Time in Ethiopia:

Jun 2, 2014

የቅንጅት መሪ የነበሩት ብርቱካን ሚደቅሳ ከሃርቫርድ ተመረቁ

Geez Bet | Monday, June 02, 2014
ወ/ሪት ብርቱካን ሚዴቅሳ በታዋቂው ሃርቫርድ ዩኒቨርስቲ፤ በታፈነ ማህበረሰብ ውስጥ የዳኝነት ነጻነት ምን እንደሚመስል /independence of the judiciary in closed societies/  የሁለት ዓመት ጥናት በመከታተል ሁለተኛ ዲግሪያቸውን አገኙ፡፡
በኢትዮጵያ ታሪክ በተቃዋሚ ፓርቲ አባልነትም ሆነ በግል ተወዳዳሪነት ሴት ፖለቲከኞች ወደ አደባባይ በማይወጡበት
ወቅት በግል ተወዳዳሪነት የተሳተፉት ወ/ሪት ብርቱካን፤ በ1997ዓ.ም. በዶ/ር ብርሃኑ ነጋ እና በፕ/ር መስፍን ወልደማርያም በተመሰረተው ቀስተደመና ፓርቲ አባል የሆኑት በ1997 ዓ.ም ነው፡፡
ቀስተደመና ቅንጅትን ከፈጠሩት ፓርቲዎች መካከል አንዱ እንደነበር የሚታወስ ሲሆን ከምርጫው በኋላ ነው ወ/ሪት ብርቱካን የቅንጅት ሊቀመንበር እንዲሆኑ የተመደቡት፡፡ በ2001ዓ.ም. የአንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ መስራች በመሆን ሰርተዋል፡፡
ከምርጫ 97 ቀውስ ጋር በተያያዘ ሁለቴ ለእስር የተዳረጉት ወ/ሪት ብርቱካን፤ በሊቀመንበርነት ይመሩት ከነበረው አንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ የተሰናበቱ ሲሆን፤ ስንብታቸውን ተከትሎ በፖለቲካው ዓለም ይቀጥሉ እንደሆነ የተለያዩ ወገኖች ጥያቄ ሲያነሱ መቆየታቸው ይታወሳል፡፡ ወ/ሪት ብርቱካን ሚዲቅሳ የአንዲት ሴት ልጅ እናት ናቸው፡፡ 
Source: Addis Admass

No comments:

Post a Comment