
Jul 31, 2013
በዓባይ ጉዳይ የግብፅ መንግሥት ሠራዊቱን በተጠንቀቅ እንዲቆም አዘዘ
Geez Bet | Wednesday, July 31, 2013

By: Ethiopian Reporter
ሱዳን በቅርቡ ከግብፅ ጐራ ልታፈነግጥ ትችላለች
በዘካሪያስ ስንታየሁ
አዲሱ የግብፅ መንግሥት በዓባይ ጉዳይ ከኢትዮጵያ ጋር ሊነሳ በሚችል ግጭት ምክንያት ሠራዊቱን በተጠንቀቅ
እንዲቆም ቢያዝም፣ የግብፅ የጦርነት እንቅስቃሴ ትኩረት ለማስቀየር መሆኑን የኢትዮጵያ መንግሥት አስታወቀ፡፡
ኢትዮጵያ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከሱዳን ጠረፍ 40 ኪሎ ሜትር ወደ ውስጥ ገባ ብላ በምትገኘውና ቡምባዲ
በምትባለው አካባቢ 5,250 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም ያለውን ታላቁ የሚሌኒየም ግድብ ፕሮጀክት ይፋ ካደረገች
በኋላ፣ ግብፅ የተለያዩ ጫናዎችን በኢትዮጵያ ላይ ለማሳደር እየተንቀሳቀሰች ትገኛለች፡፡ ግብፅም በዚህ ግድብ
ምክንያት የዓባይ የውኃ መጠን ሊቀንስ ይችላል የሚል ስጋት ስላላት፣ የዲፕሎማሲ ጫና ከማድረጓ በተጨማሪ የጦር
ሠራዊቷን በተጠንቀቅ...
Jul 27, 2013
የነጀማነሽ ማህበር ከነብዩ ኤልያስ ለፓትርያርኩ አመጣን ያሉትን መልእክት ይፋ አደረጉ
Geez Bet | Saturday, July 27, 2013

አርቲስት ጀማነሽ ሰሎሞንን ያካተተው የማህበረ ሥላሴ
ዘደቂቀ ኤልያስ አባላት፣ ለፓትርያርኩ ያመጣነውን “የቅዱስ ኤልያስ” መልእክት የሚቀበለን አጥተናል በማለት ለመገናኛ
ብዙሃን ይፋ አደረጉ፡፡ በብሔረ ሕያዋን ይኖራል ከተባለው ነብዩ ኤልያስ ተልከን መልእክታችንን ለኢትዮጵያ
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ፓትርያርክ አቡነ ማቲያስ እንዳናደርስ የጥበቃ አባላት ከልክለውናል ያሉት የማህበሩ
አባላት፤ ከመልዕክቶቹ መካከል ትክክለኛው ሰንበት ቅዳሜ ስለሆነ በእሁድ ፋንታ በብሔራዊ ደረጃ ታውጆ መከበር
ይገባዋል የሚል እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ “ኦርቶዶክስ” የሚለውን ስያሜ የሚቃወሙት የማህበሩ አባላት፤ “ተዋህዶ”
የተሰኘው እምነት ጥንታዊ የጉባኤ እለታትን ጨምሮ አራት የቅዱሳን መታሰቢያ ቀናት በብሔራዊ በዓልነት ለማስከበር
ፓትሪያርኩ ከፌደራል መንግስቱ ጋር መነጋገር ይጠበቅባቸዋል...
Jul 27, 2013
ዶ/ር ያዕቆብ ኃ/ማሪያም ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ግልፅ ደብዳቤ ላኩ
Geez Bet | Saturday, July 27, 2013

የቤኒሻንጉል ተፈናቃዮች አሁንም በችግር ላይ ናቸው” (መኢአድና ሠማያዊ ፓርቲ)
ከቤኒሻንጉል ክልል ተፈናቅለው ከነበሩት የአማራ ክልል ተወላጆች
ጋር በተያያዘ የክልሉን የስራ ሃላፊዎችና መንግስትን ለመክሰስ፣ ሰማያዊ ፓርቲና መላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት
(መኢአድ) ጥብቅና ያቆሟቸው አለም አቀፍ የህግ ባለሙያው ዶ/ር ያዕቆብ ኃይለማሪያም፤ ለጠቅላይ ሚኒስትር ኃ/ማሪያም
ደሳለኝ ግልፅ ደብዳቤ መፃፋቸው ተገለፀ፡፡ ሁለቱ ፓርቲዎች ከትናንት በስቲያ ከሠዓት በኋላ በሠማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት
በጋራ በሠጡት መግለጫ፤ ተፈናቃዮቹ አሁንም ችግር ላይ መሆናቸውን፣ ልጆቻቸው ትምህርት ማቋረጣቸውን፤ በሚዲያ
እንደሚነገረው ወደ ቀድሞ ኑሯቸው አለመመለሳቸውንና በአጠቃላይ ችግር ላይ መሆናቸ...
Jul 24, 2013
አትሌት ኃይሌ ገ/ሥላሴ ፕሬዚዳንት ለመሆን ጓጉቷል
Geez Bet | Wednesday, July 24, 2013

ወደ ፖለቲካ የምገባው ህዝብ ማገልገል ስለምፈልግ ነው
*ኢትዮጵያን አርቀንና በረጅም ጊዜ የማናይ ከሆነ፣አባይን መገደብ አያስፈልገንም
*በውጭ ሆነው የሚቃወሙ አገራቸው ላይ መታገል አለባቸው ባይ ነኝ
ከጥቂት ዓመታት በፊት ጠ/ሚኒስትር የመሆን ፍላጐት እንዳለው ገልፆ የነበረው አትሌት ኃይሌ ገ/ሥላሴ፤ ሰሞኑን ከአሶሼትድ ፕሬስ ጋር ባደረገው ቃለምልለስ “የአገሪቱ ፕሬዚዳንት መሆን እፈልጋለሁ” በማለቱ የመነጋገሪያ ርዕሰ ጉዳይ ሆኗል፡፡ በ2007 ዓ.ም በሚደረገው አገራዊ ምርጫ ተወዳድሮ ፓርላማ ለመግባት ያሰበው አትሌቱ፤...
Jul 15, 2013
አምባሳደር ዘውዴ ረታ
Geez Bet | Monday, July 15, 2013

‹‹በስሚ ስሚ ከየትም የሚለቃቀሙ ታሪኮች ናቸው ችግር እየፈጠሩ ያሉት››
አምባሳደር ዘውዴ ረታ በቀዳሚዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት በጋዜጠኝነትና በዲፕሎማትነት ሲታወቁ በዚህ ዘመን ደግሞ የታሪክ ተመራማሪና ጸሐፊ ናቸው፡፡
ታሪክ ሲጽፉም ማስረጃዎችን በሚገባ እንደሚያገላብጡና
እንደሚመረምሩ ይነገርላቸዋል፡፡ በተለይ ከተወሰኑ ዓመታት ወዲህ ለንባብ ባበቋቸው የታሪክ መጻሕፍት የበለጠ
ይታወቃሉ፡፡ ‹‹የኤርትራ ጉዳይ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት፣ ተፈሪ መኮንን ረጅሙ የሥልጣን ጉዞ፣
የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት ታሪክ›› የሚባሉት መጻሕፍት የበለጠ ታዋቂ አድርገዋቸዋል፡፡ የኢትዮጵያ ዜና
አገልግሎት ድርጅትን መሥርተው በኃላፊነት ከመምራታቸው በፊት፣ የቤተ መንግሥት ዘጋቢ የነበሩ ሲሆን፣ ረዳት ሚኒስትር
ደረጃ ደርሰዋል፡፡ በዲፕሎማሲው ዓለም ደግሞ በተለያዩ...
Jul 12, 2013
የፓን አፍሪካኒዝም ራዕይ ጭንገፋ! (ክፍል ሁለት)
Geez Bet | Friday, July 12, 2013

ከ
ዚህ በፊት በጻፍሁት ጽሁፍ ስለ ፓን አፍሪካኒዝም ጅማሮ (አመሰራረት) ለማሳየት ሙከራ አድርጊያለሁ። ዛሬ ደግሞ የአፍሪካ ሕብረት እንዴት እንደተመሰረት ትንሽ ካየና በኋላ የፓን አፍሪካኒስቶች ራዕይ እንዴት በአፍሪካ አምባገነን መሪዎች እንደጨነገፈ እናያለን፡፡
በ1960ዎቹ ብዙ የአፍሪካ ሃገራት ነጻነታቸውን ያገኙበት ነበር፡፡ እነዚህ ነጻነታቸውን የተጎናጸፉ (የተጎናጸፉ የሚለው በምጸት ይነበብልኝ) ሃገራት ዳግም በኢምፔራሊስቶች እንዳይወረሩ የአፍሪካ አንድ መሆንን በየቦታው ማቀንቀን ጀመሩ። በተለይ ኩዋሜ ንኩርማህ አፍሪካ ጠንካራ እንድትሆንና ከውጭ ተጽዕኖ እንድትላቀቅ መዋሃድ አለባት ብሎ ያምን ነበር፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የያኔዎቹ መሪዎቹ ካሁኖቹ ጋር ሲወዳደሩ እጅግ ተራመጅ ነበሩ፡፡ በእነዚህና...