ነገዶችና ጎሳዎች እንጂ ብሄሮችና ብሄረሰቦች የሉም፤ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው አንድ ብሄር ብቻ ነው” ነው የሚሉት፡፡ እኔ ግን “በኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ ብሄሮችና ብሄረሰቦች አሉ፤ ነገድና ጎሳ የብሄር ቅርንጫፎች እንጂ ራሳቸውን የቻሉ ህዝቦች አይደሉም” ነው የምለው፡፡ በሌላ በኩል ፕሮፌሰር መስፍን “የብሄረሰቦችን መብት ለማስከበር በብሄር መደራጀቱ ለሀገር አንድነት አደጋ አለው” የሚል እምነት አላቸው፡፡ እኔ ግን “ለመጥፎ ዓላማ እስካልሆነ ድረስ በብሄር መደራጀቱ መጥፎ አይደለም” የሚል እምነት አለኝ፡፡...
ሙሉውን አንብብ-Read More

Apr 28, 2014

የክርስቲያንና የሙስሊም ፍቅር በገለምሶ

Geez Bet | Monday, April 28, 2014
ጸሓፊ፡-አፈንዲ ሙተቂ:-  ከጥቂት ሳምንታት በፊት ስለገለምሶው መምሬ ሙላቱ የምትተርክ አንዲት ጽሑፍ ለጥፌ ነበር፡፡ አሁን ሳስበው ግን ያቺ ጽሁፍ መሀል መንገድ ላይ ተቆርጣ የቀረች ሆና እየታየችኝ ነው፡፡ ስለዚህ ለናንተም፤ ለወገንም፣ ለታሪክ ጸሓፊያንም እንዲጠቅም ይህችኛዋን ሐተታ እጨምርበት ዘንድ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡   በ1981 የስድስተኛ ክፍል ተማሪ እያለሁ ይመስለኛል፡፡ ከትምህርት ቤት መልስ የጨዋታ ጓዶቼን ፍለጋ “ኒብራ” ከተሰኘው የገለምሶ ከተማ ዋነኛ ጎዳና ወረድኩ፡፡ ጓዶቼን ብዙም ርቀት ሳልሄድ ከትልቁ የጋሽ መሐመድ በከር መደብር በረንዳ ላይ አገኘኋቸው፡፡ እዚያም የኳስ ጨዋታ ሰዓታችን እስኪደርስ ድረስ በትረባና በፉገራ መናቆር ጀመርንና አንዱ ሌላውን ለማብሸቅ ይሞካክር ገባ (በጊዜው ትረባ፣ ፉገራና ለከፋ ጊዜያችንን የሚገፋልን ትልቅ...
ሙሉውን አንብብ-Read More

Apr 23, 2014

በምስራቅ ወለጋ ዜጎች እየተፈናቀሉ ነው

Geez Bet | Wednesday, April 23, 2014
በምስራቅ ወለጋ ስቡ ስሪ ወረዳ ‹‹ይህ አገር የእናንተ አይደለም፡፡ አገራችሁን ግቡ፡፡›› በሚል 200 ያህል አርሶ አደሮች እንደተፈናቀሉ አስታወቁ፡፡ በ1990ዓ.ም ጀምረው በአካባቢው የኖሩት እነዚህ ዜጎች ‹‹የመኖሪያ መታወቂያ ተሰጥቶን፣ ውጡ ምሬታቸውን ለዝግጅት ክፍላችን ገልጸዋል፡፡ አርሶ አደሮቹ ከዚህ ቀደም በ1992 በተመሳሳይ ቤትና ንብረታቸው ወድሞ ተፈናቅለው የነበረ ቢሆንም መንግስት እንደገና እንዳቋቋማቸው ይገልጻሉ፡፡ ‹‹በአንድ በኩል አገራችሁ አይደለም ውጡ!›› የሚሉት የአካባቢው ባለስልጣናት በሌላ በኩል ደግሞ ‹አካባቢውን ልንሰራበትና ልናሰራበት ነው ይሉናል፡፡ በ1992ም መንግስት እንደገና አቋቁሞናል፡፡ አሁንም ቦታው ከተፈለገ መንግስት ተገቢውን ካሳ ሊሰጠን ይገባል፡፡› ብለን ስንጠይቅ ደግሞ ‹እናንተን መንግስት አያውቃችሁም፡፡ በምስራቅ ወለጋ ዜጎች እየተፈናቀሉ...
ሙሉውን አንብብ-Read More

Apr 23, 2014

አርሶ አደሮች መሬታቸውን ያለካሳ እየተነጠቁ ነው

Geez Bet | Wednesday, April 23, 2014
መራዊ፡- በምዕራብ ጎጃም ዞን ሜጫ ወረዳ ያለ ፈቃዳችን መሬታቸውን አሳልፈን አንሰጥም ያሉ አርሶ አደሮች እስርና ድብደባ እየደረሰባቸው መሆኑን ከአካባቢው የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡ በመራዊ አካባቢ ሜጫ ወረዳ እናሸንፋለን ቀበሌ መንግስት የከርሰ ምድር ውሃ ቁፋሮ እናካሂዳለን በሚል ከ400 በላይ የሚሆኑ አርሶ አደሮች ከመሬታቸው እንዲለቁ የተደረገውን እርምጃ አርሶ አደሮቹ በመቃወማቸው እስርና ድብደባ እየደረሰባቸው መሆኑን የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ በአካባቢው ከአሁን ቀደም ተመሳሳይ እርምጃዎች የተወሰዱ ሲሆን የአርሶ አደሮቹ መሬት በአበባ ኢንቨስትመንት ላይ ለተሰማሩ ባለሀብቶች ተሰጥቶባቸዋል፡፡           ይህም በአሁኑ ወቅት መንግስት ውሃ ለመቆፈር በሚል አርሶ አደሮቹ ከመሬታቸው እንዲለቁ የሚወስደው እርምጃ በተመሳሳይ ...
ሙሉውን አንብብ-Read More

Apr 16, 2014

አርሶ አደሮች የመሬት ይዞታ ደብተራቸውን ተቀሙ

Geez Bet | Wednesday, April 16, 2014
•‹‹እቃችንን ሽጠን ፈቃዳችን እንመልሳለን›› ነጋዴዎች::  ደብረ ማርቆስ፡- በምስራቅ ጎጃም ዞን ከአምስት በላይ ወረዳዎች ውስጥ መንግስት የአርሶ አደሮችን የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር እየሰበሰበ መሆኑ ተሰማ፡፡ በምስራቅ ጎጃም ዞን ጎዛምን፣ ባሶ ሊበን፣ አንደድና ሌሎችም ወረዳዎች የመሬት አስተዳደርና የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ሰራተኞች መሬቱን እንደገና ለማጥናት እንዲሁም የግልና የመንግስት ይዞታን ለመለየት በሚል የይዞታ ማረጋገጫ ደብተሮችን እየሰበሰቡ መሆኑን ከአካባቢው የደረሰን መረጃ ያስረዳል፡፡ ምንም እንኳ የይዞታ ደብተሩን ሰብሳቢዎቹ በይፋ ለጥናት እንዲሁም የመንግስትና የግል ይዞታን ለመለየት ነው ቢሉም ካድሬዎች ‹‹ኢህአዴግን ካልመረጣችሁ መሬታችሁን እንነጥቃችኋለን፡፡ መሬት የምንሰጠው እኛን ለመረጠ ብቻ ነው፡፡›› በሚል እያስፈራሯቸው እንደሆነ አርሶ አደሮቹ...
ሙሉውን አንብብ-Read More

Apr 16, 2014

በቤንሻንጉል አሁንም ዜጎችን ማፈናቀሉ ቀጥሏል!

Geez Bet | Wednesday, April 16, 2014
• ‹‹አማራ ክልል አያገባኝም ብሏል››::  በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት የሚኖሩ የአማራ ብሔር ተወላጆች ለዓመታት ከኖሩበት ቦታ እየተፈናቀሉ መሆኑን ተፈናቃዮች አስታወቁ፡፡ ባለፈው ዓመት ቁጥራቸው በርካታ የሆኑ የአማራ ብሔር ተወላጆች ከክልሉ መፈናቀላቸው የሚታወስ ሲሆን ከሰሞኑ ደግሞ ማፈናቀሉ በአዲስ መልክ የቀጠለ መሆኑ ተመልክቷል፡፡ ተፈናቃዮቹ በክልሉ ድባጤ ወረዳ አልባሳ ቀበሌ ነዋሪዎች ሲሆኑ ከ250 ሰዎች በላይ ከአካባቢው ውጡ ተብለዋል፡፡ ‹‹በአካባቢው ሰፈራ እየተሰጠ ነው፡፡ የተባረሩት ሰዎች ግን 15ና 20 አመት በአካባቢው ኖረዋል፡፡ ቤትና ንብረትም አላቸው፡፡ ከጥቅምትና ታህሳስ ጀምሮ ግን ‹እናንተ በአካባቢው መኖር አትችሉም› ተብለው መስፈር የለባችሁም ተብለዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት እኒህ ሰዎች ዛፍ ስር ነው የሚኖሩት፡፡›› ሲሉ ስለ ሁኔታው ለዝግጅት...
ሙሉውን አንብብ-Read More

Apr 16, 2014

Gunmen kill nine in western Ethiopia bus attack: state media

Geez Bet | Wednesday, April 16, 2014
ADDIS ABABA (Reuters) - Gunmen ambushed a bus carrying dozens of people in western Ethiopia near the Sudanese border, killing nine and wounding six others, state-run media said on Wednesday. There was no claim of responsibility and no group was blamed for the attack, but Ethiopia says it has thwarted several plots in recent years by Ethiopian insurgents as well as Somali al Qaeda-linked al Shabaab Islamist militants. A handful of rebel groups are waging low-level separatist insurgencies in...
ሙሉውን አንብብ-Read More

Apr 15, 2014

በሱሉልታ ከተማ የአማራ ተወላጆች ናችሁ የተባሉ ተደበደቡ

Geez Bet | Tuesday, April 15, 2014
ሶስት ሰዎች ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸው በአዲስ አበባ የተለያዩ ሆስፒታሎች ገብተዋል:: “ረብሻውን ያነሱት ህዝብን የማይወክሉ ወሮበሎች ናቸው”      የከተማው ኮሙዩኒኬሽን):-“ባህርዳር በተካሄደው የስፖርት ውድድር ላይ የኦሮሞ ተወላጆች ላይ አድልዎ ተፈጽሟል” በማለት የተቧደኑ ወጣቶች፣ ባለፈው ሐሙስ የሱሉልታ ከተማ ነዋሪ የሆኑ በርካታ የአማራ ተወላጆች ላይ ድብደባ ፈፀሙ፡፡  በድብደባ በርካታ ሰዎች ከመጐዳታቸውም በተጨማሪ፤ ቤት ንብረት ላይም ጥፋት እንደደረሰ የተናገሩት ጉዳት የደረሰባቸው ግለሰቦች ጉዳዩን ሕገወጥ ነው ሲሉ አውግዘውታል፡፡ የከተማዋ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ሃላፊ፤ የስፖርት ውድድርን ሰበብ በማድረግ ረብሻ የቀሰቀሱ ሰዎች ህዝብን የማይወክሉ ወሮበሎች ናቸው ብለዋል፡፡ ረብሻውን ቀስቅሰዋል ተብለው ከተጠረጠሩት...
ሙሉውን አንብብ-Read More

Apr 14, 2014

How History and the 1931 Ethiopian Constitution Perceive the Ethiopians

Geez Bet | Monday, April 14, 2014
By Prof. Getachew Haile :- This short article addresses the issue of how Ethiopia's social and political problems are sometimes baseless, or based on minor misunderstandings. The Amharic section of the Voice of America (VOA) included a three-part discussion on the history of Ethiopia between Dr. Beyana Soba, a lawyer; Dr. Berhanu Mengist, a professor of conflict resolutions; and myself, a historian. A historian discussing history with non-historians might seem strange, but the end-result shows...
ሙሉውን አንብብ-Read More

Apr 14, 2014

Anole Oromo monument and Ethiopia’s history

Geez Bet | Monday, April 14, 2014
By Admasu Belay: - The shameful Anole (Aannolee) Oromo Monument built by the racist OPDO in the Arsi region of Oromia has angered many Ethiopians worldwide. The current regime says the monument was built to remember Oromo war prisoners allegedly mutilated by Menelik. But what we fail to understand is beyond the emotional reaction, we have overlooked its historical impact.  Since the TPLF/OLF created the current ethnic federalism system in 1993, they have brainwashed many Ethiopians...
ሙሉውን አንብብ-Read More

Apr 14, 2014

እኩልነት ወይስ የበላይነት? ኢትዮጵያን ለመምታት በማጭበርበር የተገኘ ተራድኦ

Geez Bet | Monday, April 14, 2014
ጌታቸው ኃይሌ :- መግቢያ፤  የዛሬው ድርሰቴ ለመግለጥ የሚሞክረው የዘወትር ድምፃቸው "ተበድለናል" የሚለው፥ የሌላው በደል ግን ደንታቸው  ያልሆነ፥ የኦሮሞስላሞች አክራሪዎችን ድብቅ ዓላማ ነው። የፈለገ እስላሞሮሞች አክራሪዎች ሊላቸው ይችላል። ዋናው ቁም  ነገር (1) ኦሮሞ መሆናቸው፥ (2) እስላሞች መሆናቸው፥ (3) አክራሪዎች መሆናቸው፥ (4) የሌላው ነገድ እስላም አክራሪዎች  የሚደግፏቸው መሆኑ፥ (5) የሚፈልጉት የበላይነት መሆኑ፥ ያ ካልሆነ ኢትዮጵያን ማውደም መሆኑ ለአገር ወዳዱ ሕዝብ  ግልጽ እንዲሆን ነው። እነሱ ግን "ኦሮሞ" መባልን ይመርጣሉ። ለብልሃታቸው ነው፤ ምክንያቱም፥ ኦሮሞስላሞች ወይም  እስላሞሮሞች ብቻ መባሉ እውነትነት ቢኖረውም፥ በነጠላው "ኦሮሞ" መባሉ ክርስቲያን ኦሮሞዎችንና እናት አገራቸውን  የሚወዱ...
ሙሉውን አንብብ-Read More

Apr 14, 2014

ስለፍትህ ሲባል ስርዓቱ ይፍረስ! ፪

Geez Bet | Monday, April 14, 2014
(ተመስገን ደሳለኝ ) :-  በዚህ ርዕስ ሥር ባለፈው ሳምንት በይደር ካቆየሁት ተከታይ ጽሑፍ በፊት አንድ እርምት የሚያሻው  ጉዳይን በአዲስ መስመር ላስቀድም፡፡   ሬዲዮ ፋና እና “አምደኞቹ”   በ1988 ዓ.ም በኤፈርት ባለቤትነት ስርጭቱን አሀዱ ያለው “ሬዲዮ ፋና”፣ ከምስረታው አንስቶ ዛሬም ድረስ  ልክ እንደ በረሃው ዘመን ሁሉ የሥርዓቱ ቀኝ እጅና የርካሽ ፕሮፓጋንዳው ማስተላለፊያ ቱቦ ሆኖ መዝለቁ  ለወዳጅም ለጠላትም የማያከራክር ገሀድ የወጣ ሐቅ ነው፡፡ በተለይ ደግሞ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተወሰኑ የግል  ሚዲያዎች ላይ የርግማን ዘመቻ የታወጀ ይመስል ለተከታታይ ሳምንታት “ስመ-ጥር” ረጋሚዎችን ጣቢያው  ድረስ ጋብዞ ማብጠልጠልና ማውገዙን ቀንደኛ ሥራው አድርጎ ይዞታል፡፡...
ሙሉውን አንብብ-Read More

Apr 13, 2014

ስለፍትሕ ሲባል፤ ሥርዓቱ ይፍረስ!

Geez Bet | Sunday, April 13, 2014
(ተመስገን ደሳለኝ) :-  ባለፉት አራት አስርታት ሀገሪቱ አያሌ ተግዳሮቶችን መጋፈጧ ባይዘነጋም፤ በተለያየ ጊዜ ሚሊዮኖችን  ካረገፈው አሰቃቂው ረሃብ በማይተናነስ መልኩ ሕዝቦቿን ዋጋ ያስከፈለ ጉዳይ ቢኖር የፍትሕ አለመከበር  ያስከተለው ሁለንተናዊ ምስቅልቅሎሽ ነው ብሎ ለመናገር የሚያስደፍሩ በርካታ ማሳያዎች አሉ፡፡ የየካቲቱን አብዮት ጠልፎ ሥልጣኑን የተቆጣጠረው ወታደራዊው ደርግ፣ የፍርድ ቤት ደጆችን በጓጉንቸር ቆልፎ  ሲያበቃ፣ የራሱ አባላት እጃቸውን እያወጡ ድምፅ በመስጠት በአፄው ባለስልጣናትንም ሆነ ግብረ-አበሮቹ  በነበሩ መኮንኖች ላይ የሞት ቅጣትን ያህል የመጨረሻ ከባድ ውሳኔ የማሳለፍን አስደንጋጭ ክስተት ጨምሮ፤  ከከተማ እስከ ገጠር ያደራጃቸው የአብዮት ጠባቂዎችና የገበሬ ማሕበራት ከየቤቱ አንቀው እያወጡ...
ሙሉውን አንብብ-Read More

Apr 9, 2014

‹‹ኢትዮጵያ የህዳሴውን ግድብ ግንባታ ካላቆመች ወታደራዊ ኃይል እጠቀማለሁ››

Geez Bet | Wednesday, April 09, 2014
ሞርታዳ ማንሱር፣ የግብፅ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ዕጩ  በግብፅ በቅርቡ ይካሄዳል ተብሎ ለሚጠበቀው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ራሳቸውን በዕጩነት ያቀረቡት የሕግ ባለሙያው ሞርታዳ ማንሱር፣ ‹‹ኢትዮጵያ የህዳሴውን ግድብ ግንባታ ካላቆመች ወታደራዊ ኃይል እጠቀማለሁ፤›› በማለት አስጠነቀቁ፡፡ አወዛጋቢና ስሜታዊ እንደሆኑ በይፋ የሚታወቁት የሕግ ባለሙያና ከሳምንት በፊት ደግም ዛማሌክ ለተባለው ታዋቂ የግብፅ እግር ኳስ ቡድን ሊቀመንበር ሆነው የተመረጡት ማንሱር፣  ማስጠንቀቂያውን ያስተላለፉት ባለፈው እሑድ ፕሬዚዳንታዊ ውድድርን አስመልክቶ በሰጡት ማብራሪያ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ላይ ጦነርት በመክፈት የግብፅ ሕዝብን ጥቅም እንደሚያስከብሩም ተናግረዋል፡፡ የዓባይ ወንዝን በተመለከተ እ.ኤ.አ. በ1929 እና በ1959 የተፈረሙ ዓለም አቀፍ ስምምነቶች መኖራቸውን ያስታወሱት ማንሱር፣ ኢትዮጵያ...
ሙሉውን አንብብ-Read More

Apr 7, 2014

መከላከያ ሚኒስቴር የህዳሴውን ግድብ ከማንኛውም ጥቃት የመከላከል አቅም እንዳለው አስታወቀ

Geez Bet | Monday, April 07, 2014
-ኢትዮጵያና ሱዳን የጋራ ድንበር ጠባቂ ጦር ሊመሠርቱ ነው::  የመከላከያ ሠራዊቱ የታላቁ ህዳሴ ግድብንና ሌሎች የአገሪቱ ግዙፍ ፕሮጀክቶችን ከማንኛውም ጥቃት የመከላከል ጠንካራ አቅምና ዝግጁነት እንዳለው፣ የመከላከያ ሚኒስትሩ አቶ ሲራጅ ፈጌሳ ለፓርላማ አስታወቁ፡፡  አቶ ሲራጅ የመከላከያ ሚኒስቴርን የግማሽ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ባለፈው ሐሙስ ለፓርላማው ባቀረቡበት ወቅት፣ ሠራዊቱ የህዳሴውን ግድብ የመጠበቅ አቅሙና ዝግጅቱ ምን ያህል እንደሆነ እንዲያብራሩ ተጠይቀዋል፡፡  ሚኒስትሩ ለቀረበላቸው ጥያቄ መልስ መስጠት የጀመሩት፣ በህዳሴው ግድብ ላይ ሊሰነዘሩ የሚችሉ ጥቃቶች በሁለት መንገድ ብቻ ሊሆኑ እንደሚችሉ በመተንተን ነው፡፡  ከተለዩት የጥቃት መንገዶች አንደኛው ቀጥታ በግድቡ ላይ የሚከፈት ቀጥታ ወታደራዊ ጥቃት ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ...
ሙሉውን አንብብ-Read More

Apr 7, 2014

ወታደራዊ ባንክ ለመመሥረት የተጀመረው እንቅስቃሴ ተቋረጠ

Geez Bet | Monday, April 07, 2014
የአገር መከላከያ ሚኒስቴር ወታደራዊ ባንክ በማቋቋም በ2006 ዓ.ም. ወደ ሥራ ለመግባት አቅዶ ጀምሮት የነበረውን እንቅስቃሴ አቋረጠ፡፡ የመከላከያ ሚኒስትሩ አቶ ሲራጅ ፈጌሳ ባለፈው ዓመት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭና የመከላከያ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት፣ ወታደራዊ ባንክ ለመመሥረት የተጀመረውን እንቅስቃሴ ገልጸው ነበር፡፡  ወታደራዊ ባንኩን የመመሥረት እንቅስቃሴው በአሁኑ ወቅት ሙሉ በሙሉ ተቋርጧል ሲሉ የመከላከያ ሚኒስትሩ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ ይሁን እንጂ ባንኩን የመመሥረት እንቅስቃሴ ለምን እንደተቋረጠ ከመግለጽ ተቆጥበዋል፡፡ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው የሪፖርተር ምንጮች ግን ወታደራዊ ባንኩን ለመመሥረት የተጀመረው እንቅስቃሴ የተቋረጠው በብሔራዊ ባንክ ውሳኔ ነው ብለዋል፡፡  መከላከያ ሚኒስቴር ወታደራዊ ባንክ ለመመሥረት...
ሙሉውን አንብብ-Read More

Apr 2, 2014

ከምዕራብ ሸዋ ዞን መሬት ተቀማን ያሉ የአማራ ተወላጆች ሰሚ አጣን አሉ

Geez Bet | Wednesday, April 02, 2014
“ወደ አንድነት ፓርቲ የመጣነው መሬት ያስመልስልናል ብለን አይደለም”  ስምንቱ በአዲስ አበባ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው አድረዋል  “ያለ አግባብ የተያዘ መሬት ላይ ሁሌም እግድ ይጣላል” - የዞኑ አስተዳደር በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ሸዋ ዞን ዳኖ ወረዳ አዋዲ ጉልፋ ቀበሌ፤ የመጡ 29 የአማራ ተወላጅ አርሶ አደሮች “መሬት እንዳናርስ ተከለከልን፤ ቅሬታችንን የሚሰማን አጣን” ሲሉ አማረሩ፡፡ ከ29ኙ ስምንቱ በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ፣ ወረዳ ሰባት ፖሊስ ጣቢያ፣ ረቡዕ ማታ ታስረው ማደራቸውንና ሀሙስ ረፋድ ላይ መለቀቃቸውን አርሶ አደሮቹ ለአዲስ አድማስ ተናግረዋል፡፡ አርሶ አደሮቹ አብዛኞቹ ከ1986 ዓ.ም ጀምሮ ከጎንደርና ከሌሎች የአማራ አካባቢዎች መሸኛ በማምጣት መሬት እንደተሰጣቸው፣ በአዋዲ ጉልፋ፣ በአጂላ ዳሌና በዙሪያው መሬት በማልማት፣...
ሙሉውን አንብብ-Read More

Apr 2, 2014

የአድባራት አስተዳዳሪዎች ማኅበረ ቅዱሳንን በአሸባሪነት መፈረጃቸው ሊቃነ ጳጳሳቱን አስቆጣ

Geez Bet | Wednesday, April 02, 2014
ቅሬታቸውን ለፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ሓላፊዎች ገልጸዋልየኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ተከታይ በኾኑ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የቤተ ክርስቲያኒቱን እምነትና ሥርዐት እንዲማሩ፣ ዕውቀታቸውንና ገንዘባቸውን በማቀናጀት ሞያዊ ድጋፍ እንዲያበረክቱ በማስተባበር ላይ የሚገኘውን ማኅበረ ቅዱሳንን በአሸባሪነት በመፈረጅ፣ በቅዱስ ሲኖዶስ አማካይነት ጠቅላላ ሀብቱና ንብረቱ የሚታገድበት ውሳኔ እንዲተላለፍ በመንግሥትም በኩል እርምትና ርምጃ እንዲወሰድበት የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት የአድባራት አስተዳዳሪዎች መግለጫ አውጥተውበታል በተባለው ስብሰባ ጉዳይ ኹለት የቅ/ሲኖዶስ አባላት ለከፍተኛ የመንግሥት ሓላፊዎች ቅሬታቸውን ማሰማታቸው ተገለጸ፡፡ የቅ/ሲኖዶሱን ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ሉቃስንና በአዲስ አበባ ሀ/ስብከት የፓትርያርኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስና የጅማ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስን...
ሙሉውን አንብብ-Read More

Apr 2, 2014

የአንድነት አመራሮች በወላይታ ሶዶ እንግልትና የንብረት ውድመት ደረስብን አሉ

Geez Bet | Wednesday, April 02, 2014
 ለውይይት ወደ ወላይታ ሶዶ ሄደው የነበሩት የአንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ አመራሮች  ከፍተኛ እንግልትና የንብረት ውድመት እንደደረሰባቸው ገለፁ፡፡ የፓርቲው የድርጅት ጉዳይ ሃላፊና ምክትል የድርጅት ጉዳይ ሃላፊውን ጨምሮ  የፓርቲው የወረዳው አመራሮች ተንቀሳቃሽ ስልኮች ባልታወቀ ኬሚካል ተነክረው ከጥቅም ውጭ መደረጋቸውን የአንድነት ፓርቲ አመራር  አቶ ዳንኤል ተፈራ ለአዲስ አድማስ ተናግረዋል፡፡ ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ በአንድነት አጠቃላይ እንቅስቃሴና በተሻሻለው የፓርቲው ፕሮግራም ላይ ለመወያየት አቶ ዳንኤል ተፈራና ምክትል የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ አቶ ዳንኤል ሺበሺ በተደረገላቸው ጥሪ፣  ወደ ወላይታ ሶዶ ከተማ መጓዛቸውን ገልፀው፣ከቀኑ አምስት ሰዓት አካባቢ በአንዱ የአንድነት አባል መኖርያ ግቢ ውስጥ ቡና እየጠጡ ለመወያየት መወሰናቸውን ...
ሙሉውን አንብብ-Read More