Time in Ethiopia:

Nov 11, 2013

የስዑዲ ምህረትና የሁለት ኢትዮጵያውያን መገደል

Geez Bet | Monday, November 11, 2013
የሳውዲ መንግሥት ለ ሁለተኛ ጊዜ የሰጠው የምህረት አዋጅ ቀነ ገደብ ካበቃበት ካለፈው እሁድ አንስቶ በተካሄደ የፖሊስ ክትትል ሁለት ኢትዮጵያውያን መገደላቸውን ሳውዲ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን አስታወቁ ። እነዚሁ ነዋሪዎች እንዳሉት ባለፉት ሶስት ቀናት ከሞቱት ሌላ በርካታ ኢትዮጵያውያን ታፍሰዋል ።
በአስር ሽዎች የሚቆጠሩ ደግሞ ከሞላ ጎደል ሥራቸውን አቁመዋል። የጅዳው ወኪላችን ነበዩ ሲራክ እንደዘገበው የምህረቱ የመጨረሻ ቀን ካለፈ በኋላ መንግስት በወሰደው እርምጃ ከ 5 ሺህ በላይ የተለያዩ ሃገራት ዜጎች ተይዘዋል። መንግሥት ሕገወጥ የሚላቸው እነዚህ የውጭ ዜጎች የሁለት ዓመት እሥራትና 100 ሺህ የሳውዲ ሪያል ቅጣት ይጠብቃቸዋል። ከምህረት አዋጁ ማለቅ በኋላ በጂዳ የኢትዮጵያውያን ዓለም ዓቀፍ ትምህርት ቤት ሥራ መስተጓጎሉንም ነብዩ ሲራክ ከጅዳ ዘግቧል ።

ነብዩ ሲራክ
ሂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ
Source: www.dw.de

No comments:

Post a Comment