ባ
|
ለፈው ሳምንት በእለተ ቅዳሜ (8/10/2005) ማታ አራት ሰዓት
ከሃያ አካባቢ በዛሚ 90.7 በኢትዮፒካሊንክ ፕሮግራም አቅራቢዎች የቀረበው እጅግ አስደንጋጭ ዜና ነው፡፡ አስደንጋጩ ዜና በአንድ
ስሙ ባልተጠቀሰ ትምህርት ቤት ውስጥ የ10 እና የ11 ዓመት ወንድ ሕጻናት መደፈራቸው ሲሆን፣ ተጠርጣሪዎቹ ደግሞ የትምህርት ቤቱ
ስድስት መምህራን ናቸው፡፡ ልጆቹ በጋንዲ እና በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል እንደተረጋገጠው በግብረ ሶዶማዊያን ተደፍረዋል፡፡ ተደፍረዋል
የሚለው ቃል የነገሩን ክብደት ያቀለዋል፡፡ ከመግደል ሙከራ በላይ ተዶርጎባቸዋል ብል የተሻለ ይመስለኛል፡፡ በተለይ ነፍስ ያላወቁ ሕጻናት መሆናቸው ለሰሚው ከአስደማሚነት ባለፈ የሚያናድድና
ፍጹም ነውረኛነት የተሞላበት ነው፡፡ የአንደኛው ሕጻን እናት የልጇን እና የእሷን ነፍስ ለማጥፋት ሙከራ አድርጋለች፡፡ ይህን ነውረኛ
ተግባር ፈጸሙት የተባሉት ስድስቱ ተጠርጣሪ መምህራን