የፕሬዚዳንትነት
ቆይታቸውን በማጠናቀቅ ላለፉት 12 ዓመታት የቆዩበትን ብሔራዊ ቤተ መንግሥት ለአዲሱ ፕሬዚዳንት እንደሚያስረክቡ
ለሚጠበቁት ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ መኖሪያ እንዲሆን በወር 530 ሺሕ ብር የሚከፈልበት ቤት ለመከራየት
የተገባው ውል ተሰረዘ፡፡
ምንጮች
እንደገለጹት፣ ፕሬዚዳንት ግርማ በቅርቡ ከቤተ መንግሥት ሲለቁ ከነቤተሰቦቻቸው እስከ ሕይወት ፍፃሜያቸው ይኖሩበታል
ተብሎ የተመረጠውና በወር 530 ሺሕ ብር ለመክፈል ከቤቱ ባለቤት ጋር የተደረገው ስምምነት፣ የሰነዶች ማረጋገጫና
ምዝገባ ጽሕፈት ቤት ቀርቦ ውል ታስሮበት ነበር፡፡ ሆኖም የኪራይ ስምምነቱ ውል ከተፈረመ ከሁለት ሳምንታት በኋላ
የፕሬዚዳንቱ ጽሕፈት ቤት ውሉ እንዲቋረጥ መወሰኑን አስታውቋል፡፡
አዲስ
አበባ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ውስጥ የሚገኘውን ለፕሬዚዳንት ግርማ መኖሪያ የተመረጠውን ቤት ለመከራየት
ከአከራዩ ጋር የኪራይ ውል ስምምነት ያደረገው የፕሬዚዳንቱ ጽሕፈት ቤት ነበር፡፡ ቀድሞም ቢሆን ስምምነቱ የተጋነነና ለG+1 መኖሪያ ቤት ይህን ያህል ዋጋ ይከፈላል የሚል ሙግት ቀርቦ እንደነበር ምንጮች ገልጸዋል፡፡ ስምምነቱ በይፋ ከተፈረመ በኋላ ግን የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጭምር ኪራይ ተገቢ አይደለም በማለት ውሳኔ በማስተላለፋቸው፣ የፕሬዚዳንቱ ጽሕፈት ቤት በውሉ ውስጥ የተካተቱትንና ውሉን ለማፍረስ ያስችሉኛል ያላቸውን አንቀጾች በመጥቀስ እንዲሰረዝ አድርጓል፡፡ ይህንንም የመኖሪያ ቤቱን ለማከራየት ውል ለገቡት ባለንብረት በደብዳቤ ማስታወቁንም ምንጮች ገልጸዋል፡፡ የኪራይ ስምምነቱን የመዘገበው የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ጽሕፈት ቤትም ውሉ መሰረዙን እንዲያውቅ የፕሬዚዳንቱ ጽሕፈት ቤት ደብዳቤ ጽፏል ተብሏል፡፡

ሕጋዊ
የውል ስምምነት ስለመደረጉ ማረጋገጫ የሰጠውና ምዝገባ ያካሄደው የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ጽሕፈት ቤት፣
ለፕሬዚዳንቱ መኖሪያ ተብሎ የኪራይ ስምምነት የተደረገበት ውል እንዲሰርዘው በደብዳቤ ተገልፆለታል ተብሏል፡፡
ተጋነነ
የተባለው የቤት ኪራይ ውል የተፈጸመው በአገሪቱ ሕግ መሠረት ሥልጣናቸውን ለለቀቁት ፕሬዚዳንት ቀሪ ሕይወታቸውን
በተሟላ ሁኔታ እንዲያሳልፉ አስፈላጊው ጥቅማ ጥቅም መጠበቅ ስላለበት ቢሆንም በዚህን ያህል ዋጋ ቤት መከራየት ተገቢ
አለመሆኑን የሚገልጹም አሉ፡፡
እንደ
ምንጮች ገለጻ ከሆነ ፕሬዚዳንቱ ከቤተ መንግሥት ሲወጡ ሊኖሩበት የሚችለውን ቤት ለማዘጋጀት የቤተ መንግሥት ጽሕፈት
ቤት አምስት የተያዩ ቤቶችን በመምረጥ የተሻለ ነው ተብሎ የተመረጠው አሁን ውሉ እንዲቋረጥበት የተደረገው ቤት ነው
ተብሏል፡፡
ከኃላፊነት
የተነሱት የአገርና የመንግሥት መሪዎች፣ ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎች፣ የምክር ቤት አባላትና ዳኞች የሚያገኙዋቸውን
መብቶችና ጥቅሞች ለመወሰን የወጣው አዋጅ እንደሚደነግገውም ለተሰናባቹ ፕሬዚዳንት ቤት እንደሚዘጋጅ ይጠቅሳል፡፡
በዚህ
አዋጅ አንቀጽ 4 መሠረት የመኖሪያ ቤት አገልግሎትን በተመለከተ የተጠቀሰው ከኃላፊነት የተነሳ ፕሬዚዳንት፣ ጠቅላይ
ሚኒስትር ወይም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ለራሱና ለቤተሰቡ መኖሪያነት የሚያገለግል የሠራተኞች ደመወዝን ጨምሮ
በመንግሥት ወጪ የሚተዳደር ከአራት እስከ አምስት መኝታ ክፍሎች ያሉት መኖሪያ ቤት የሚሰጠው መሆኑን ነው፡፡
ከሚሰጣቸው
መኖሪያ ቤት ባሻገር ደረጃቸውን የጠበቁ ሦስት ለመጓጓዣ የሚያገለግሉ የመንግሥት ተሽከርካሪዎችም ይመደቡላቸዋል፡፡
ለተሽከርካሪው ሹፌር ደመወዝ፣ የነዳጅና የጥገና እንዲሁም ሌላ ወጪ በመንግሥት የሚሸፈን መሆኑንም ያመለክታል፡፡
ከኃላፊነቱ
የሚነሱ ሦስት ከፍተኛ ኃላፊዎች በተለያዩ የሕዝባዊ አገልግሎቶች ላይ ከተሰማራ መኖሪያ ቤቱ በሚገኝበት ከተማ የቢሮ
አገልግሎት እንደሚሰጠው የሚደነግግ ሲሆን፣ ባለመብቶቹ የሚመርጧቸውና መንግሥት ደመወዛቸውን የሚከፍላቸው አንድ
ጸሐፊና አንድ ባለሙያ ጭምር ይኖራቸዋል፡፡
በዚሁ
አዋጅ ድንጋጌ መሠረት ከኃላፊነት የተነሳ ፕሬዚዳንት ጠቅላይ ሚኒስትር በሞት ሲለይ ጥቅማ ጥቅሙ ለቤተሰቦቻቸው
ይተላለፋል፡፡ በዚሁ መሠረት በሞት ሲለዩ የግል ወጪ አበል ለባለቤቱ መክፈሉ የሚቀጥል ሲሆን፣ የባለመብቱ ባቤትም
ከዚህ ዓለም በሞት ከተለዩም የመኖሪያ ቤት፣ የሕክምና ክፍያ የግል ደኅንነት ጥበቃ አገልግሎቶች እንደማይቋረጡበትም
ይደነግጋል፡፡
ፕሬዚዳንት ግርማ የ12 ዓመታት የፕሬዚዳንት ዘመን መጠናቀቅን ተከትሎ በአዋጁ መሠረት መንግሥት የሚያዘጋጅላቸው ቤት አዲሱ ፕሬዚዳንት ማንነት ይፋ ከመሆኑ በፊት ይዘጋጃል ተብሎ እየተጠበቀ ነው፡፡
Source: Reporter
No comments:
Post a Comment