የግብፅ ጦር ዘመን ባፈራዉ ዘመናይ ጦር መሳሪያ መግደል፣ መደብደብ ማሰሩን፣ ሙስሊም ወንድማማቾች እምነት፣ቁጭት ና
እልሕ በወለደዉ ፅናት መፋለሙን እንደቀጠሉ ነዉ።የዘመኑ ፈርዖኖች ፍሊሚያ የፈረዕኖቹን ዉልድ እየፈጀ፣ የፈርዖኖቹን
ታሪካዊ፣ ሥልታዊት ሐገርን እያወደመ-ቁል ቁል ያንደረድራታል።የጥፋት ዉድመቱ ሒደት፣ ዉጤት መዘዝ አረብ አይሁድን፣
አፍሪቃ እስያን፣ ከሁሉም በላይ አዉሮጳ አሜሪካን እያሳሰበ ግን አቋማቸዉን እያዋዠቀ ነዉ።የግብፅ እልቂት-ዉድመት
መነሻ የሁለቱ ፈርዖኖች ደምሳሳ ቅኝት ማጣቀሻ፣ የተቀረዉ ዓለም አቋም መድረሻችን ነዉ ላፍታ አብራችሁኝ ቆዩ።
*ግብረሰዶማዊያን በኢትዮጵያ ውስጥ “ሬንቦ” የተባለ ማህበር አቋቁመዋል
*በግብረሰዶማውያን ዙርያ የተካሄዱ ጥናቶች አዳዲስ መረጃዎችን ይፋ አድርገዋል
*ከ14 ዓመት በታች የሆኑ ህፃናትና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች የጥቃት ሰለባ ሆነዋል
*ኢትዮጵያውያን ከተመሳሳይ ፆታ ጋር ወሲብ ሲፈፅሙ የሚያሳዩ ፊልሞች ለገበያ ቀርበዋል
ከወራት በፊት እዚህ
አዲስ አበባ ከተማችን ውስጥ የተፈፀመ ታሪክ ነው፡፡ ድርጊቱ የተፈፀመው በአንድ ስመ-ጥር የወንዶች ልብስ መሸጫ
ቡቲክ ውስጥ ነው፡፡ ወጣቱ በቡቲኩ ውስጥ ተቀጥሮ መስራት ከጀመረ ቆየት ብሏል፡፡ በአለባበሱ ሽቅርቅርና ዘመናዊ
ነው፡፡ ወደ ቡቲኩ የሚመጡትን ደንበኞች በፈገግታና በትህትና እየተቀበለ ያስተናግዳል፡፡ ደንበኞች የፈለጉትን ልብስ
አስወርደው ለመለካት ወደ መልበሻ ክፍል ሲገቡ በዓይኑ ይከተላቸዋል፡፡ በገቡበት የመልበሻ ክፍል መጋረጃ ላይ
አይኖቹን *በግብረሰዶማውያን ዙርያ የተካሄዱ ጥናቶች አዳዲስ መረጃዎችን ይፋ አድርገዋል
*ከ14 ዓመት በታች የሆኑ ህፃናትና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች የጥቃት ሰለባ ሆነዋል
*ኢትዮጵያውያን ከተመሳሳይ ፆታ ጋር ወሲብ ሲፈፅሙ የሚያሳዩ ፊልሞች ለገበያ ቀርበዋል
ተክሎ ለደቂቃዎች እንደሚቆይ የቡቲኩ ባለቤት ብዙ ጊዜ ታዝቦታል፡፡ ሆኖም ደንበኞቹ አዲሱን ልብስ ለብሰው ሲወጡ ለማየት ከመጓጓት የተነሳ እየመሰለው በዝምታ ያልፈዋል፡፡ “ለምን እንዲህ ታያለህ?” ብሎ ጠይቆት አያውቅም