
Dec 24, 2014
Ethiopian pilots very likely to have landed at Eritrea-held Assab Port: source
Geez Bet | Wednesday, December 24, 2014

WASHINGTON, DC - An Ethiopian pilot and two of his crew members defected
to Eritrea flying an Mi-35 combat helicopter, the state television
announced on Monday.
The pilots were based in the eastern city of Dire Dawa and they executed
their plan during what the state-owned TV called a "routine flight
training." The announcement came in after days of massive aerial search
across northeastern Ethiopia.
The crew members were Captain Samuel Giday, Lt. Bililign Desalegn, and
flight technician...
Dec 24, 2014
የኢትዮጵያ መንግሥት ገመና – ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ (ከዝዋይ እስር ቤት)
Geez Bet | Wednesday, December 24, 2014

በእስር ላይ ያለው የተደናቂው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ሁለተኛውንና ‹የኢትዮጵያ መንግስት ገበና› የተሰኘው
ጦማር ከዝዋይ እስር ቤት ወጥቷል፡፡ ተመስገን አብረውት የታሰሩ የፖለቲከኛ እስረኞች በሚታወቅበት የጋዜጠኝነት
ችሎታው እየጠየቀና እያውጣጣ መፈጠራቸው የሚያስምሙ ታሪኮችን ለመልቀም እንደቻለ ጽሁፉን ያነበበ ይረዳዋል፡፡
ክፍል 2
ተመስገን ደሳለኝ
በዚህ አውድ ለማቅረብ የተገደድኩበትን ዘግናኝ ታሪክ፣ ወደር በሌለው አስከፊነቱ የተነሳ ለንባብ ባላበቃው
በወደድኩ ነበር፡፡ ግና! ይህ መንግስታዊ የጭካኔ ተግባር፣ ዛሬም በምስኪን ዜጎች ላይ እየተፈፀመና ብዙዎችን ሰለባ
እያደረገ በመሆኑ ህዝቡ ይህን ሊሸሸግ እየተሞከረ ያለውን መከራ ተረድቶ ሥርዓቱን በአደባባይ ዓመፅ “ሃይ!” ይል
ዘንድ ትርክቴን ለማጠናቀር ተገድጄያለሁ፡፡ ለእስር ያበቃኝ የጋዜጠኝነት ሙያዬም ተጨማሪ ዕዳ ጭኖብኛል፡፡
“ጄል-ኦጋዴን”
ጄል...
Dec 23, 2014
የሕወሓት አስተዳደር የአስመራው መንግስት ሄሊኮፕተሩን በሱዳን በኩል እንዲመልስለት መጠየቁ ተሰማ
Geez Bet | Tuesday, December 23, 2014

(ምንሊክ ሳልሳዊ) ስርአቱን ከዱ የተባሉት አብራሪዎች ከድሬዳዋ ተነስተው በጅቡቲ ድንበር አስታከው በአሰብ ዘልቀው
ኤርትራ ያሳረፉት ሄሊኮፕተር በሱዳን በኩል እንዲመለስለት ሻእቢያን መጠየቁን የሱዳን ዲፕሎማቶች ጠቆሙ::
ወያኔ በኢትዮጵያውያን ላይ የሚያደርገውን ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት እና በአየር ሃይሉ ውስጥ የሚፈጸመውን
ደባ በመቃወም ከድተዋል የተባሉት 2 ፓይለቶች(ካፒቴን ሳሙኤል እና ቢሊሊኝ )እና አንድ ቴክኒሽያን(ጸጋ
ብርሃን)ለኤርትራ መንግስት እጃቸውን የሰጡ ሲሆን ይህንንም የወያኔው ቴሌቭዥን ጣቢያ እማኝነቱን ሰቷል::
አብራሪዎቹ ይዘውት የሄዱትን ሄሊኮፕተር እንዲመለስለት ወያኔ የሱዳን ዲፕሎማቶችን የላከ ሲሆን ሻእቢያ
የማይመልስ ከሆነ የወያኔ መከላከያ ሰራዊት ከባድ አጸፋዊ እርምጃ እንደሚወስድ አንድ ለስርአቱ ቅርብ የሆነ ድህረገጽ
ጽፏል::
በሃገር ውስጥ...
Dec 23, 2014
Ethiopia: Pilot Hijacked Our Military Helicopter to Eritrea
Geez Bet | Tuesday, December 23, 2014

The Ethiopian Defense Ministry charges that a pilot hijacked to Eritrea an attack helicopter which went missing a few days ago.
In a statement issued late Monday the ministry said the pilot of the
Ethiopian attack helicopter forced his co-pilot and technician to land
in Eritrean territory.
The helicopter was conducting a routine training flight when it
disappeared on Friday morning, prompting a massive military search
across northern Ethiopia.
It's unusual for Ethiopian army personnel...
Oct 9, 2014
‹ፍልስፍና ምንድን ናት?› ብሎ ለጠየቀ!
ZETOBIA | Thursday, October 09, 2014
(በካሣሁን ዓለሙ)
‹ፍልስፍናን እማራለሁ› ብዬ ት/ቤት ብገባ፣ መምህሩ ‹ፍልስፍና
ምንድን ናት?› ብሎ መልሶ እኔኑ ጠየቀኝ፤ ‹ካወቅኳትም ለም
ንስ ልማራት ሒሳብ ከፈልኩ?› አልኩኝ፤ ምን ላድርግ?
ቢቸግረኝ ያው ‹የፍልስፍና አስተማሪዎች ናቸው› ከሚባሉት ፋይል የሰማሁትን ስምምነታቸውን ይዤ፡- ፍልስፍና እኮ
እንዲህ ነው ማለት ጀመርኩ!
በመሠረቱ ጭንቁ መልሱ ላይ ነው እንጂ የፍልስፍና አዋቂና ምጡቅ
የተባለ ሁሉ ይችን ‹ፍልስፍና ምንድን ናት?› የምትል ጥያቄ ሳያነሳት አይቀርም፤ መምህሬም ‹ጥያቄዋ ትንሽ ገብታው
ነው› መሰል የጠየቀኝ፤ እንደኔ ያላብላሉት ሳይሆኑ መልሷን ሲጭሩ የኖሩት ሊቃውንት ግን ግምታዊ መልሳቸውን
ሰጥተዋል፤ እኔም በመጠኑ ሰምቻለሁ (ከፈለጋችሁ ጆሮ ጠገብ በሉኝ)፡፡ በአጠቃላይ ግን በሊቃውንቷ ‹ፍልስፍና ጥበብን
ማፍቀር ናት› የሚል...
Aug 27, 2014
የፕሮፌሰር ጌታቸው ነገር! (ወርቁ ፈረደ)
Geez Bet | Wednesday, August 27, 2014

ብሄርተኝነትን ታጥቀው አገራችንን ወደ አደገኛ ጠርዝ ከሚገፏት ምሁራን መካከል፣ የተወሰኑት ላይ የአቅሜን ያህል ሂስ ለመሰንዘር ሞክሬያለሁ፡፡ አሁን ደግሞ የፕሮፌሰር ጌታቸውን አንዳንድ የተዛቡ ሀሳቦች ለመዳሰስ እሞክራለሁ፡፡
ፕሮፌሰር ጌታቸው አንቱ የሚባሉ ምሁርና አንተ የሚባሉ ፖለቲከኛ ናቸው፡፡ ጥናቶቻቸውን አንብቦ በእውቀታቸው ስፋት እና በጽሁፍ ችሎታቸው የማይደነቅ ሰው ማግኘት ይከብዳል፡፡ ያም ሆኖ ጌቾ በመጣጥፎቻቸው፣ በግለ ታሪካቸው፣ እንዲሁም የአባ ባህርይ ድርሰቶችን በሰበሰቡበትና ባሰናዱበት ጥራዛቸው የሚያንጸባርቋቸው አንዳንድ የተዛቡና አደገኛ ሐሳቦች አብረው የሚያኗኑሩ አይደሉም:፡
ለምሳሌ በቅርቡ፣ በአንዳንድ የኦሮሞ ብሄርተኞች በኩል ለሚሰነዘሩ ዘለፋዎች ምላሽ እንዲሆን የጻፉትን “ዕርቅና ሰላም፣ የሕይወት ቅመም” የተባለ መጣጥፋቸውን ያነበበ ሰው፤ አንጋፋ ምሁራኖቻችን...
Aug 27, 2014
“በበዓሉ ግርማ ጉዳይ ላይ ከሕሊና ዕዳ ነጻ ነኝ” ደራሲና ሐያሲ አስፋው ዳምጤ
Geez Bet | Wednesday, August 27, 2014
ደራሲና ሐያሲ አስፋው ዳምጤ ናደው፣ የተወለዱት መጋቢት 1ዐ ቀን 1927 ዓ.ም. አዲስ አበባ ጊዮርጊስ አካባቢ፣ መርሐ ጥበብ
ማተሚያ ቤት ግቢ ከሚባለው ቦታ ነው፡፡
አቶ አስፋው የቤተ ክህነት ትምህርት ለጥቂት ጊዜ ከተማሩ በኋላ፣ በዘመናዊ ትምህርት፣ የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃን፣ በኮከበ
ፅባሕ ቀ.ኃ.ሥ. አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት፣ በመጀመሪያ ዲግሪ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ በሁለተኛ ዲግሪ ደግሞ
በእንግሊዙ ኪምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ ተምረው ተመርቀዋል፡፡
ወደሥራ ዓለም ከተቀላቀሉ በኋላ፣አብዛኛውን የሥራ ጊዜያቸው በገንዘብ ሚኒስቴር በተለያዩ የኃላፊነት ደረጃዎች ያገለገሉ ሲሆን፣
ከገንዘብ ሚኒስቴር እንደለቀቁ በኢትዮጵያ መጽሐፍ ድርጅትና በኩራዝ አሳታሚ ሠርተዋል፡፡
አቶ አስፋው ከኢትዮጵያ ውጭ ካሳለፉት ሰባት ዓመታት ውስጥ፣ በእንግሊዝ ለትምህርት ሶስት ዓመት፣ ቀሪውን አራት ዓመት
ደግሞ...
Aug 8, 2014
አገሬ ታማለች!
ZETOBIA | Friday, August 08, 2014

አገሬ ታማለች!
(በካሣሁን ዓለሙ)
እማማ ታማለች፣
አገሬ ታማለች፣
ሆስፒታል ተኝታ
እ!እ!…ህእ!ም!…ህም!!! ትለኛለች፤
ከህቅታዋም ውስጥ ጣሯ ይሰማኛል፣
ህመሟን ስቃዩዋን፣
ዝም ብዬ እየሰማሁ፣
እማዬ! እላታለሁ፤
ህመሟ ያመኛል፣
ጧሯ ይነዝረኛል፣
አዎ! እማማ ታማለች፣
ይኸው በሆስፒታል
እ!!…ህ!!!.. እህ!!!… ትለኛለ...
Jul 14, 2014
የአንዳርጋቸው ጽጌ የእንግሊዝ ፓስፖርት
Geez Bet | Monday, July 14, 2014

ማክሰኞ ምሽት ሐምሌ 1 ቀን 2006 ዓ.ም. ኢቲቪ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን አስመልክቶ ያቀረበው ዜናን ብዙዎች በተቀላቀለ ስሜት ነበር የተከታተሉት፡፡
ዜናው የአቶ አንዳርጋቸውን ንግግር ለአፍታ ያቀረበ ሲሆን ይዘቱ ግን ግራ ያጋባቸው በርካቶች ናቸው፡፡ አቶ አንዳርጋቸው ‹‹እኔ አሁን ከራሴ ጋር ታርቄ ሰላም አግኝቻለሁ፡፡ እውነቴን ነው የምልህ እኔ እንደ ምርቃት ነው የተቀበልኩት፡፡ አሁን የሚያስቸኩለኝ ነገር የለም፡፡ ጥሩ ዕረፍት ማድረግ እፈልጋለሁ፡፡ ምክንያቱም በጣም በጣም ደክሞኛል … ሰልችቶኛል፡፡ እውነቴን ነው የምልህ ተረጋግቼ ያለሁበት ሁኔታ ነው፡፡ ምንም ዓይነት ጥላቻ በውስጤ የለም፡፡ ምንም ዓይነት ብስጭት የለኝም፡፡ ምንም ዓይነት መጥፎ ስሜት አይሰማኝም፡፡ በቃ … የመጨረሻ እርጋታና ዕረፍት ውስጥ ነው ያለሁት፤›› ሲሉ ተደምጠዋል፡፡
ከአንዴም ሁለቴ በፍርድ ቤት...
Jul 8, 2014
አይ አበሻ! አበሻና ቀጥታ መስመር [ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ-ማርያም]
Geez Bet | Tuesday, July 08, 2014

አበሻና ቀጥታ መስመር አይተዋወቁም፤ ቀጥታ መስመር መጀመሪያ አለው፣ መጨረሻም አለው፤ አበሻ እንዲህ ተጀምሮ የሚያልቅ ነገር አይወድም፤ እልቅ ሲል ጭር ይልበታል፤ አበሻ የባህርዩ የሆነውና የሚስማማው ክብ መስመር ነው፣ ክብ መስመር መጀመሪያ የለው፣ ማለቂያ የለው፣ ሲዞሩ መዋል ነው፤ አበሻ ነገሩ ሁሉ ክብ ነው፤ ቤቱ ክብ ነው፣ እንጀራው ክብ ነው፣ ዳቦው ክብ ነው፣ ድስቱ ክብ ነው፣ ጋኑም ክብ ነው፤ ክብ ያልሆነነገር አበሻ ምን አለው?
አበሻ ነገሩ ሁሉ ክብ ነው፣ አዙሪት ነው፣ ታሪኩም አዙሪት ነው፣ ሄደ የተባለው ሁሉ ተመልሶ ይመጣል። አበሻ ማለት አዙሪት ነው፣ አዙሪት ማለትም አበሻ ነው። የእንግሊዝ ወይም የሩስያ ወታደሮችን ሰልፍ ስታዩ ቀጥታ መስመር ምን እንደሆነ ተገነዘባላችሁ። የአበሻ ወታደሮችስ? ተለያይቶ የተገጣጠመ ክብ መስመር?
አበሻ በመስመር መሄድም ሆነ መቆም አይሆንለትም።...
Jul 8, 2014
ኢትዮጵያውያን ባሎች ሚስቶቻቸውን በመደብደብ ከአፍሪካ 3ኛ ናቸው
Geez Bet | Tuesday, July 08, 2014

87 በመቶ የማሊ ሴቶች ድብደባ ተገቢ ነው ይላሉ::
የጊኒና የኢትዮጵያ ሴቶችም ድብደባ ተገቢ ነው ብለው ያስባሉ::
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የተለያዩ ተቋማት በቤት ውስጥ ጥቃት ዙሪያ ያወጧቸውን ሪፖርቶች መነሻ በማድረግ በቅርቡ በ37 የአፍሪካ አገራት ላይ የተሰራ አንድ ጥናት፣ ኢትዮጵያውያን ባሎች ሚስቶቻቸውን አዘውትረው በመደብድብ 3ኛ መሆናቸውን አረጋገጠ።
‘አፍሪካ ሄልዝ፣ ሂዩማን ኤንድ ሶሻል ዲቨሎፕመንት ሰርቪስ’ የተባለው አህጉራዊ ድርጅትና በሴቶች ጥቃት ዙሪያ የሚሰሩ ሌሎች ተቋማት በጋራ የሰሩት ጥናት እንደሚለው፣ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ኢትዮጵያውያን ባሎች የትዳር አጋሮቻቸውን መደብደብ አግባብ ነው ብለው የሚያስቡና በተለያዩ ምክንያቶች ሚስቶቻቸውን የሚደበድቡ ናቸው፡፡
ጥናቱ ከተሰራባቸው የአፍሪካ አገራት የበለጠ ተደባዳቢ ባሎች...
Jul 7, 2014
ድኻው ምን አረገ
Geez Bet | Monday, July 07, 2014

ዳንኤል ክብረት: -
ሰሞኑን ከአንድ ሰው ‹የማጭበርበር› ነገር ጋር በተያያዝ ከዚህም ከዚያም አስተያየት ይሰጣል፡፡ አብዛኞቹ የመገናኛ ብዙኃንም ትኩረታቸውን በሰውዬው ላይ አድርገው እንዴት እንዲህ ሊያደርግ ቻለ? ለምን እንዲህ አደረገ? ምን ነክቶት ነው? እያሉ ጉዳዩን ከማኅበረሰብ ሳይንስ፣ ከሥነ ልቡና፣ ከእምነትና ከባሕል አንጻር እየተነተኑ ይገኛሉ፡፡
እኔ ግን ይህን ጉዳይ ስከታተል ትዝ የሚለኝ አንድ የሀገራችን ተረት ነው፡፡ ሰውዬው መንገድ ላይ ሲሄድ በሩ ወለል ብሎ የተከፈተ ቤት ያገኛል፡፡ ለጥቂት ቆም ብሎ ሁኔታውን ሲያይ ማንም በአካባቢው ዝር የሚል አልነበረም፡፡ ነገሩ የተከፈተ በር ብቻ ሳይሆን ‹የተከፈተ ዕድልም› የሆነለት ሰውዬ የተከፈተው ቤት ውስጥ ዘው ብሎ ይገባል፡፡ማንም አልነበረም፡፡ ወዲያና ወዲህ እየተንጎራደደ ቤቱን ቃኘና ዓይኑ ያረፈበትን...
Jul 7, 2014
'Britain is supporting a dictatorship in Ethiopia'
Geez Bet | Monday, July 07, 2014

By: David Smith:-
It's 30 years since Ethiopia's famine came to attention in the UK. Now, a farmer plans to sue Britain for human rights abuses, claiming its aid has funded a government programme of torture and beatings as villagers have been removed from their homes.
"Life was good because the land was the land of our ancestors. The village was along the riverside, where you could get drinking water, go fishing and plant mango, banana and papaya. The...
Jul 7, 2014
የእንግሊዝ መንግሥት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ለኢትዮጵያ መተላለፋቸውን መስማቱን አስታወቀ
Geez Bet | Monday, July 07, 2014

-አና ጎሜዝ ወደ እንግሊዝ መመለስ አለባቸው እያሉ ናቸው::
ከዱባይ ወደ አስመራ ለመሄድ የመን ሰንዓ ላይ በየመን የፀጥታ ኃይሎች ተይዘው ታስረዋል የተባሉት በሽብርተኝነት የተፈረጀው የግንቦት 7 ዋና ጸሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ፣ ለኢትዮጵያ ተላልፈው ተሰጥተዋል መባሉን እንደ ሰማ የእንግሊዝ መንግሥት አስታወቀ፡፡
ከሚመለከታቸው የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ማረጋገጫ እንደሚፈልግ ገልጿል፡፡
በአዲስ አበባ የሚገኘው የእንግሊዝ ኤምባሲ የፖለቲካ ጉዳዮች ምክትል ጸሐፊ ሚስተር ኢያን ኮክስ አቶ አንዳርጋቸውን በሚመለከት ለሪፖርተር በላኩት መግለጫ እንዳስረዱት፣ የእንግሊዝ ዜግነት ያላቸው አቶ አንዳርጋቸው ሰኔ 16 ቀን 2006 ዓ.ም. ሰነዓ ውስጥ መጥፋታቸው ተገልጾላቸዋል፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የእንግሊዝ ባለሥልጣናት አቶ አንዳርጋቸው ያሉበትን ሁኔታና ሥፍራ...
Jul 2, 2014
የግንቦት 7 ዋና ጸሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በየመን በቁጥጥር ሥር ስለመዋላቸው የሪፖርተር ዘገባ
Geez Bet | Wednesday, July 02, 2014

መነሻቸውና መድረሻቸው ከየትና ወዴት እንደሆነ ያልተገለጸው የግንቦት 7 ዋና ጸሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ፣ የመን ሰንዓ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በየመን የፀጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር ውለው መታሰራቸው ተሰማ፡፡
አቶ አንዳርጋቸው በየመን የፀጥታ ኃይሎች ተይዘው ታስረዋል የተባለው ሰኔ 16 ቀን 2006 ዓ.ም. ሲሆን፣ ሰንዓ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ከመያዛቸው ውጪ ከየት ተነስተው ወዴት እንደሚሄዱ አልታወቀም፡፡
በኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአሸባሪነት ከተፈረጁት አልቃይዳ፣ አልሸባብ፣ ኦነግና ኦብነግ ጋር በአሸባሪነት የተፈረጀው ግንቦት 7 ዋና ጸሐፊውን በሚመለከት ያወጣው መግለጫ እንደሚያስረዳው፣ አቶ አንዳርጋቸው በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ካወቀ ጊዜ ጀምሮ በተለያዩ መንገዶች ለማስለቀቅ ውስጥ ለውስጥ ጥረት ቢያደርግም...
Jul 1, 2014
የግንቦት 7ቱ ዋና ጸሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በየመን ታሰሩ
Geez Bet | Tuesday, July 01, 2014

የግንቦት 7 ከፍተኛ አመራር አባልና በአስመራ የሚገኘውን የግንቦት 7 ትግል ይመሩታል የሚባሉት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በየመን መታሰራቸውን ግንቦት 7 ባወጣው መግለጫ አስታወቀ።
እንደ ግንቦት 7 ንቅናቄ መግለጫ ከሆነ አቶ አንዳርጋቸው ላለፉት አንድ ሳምንታት በየመን ታግተው የሚገኙ ሲሆን ለማስለቀቅ የተደረገው ጥረትም አልተሳካም። አቶ አንዳርጋቸው ወደ የመን የተጓዙት ለትራንዚት እንደሆነ የገለጸው የንቅናቄው መግለጫ የየመን መንግስት እኚህን የትግል ሰው ለኢትዮጵያ መንግስት አሳልፎ እንዳይሰጥ ስጋት እንዳለበት አስታውቋል።
በአቶ አንዳርጋቸው መታሰር ጉዳይ በሶሻል ሚዲያዎች ላይ መነጋጋሪያ የሆነ ሲሆን የፖለቲካ ተንታኙ ጃዋር መሀመድ የሚከተለውን በፌስቡክ አስፍሯል።Jawar Mohammed On Facebook:
“Despite our difference in political opinion,...
Jul 1, 2014
Yemen detains Andargatchew Tsige during transit at airport
Geez Bet | Tuesday, July 01, 2014

WASHINGTON, DC - Yemeni authorities on June 24 arrested a top Ethiopian rebel group leader while he was in transit at Sanaa airport, sources said.
Andargatchew Tsige, secretary of Ginbot 7, a rebel group based in Eritrea, arrived in the Yemeni capital aboard Yemenia Airlines. He was waiting for his flight when Yemeni security men whisked him away into detention. Fears are mounting he might be extradited to Ethiopi...
Jul 1, 2014
10 የሱዳን ወታደሮች በኢትዮጵያ ድንበር አካባቢ ተገደሉ
Geez Bet | Tuesday, July 01, 2014
.jpg)
አፍሪካን ፕሬስ ኤጀንሲ እንደዘገበው 10 የሱዳን ወታደሮች በኢትዮ -ሱዳን ድንበር አካባቢ ከተገደሉ በሁዋላ በድንበር አካባቢ ውጥረት ሰፍሯል። እሁድ እለት ደግሞ ተጨማሪ 13 የሱዳን ወታደሮች መቁሰላቸው የተዘገበ ሲሆን፣ ጥቃቱም በኢትዮጵያ ሚሊሺያዎች ሳይፈጸም እንዳልቀረ ተዘግቧል።
የሱዳን ኮማንዶ ጦር ወደ ኢትዮጵያ ድንበር ሃይሉን እያሰባሰበ መሆኑን የገለጸው ዘገባው፣ በአንድ ወር ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ መካሄዱን ጠቅሷል። ሱዳንና ኢትዮጵያ የድንበር ከተሞቻቸውን ከታጣቂዎች ጥቃት ለመከላከል በሚል አንዱ በሌላው አገር ድንበር ጥሶ በመግባት እርምጃ እንዲወስድ መስማማታቸው ይታወቃል።
የሱዳን መንግስት ወታደሮቹ መገደላቸውን አምኖ፣ በኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት ተገደሉ የሚለውን እንደማይቀበለው አስታውቋል። የሱዳን መንግስት ጦር ቃል አቀባይ ኮሌኔል አልስዋርሚ ካሊድ ሳድ እንደተናገሩት...
Jun 30, 2014
ልቃዊነት የዘመናችን ሃይማኖት
ZETOBIA | Monday, June 30, 2014

ካሣሁን ዓለሙ:-
ሃይማኖት በሥርዎ ቃሉ ማመንና መታመን የሚሉ ፅንሣተ-ሐሣብን የያዘ ቃል ነው፡፡ ማመን በአንድ ነገር ላይ እምነት ማሳደር ሲሆን መታመን ደግሞ ላመኑበት ነገር መታገልና መቆም ነው፡፡ ይህንን ይዘን ወደ ፍልስፍናው መከራከሪያ ስንገባ በዓለማችን የሚገኙ የሃይማኖት ይዘቶችን በሦስት ከፍለን ልንያቸው እንችላለን፡፡
1) በእግዚአብሔር ህልውነት ላይ የተመሠረተ ሃይማኖት (Theist)
የእግዚአብሔር ህልውነትን በማመንና እሱን በመመሥከር እግዚአብሔር ከፍጥረቱ ጋር ግኑኝነት የሚያደርግ በሥራው ፍፁም የሆነ አምላክ መሆኑን ይቀበላል፡፡ ስለሆነም የሰው ልጆች ከእነሱ በላይና ፍጹም ከኾነ ኃይል ጋር ግንኙነት ያደርጋሉ፤ እሱም በመገለጥ ስለ ዐለማትና ፍጥረታት አፈጣጠር፣ ስለ ሰው ልጆች መፈጠርና ህልውና ነግሯቸዋል፤ ያነጋግራቸዋል ብሎ ያምና፤ ለዚህም ጥብቅና ቆሞ...
Jun 30, 2014
Ethiopian Sudani border Security tension flares again
Geez Bet | Monday, June 30, 2014

hartoum (HAN) June 30, 2014. Regional Security border updates. The Horn of Africa’s Fractious neighbors renew crossfire over disputed border lines after a Sudan troops was killed in clashes with unknown Ethiopian forces.
“Ethiopian militia group opened unprovoked fire from across the border at Sudan border post , they fired mortars and automatic weapons,” one
Sudani Diplomat told HAN (the Horn of Africa Newsline) in Khartoum on condition of anonymity. “Our troops responded...