Time in Ethiopia:

Nov 5, 2013

አነጋጋሪዉ የስለላ ቅሌትና ጀርመን

Geez Bet | Tuesday, November 05, 2013
የአሜሪካንን ምስጢራዊ መረጃዎች ያጋለጠው የቀድሞው የአሜሪካን የስለላ ድርጅት ባልደረባ ኤድዋርድ ስኖውደን፤ ባለፈዉ ሳምንት ሐሙስ ከታዋቂዉ የጀርመን ፖለቲከኛ ጋር ሞስኮ ላይ ሲገኛኝ ጀርመን ሁኔታዎችን ካመቻቸችለት በጀርመን ምክር ቤት ተገኝቶ ስለ አሜሪካ የስለላ ጉዳይ በግልፅ ለመናገር እንደሚፈልግ መናገሩ ይታወቃል።
       ይህ ከተሰማ ከቀናቶች በኋላ ደግሞ የዩናይትድ ስቴትስ የሕግ አርቃቂዎች ለቀድሞዉ የአሜሪካ የስለላድርጅት ባልደረባ ለኤድዋርድ ስኖዉደን ምንም ዓይነት ምሕረት እንደማይሰጡ ተናግረዋል። የስኖዉደን እና የአሜሪካ ዛቻ የጀርመናዉያን ለስኖዉደን ጥገኝነት ለመስጠት መፈለግ እያነጋገረ መሆኑን የዶቼ ቬለዉ ፍሪደል ታዉበ ዘግቧል። የአሜሪካንን ምስጢራዊ መረጃዎች ያጋለጠው የቀድሞው የአሜሪካን የስለላ ድርጅት ባልደረባ ኤድዋርድ ስኖውደን፤ የስደት ህይወት ፀጥታ የነገሰበት አይደለም። ስኖዉደን ከቤተስብ እና ጓደኛ ናፍቆት ባሻገር፤ ሌሎች ጥቃቅን ነገሮችን ሁሉ እንደሚናፍቅ ተናግሮአል። ከነዚህ መካከል ደግሞ በአሜሪካ በፍቅር ይበላዉ የነበረዉ እስካሁን ግን በሩስያ ያላገኘዉ ደረቅ የድንች ጥብስ መሰል ምግብ በዐይኑ ላይ መዞሩ ነዉ። የቀድሞዉ የአሜሪካ የስለላ ድርጅት ባልደረባ ስኖዉደን፤ ይህን የገለፀዉ ባለፈዉ ሳምንት ሐሙስ የአረንጓዴ
ፓርቲ አባል የሆኑት የጀርመኑ ፖለቲከኛ ሃንስ ክርስቲያን ሽቶሮብለ ሞስኮ ሩሲያ ላይ ባገኙት ወቅት አብሮአቸዉ ለነበዉ
አንድ የጀርመን ጋዜጠኛ ነበር። ስኖዉደን በአሜሪካ ይበላዉ ከነበረ ቶርቶላ ናፍቆት ባሻገር፤ ጀርመናዉያኑ እንግዶቹ ይበልጥ መስማት የሚፈልጓቸዉን ሌሎች ርዕሶችንም ሳይጠቅስ አላለፈም። ይኸዉም ስኖዉደን ቅድመ ሁኔታዎች ከተመቻቹለት ስለስለላዉ ጉዳይ ጀርመን ፓርላማ በመገኘት የመግለፅ ፍላጎት እንዳለዉ፤ ለጀርመናዊዉ ታዋቂ ፖለቲከኛ ሃንስ ክርስቲያን ሽቶይብለ ነግሮአቸዋል።
ኤድዋርድ ስኖውደን፤ ጥገኝነት የሰጠችዉን ሩስያን ለቆ ወደ ጀርመን ለዚህ ጉዳይ ከመጣ ያስጠጋችዉን ሀገር ድንበር ሲለቅ ያለዉን የጥገኝነት መብት ስለሚያጣ፤ ወደ ሩስያ ተመልሶ ለመግባትና ለመኖር ዳግም የጥገኝነት ጥያቄ ማቅረብ ይኖርበታል። ይህን ያስተዋሉ አንዳንድ የጀርመን ፖለቲከኞች ታዲያ፤ ግለሰቡ አጣብቂኝ ዉስጥ ከሚገባ መጥቶ የአሜሪካንን የስለላ ቅሌት በዝርዝር ካጋለጠ፤ የፖለቲካ ጥገኝነት ቢሰጠዉ የሚል ሃሳብ ሲሰጡ ተደምጦአል። የአረንጓዴ ፓርቲ አባል ሃንስ ክርስቲያን ሽቶሮብለ ስኖዉደን በአሜሪካን ኮንግረስ ፊት ቀርቦ ይፋ ስላወጣዉ መረጃ ምስክርነት ለመስጠት ዝግጁ ነኝ ማለቱንም ተናግረዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለም ባሳለፍነዉ ሳምንት መጨረሻ የአሜሪካ ከፍተኛ የሕግ አዉጪዎች፤ የአሜሪካንን የስለላ ጉዳይ አደባባይ ያወጣዉ ስኖዉደን ለጀርመን ምክር ቤት ደብዳቤ በይፋ ከላከ በኋላ ግልጽ እንዳደረጉት ፤ ስኖዉደን ምንም አይነት ምህርት አያገኝም። በአሜሪካ ሴኔት የስለላ ኮሚቴ ዋና ሊቀመንበር ዲአነ ፋይንስታይን እንዳሉትም፤ ስኖዉደን እድሉን ሳይጠቀምበት ቀርቶአል፤
«ምስጢር አጋላጭ ከሆነ ስልክ አንስቶ ለምክር ቤቱ የስለላ ኮሚቴ እንዲሁም፤ ለሴኔቱ የስለላ ኮሚቴ በመደወል « ልታዩት የሚገባ መረጃ አለኝ» ማለት የሚችልበት እድል ነበረዉ። እናም በእርግጠኝነት እናየዉ ነበር። ሁለታችንም በጋራ ወይም በተናጠል ብቻ እናየዉ ነበር። ያንንም መረጃ ባየነዉ ነበር። ግን ይህ አልሆነም። አሁን ሀገራችን ላይ ይህን ከባድ ጉዳት አድርሷል፤ እናም እንደሚመስለኝ መልሳችን ምንም ዓይነት ምሕረት የለም ነዉ።»
በሌላ በኩል በዩናይትድ ስቴትስ እና በአዉሮጳዉ ኅብረት ወንጀለኛ ተብሎ የሚፈልጉትን ግለሰብ አሳልፎ የመስጠት ዉል መኖሩይታወቃል። በጀርመን ምክር ቤት የጥናት መዘርዝር መሠረትም ተመሳሳይ መግባቢያ ቢኖርም፤እንደ ስኖዉደን ዓይነቱ በፖለቲካ ጉዳይ ተፈላጊ ግለሰብ ግን ተላልፎ ላይሰጥ ይችላል። የአረንጓዴዎቹ ፓርቲ አባል እና የጀርመን ምክር ቤትፕሬዝደንት ክላዉዲያ ሮትም፤የስኖዉደን የማጋለጥ ተግባር ለኛ ትልቅ ማስጠንቀቂያ እና ጠቋሚ ነዉ።እዚህ ያለስጋት መጥቶ የመኖር ሁኔታዉ የሚመቻችለት ቢሆን ትልቅ ምስክር ሊሆን ይችላል ሲሉ ተናግረዋል። እንደ ክላዉዲያ ሮት ሁሉ ሽፒግል ለተሰኘ አንድ የጀርመን ታዋቂ መፅሄት ስኖደን ጀርመን ሀገር ጥገኝነት እንዲሰጠዉ አስተያየታቸዉን ከሰጡ5ተ ታዋቂ ጀርመናያን መካከል የቀድሞዉ የክርስትያን ዲሞክራቲክ ህብረት ፓርቲ ዋና ጸሐፊ ሀይነር ጋይስለር እንዲሁም እዉቁ የፊልም ተዋናይ ዳንኤል ብሩል ይገኙበታል።
በአሜሪካን ምክር ቤት ሪፐብሊካኑ የምክር ቤት የስለላ ኮሚቴ ዋና ተጠሪ በበኩላቸዉ የቀድሞዉ የNSA ባልደረባ ኤድዋርድ ስኖዉደን የፋቱን ቅጣት ለማቅለል ሳይሆን መረጃዉን ለምን እንደሰረቅ ሊነግረን ከቻለ ላናግረዉ እችላለሁ ነዉ ያሉት፤ « ሕግንበመጣስስለሰረቀዉና ስለወሰደዉመረጃ፤ እንዲሁም ስለጣሰዉ መሃላ ኃላፊነትወስዶ ማብራሪያ ለመስጠት ተመልሶ መምጣት ከፈለገ፤ ከእሱ ጋ ለመነጋገር ደስተኛ ነኝ። ግን ላደረገዉ ተጠያቂ መሆን አለበት፤ ለምን እንዳደረገዉ እና የመሳሰሉትን መናገር አለበት፤ ያን የማድረጊያዉ ጊዜም ነዉ ተገቢዉም መንገድ ነዉ።» ከስኖዉደን ለጀርመን ምክር ቤት ደብዳቤ ይዘዉ ከሞስኮ የተመለሱት፤የጀርመኑ ታዋቂ ፖለቲከኛ ስኖዉደን የአሜሪካን ጠላት የሚባል ሰዉ እንዳልሆነ ለመረዳት መቻላቸዉን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ተናግረዋል።

አዜብ ታደሰ

ሸዋዪ ለገሠ
Source: www.dw.de

No comments:

Post a Comment